ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ አዲሱን ወረርሽኝ በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል?

Thumbnail for fact-checked article about Marburg outbreak in Ethiopia

በፋሲል አረጋይ

የተጠቀሰው መረጃ

ሰባ ሺህ (70,000) ተከታዮች ያሉው አዲስ መረጃ ADDIS Mereja የተሰኘ የፌስቡክ ገፅ ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በኢትዮጵያ የተከሰተውን ገዳይ ወረርሽኝ አስመልክቶ መግለጫ እንደሰጡ የሚገልጽ የቪዲዮ መረጃ በፌስቡክ አጋርቷል።

ብያኔ

በፌስቡክ የተሰራጨው የቪዲዮ መረጃ ሀሰት ነው። በጂንካ ከተማ የተከሰተውን ወረርሽኝ አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ አልሰጡም።

የማጣራት ስራ እና ግኝቶች

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ በምትገኘው ጂንካ ከተማ ከሰሞኑ የተከሰተውን የሂሞራጂክ ፊቨር በሽታ በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) “ሰበር መግለጫ” እንደሰጡ የሚገልጽ ቪዲዮ በፌስቡክ ተሰራጭቷል። ይህ ጽሑፍ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ የቪዲዮ መረጃው አራት መቶ ሃያ ስድስት ሺህ (426,000) ተመልካች ሲያገኝ አንድ ሺህ ስድስት መቶ (1600) የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ተጋርተውታል።

MultiFact Check የጉግል ሌንስ ምስል ማጣሪያን በመጠቀም ባካሄደው የመጀመሪያ ደረጃ ማጣራት ቪዲዮው ከዚህ ቀደም በተለያዩ ድረ-ገጾችና ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ጥቅም ላይ እንደዋለ አረጋግጧል።

በዚህም ቪዲዮው ለመጀመሪያ ጊዜ የተለቀቀው መጋቢት 26 ቀን 2012  በጠቅላይ ሚኒስትሩ የፌስቡክ ገጽ ላይ ነው። ይሄም በወቅቱ የኮቪድ 19 በሽታ በኢትዮጵያ ከተከሰተ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለማህበረሰቡ ያስተላለፉትን መልዕክት የሚያሳይ ነው። (እዚህ ይመልከቱ)

በተጨማሪም በወቅቱ የጠቅላይ ሚኒስትሩን የቪዲዮ መልዕክት በተመለከተ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን በይፋዊ የፌስቡክ ገጿቸው ላይ የሰሯቸውን ዘገባዎች እዚህእዚህ እና እዚህ መመልከት ይቻላል።

መደምደሚያ

ከላይ የተገለጸው የፌስቡክ ገጽ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በኢትዮጵያ የተከሰተውን ወረርሽኝ በተመለከተ ሰበር መግለጫ ሰጡ በሚል ያስተላለፈው መረጃ ፤ በሰሞኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጂንካ ከተማ ከተከሰተው በሽታ ጋር ምንም ተይይዝ የሌለውና ከአመታት በፊት ለሌላ መረርሽኝ የተሰጠ መግላጫ በመሆኑ መረጃውን ሀሰት ነው በማለት MFC በይኖታል፡፡

አውድ

ስለ በሽታው እስካሁን የምናውቀው

ከሰሞኑን በደቡብ ኢትዮጵያ ጅንካ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ ምንነቱ ያልተገለጸ በሽታ እንደተከሰተ በዚህም ሳቢያ ሁለት የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 6 ሰዎች እንደሞቱ ተዘገበ።

ይሄንን ተከትሎ ህዳር 3 ቀን 2018 ዓ/ም የጤና ሚኒስቴር መግለጫ ያወጣ ሲሆን በጅንካ ከተማ ሄሞራጂክ ፌቨር መከሰቱን አረጋገጠ። ይህ ጽሁፍ እየተዘጋጀ ባለበት ወቅት ማለትም ህዳር 5 ቀን 2018 ዓ/ም ተጨማሪ መግለጫ ያወጣው የጤና ሚኒስቴር በላብራቶሪ በተደረገ የዘረመል ምርመራ ይሄው የተከሰተው በሽታ ማርበርግ በመባል የሚታወቀው የሄሞራጂክ ፊቪር የበሽታ አይነት መሆኑን አስታውቋል። በኢትዮጵያ የዚህ በሽታ መከሰት ከተነገረ በኋላ የዓለም ጤና ድርጅት የ300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ለኢትዮጵያ መልቀቁን ዋና ዳይሬክተሩ ቴድሮስ አድሃኖም (ዶ/ር) ይፋ አድርገዋል። (እዚህ ይመልከቱ)

ማርበርግ ቫይረስ ምንድነው?

ቫይረሱ ለመጀመሪያ ጊዜ የታወቀው በአውሮፓውያኑ 1967 በጀርመን ማርበርግ እና ፍራንክፈርት እንዲሁም በሰርቢያ ቤልግሬድ በተከሰቱት ወረርሽኞች ሲሆን፣ 31 ሰዎች በቫይረሱ ከተያዙ በኋላ ሰባቱ በበሽታው ምክንያት ለህልፈት ተዳርገዋል። የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው በበሽታው ከሚያዙ ሰዎች መካከል በአማካይ ግማሾቹ ለሞት ይዳረጋሉ። ይህም ቁጥር ከ24 በመቶ እስከ 88 በመቶ አማካይ ውስጥ የሚያርፍ እንደሆነም የአለም የጤና ድርጀት በድረ ገጹ ላይ ያስነብባል፡፡ ቫይረሱ ሄመሬጂክ ትኩሳት ከኢቦላ ቫይረስ ጋር እንደ ፊሎቫይረስ የሚመደብ እና ተመሳሳይነት ያለው እንደሆነም ተብራርቷል።

በሽታው እንደ ትኩሳት ፣ ከባድ የራስ ምታት ፣ የጡንቻ ህመም የሚያሳይ ሲሆን ከቀናት በኋላም የሆድ ህመም እና ማስታወክን ጨምሮ የማያቋርጥ የህመም ምልክቶችን ያሳያል።

ምስል፦ ማርበርግ ቫይረስ [Shutterstock]

የማርበርግ ቫይረስ እንዴት ይተላለፋል?

እንደ የአለም የጤና ድርጅት ገለጻ ፤ የማርበርግ ቫይረስ በበሽታው በተያዘ ሰው የሰውነት ፈሳሽ ወይም በበሽታው ከተያዙ እንስሳት ጋር በመገናኘት ወይም በሽንታቸው እና በዝንጀሮዎች ወይም የሌሊት ወፎች ይተላለፋል። 

ቫይረሱ በሰዎች መካከል በተበከለ ደም፣ በአካል ክፍሎች ወይም በሀዋሳት ቀጥተኛ ግንኙነት እንዲሁም ከተበከሉ ቁሳቁሶች እና መገልገያዎች ሊተላለፍ ይችላል። በአንዳንድ ሁኔታዎች ቫይረሱ የተበከለ ምግብ ወይም ውሃ በመጠቀም ሊተላለፍ ይችላል፡፡ 

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ምልክቶች

እንደ WHO (የአለም የጤና ድርጅት) ከሆነ የማርበርግ ቫይረስ በሽታ በትንሽ ጉንፋን በሚመስሉ ምልክቶች ይጀምራል፡፡ ምልክቶቹ ብዙውን ጊዜ በሁለት ደረጃዎች የመጀመሪያ ደረጃ እና ከባድ ተብለው ይታያሉ፡፡ 

ደረጃ 1 – የመጀመሪያ ምልክቶች፡ መጀመሪያ ላይ፤ የ MVD ምልክቶች እንደ ጉንፋን መጥፎ ሁኔታ ይሰማቸዋል፡፡ ይህ ደረጃ ብዙውን ጊዜ በድንገት ይጀምራል እና በፍጥነት እየባሰ ይሄዳል። በደረጃ 1 ውስጥ የተለመዱ ምልክቶችም ፦ ድንገተኛ ከፍተኛ ትኩሳት ፣  በጣም ከባድ ራስ ምታት ፣ የጡንቻ ህመም እና የሰውነት ህመም ፣ በጣም የድካም ስሜት ወይም ደካማነት ፣ የምግብ ፍላጎት ማጣት የማቅለሽለሽ እና ማስታወክ ተቅማት የሆድ (የሆድ) ህመም በጉንፋን የተዘጋ ጉሮሮ፡፡ 

ደረጃ 2 – ከባድ ምልክቶች (ከ5-10 ቀናት) በሽታው ቶሎ ካልታከመ በሽታው ወደ ከባድ ደረጃ ሊሸጋገር ይችላል፡፡ ምልክቶቹም ፦ ከድድ፣ ከአፍንጫ ወይም ከቆዳ ስር የሚወጣ ደም መፍሰስ ፣  በቆዳው ላይ ቀይ ወይም ወይን ጠጅ ነጠብጣቦች (የውስጥ ደም መፍሰስ) ደም በማስታወክ ፣ የመተንፈስ ችግር የደረት ህመም ዝቅተኛ የደም ግፊት ፣ የሚጥል (በአንዳንድ ሁኔታዎች) ይህ ደረጃ ለሕይወት አስጊ የሆኑ ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል፡፡ 

በሽታው እንዴት ይታከማል? 

የማርበርግ ቫይረስ በሽታን አሁን ሙሉ ለሙሉ የሚያድነው የተለየ መድሃኒት የለም። ነገር ግን በቅድመ እንክብካቤ እና ትክክለኛ የሕክምና ድጋፍ ታካሚዎች ማገገም ይችላሉ፡፡  ዋናው የሕክምና ግብ ሰውነት ኢንፌክሽኑን በሚዋጋበት ጊዜ ጠንካራ ሆኖ እንዲቆይ መርዳት ነው፡፡ ሕክምናው ብዙውን ጊዜ የሚያጠቃለለውም ፦ የደም ሥር (IV) ፈሳሾች እና ኤሌክትሮላይቶች ድርቀትን ለመከላከል ፣ መተንፈስ አስቸጋሪ ከሆነ የኦክስጂን ሕክምና ጥቅም ላይ ይውላል ፤ የደም መፍሰስ ወይም ዝቅተኛ የደም ብዛት ሲከሰት ደም መውሰድ እና ቫይረሱ ወደ ሌሎች እንዳይዛመት መከላከል የመሳሰሉትን ህክምናው ያጠቃልላል፡፡

የMFC ማሳሰቢያ የቫይረሱ ምልክት ከታየብዎ ወይም ምልክቱን ያሳየ ሰው ካስተዋሉ ፣ ከንክኪ በመራቅና በፍጥነት በአቅራቢያዎ ወዳለ የልየታ ጣቢያ በመሄድ አልያም የጤና ባለሙያዎችን በመጥራት ራሰዎንም ሆነ ማህበረሰብዎን ከወረርሽኙ መዝመት እንዲጠብቁ እናሳስባለን፡፡

We at the MFC strive to verify misleading and false claims so that people get fact-based information and make an informed decision as well. In the process of our work, accuracy and transparency hold a central role. Therefore, if you see errors in our content, please write to us at info@multifactcheck.org so that our team will make corrections.

Share post on Social media

See related posts

ABOUT MFC

MultiFactCheck

(MFC) is an independent fact-checking organization which is launched to pin-point, track-down, scrutinize, investigate, interrogate, publish and distribute the factual accuracy of claims made by public figures. MFC’s project has geographical priorities. Our work mainly focuses on nations in the Horn of Africa and their diaspora community who reside abroad. We operates from various regions of Africa, Europe and North America. Through a multitude of professional proficiency, MFC deploys best practices of journalism, scholarship and expertise in order to flag, investigate and publish a fact.