የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማሳሰቢያ ሰጠ በሚል የቀረበው ደብዳቤ ትክክል ነው?

Thumbnail Image for fact-checked article about inmates

በፋሲል አረጋይ

የተጠቀሰው መረጃ

በሙስና የተጠረጠሩ ሰዎች ወደ ማረሚያ ቤት እየገቡ ስለሆነ ታራሚዎች ንብረታቸውን እንዲጠብቁ ማሳሰቢያ እንደተሰጣቸው የሚያሳይ የደብዳቤ ምስል በፌስቡክ ተሰራጭቷል። 

ብያኔ

ምስሉ በ 2007 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ከተጻፈ ደብዳቤ ተወስዶ የተቀናበረ በመሆኑ MFC ሐሰት ሲል በይኖታል።

በሙስና የተጠረጠሩ ሰዎች ወደ ማረሚያ ቤት እየገቡ እንደሆነ በመግለጽ ታራሚዎች ንብረቶቻቸውን ከስርቆት እንዲጠብቁ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማሳሰቢያ መስጠቱ ያሳያል በሚል አንድ የደብዳቤ ምስል በፌስቡክ ተሰራጭቷል። (አርካይቭ እዚህ ይመልከቱ)

በደብዳቤው ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማህተም እና የከንቲባ ጽ/ቤትና ካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ ስም እና ፍርማ ይታያል።

የማጣራት ስራ እና ግኝቶቹ

MultiFactCheck (MFC) “ለሁሉም ታራሚዎች” የተጻፈ ማሳሰቢያ እንደሆነ በመግለጽ የቀረበው ደብዳቤ ላይ የማጣራት ስራ ሰርቷል። በዚህም የGoogle Lens ምስል ማሰሻ መሳሪያን በመጠቀም በተደረገ የመጀመሪያ ደረጃ ማጣራት ደብዳቤው ከሰባት ዓመት በፊት “አፈንዲ ሙተቂ” በተባለ የፌስቡክ ገጽ ላይ ተለጥፎ ነበር። (እዚህ ይመልከቱ)

MFC በኢንተርኔት ላይ የሚገኙ መረጃዎች ላይ ባካሄደው ተጨማሪ ጥልቅ ምርመራ በፌስቡክ የተሰራጨው ደብዳቤ በ 2007 ዓ/ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ለሰማያዊ ፓርቲ ከጻፈው ባለሁለት ገጽ ደብዳቤ ተወስዶ ተቀናብሮ የተዘጋጀ መሆኑን አረጋግጧል።

ከታች በምስሉ ላይ እንደቀረበው ህዳር 11 ቀን 2007 ዓ/ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት በደብዳቤ ቁጥር አ አ/ከጽ/03/30.4/43 ለሰማያዊ ፓርቲ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ጽፏል። በዚህም የደብዳቤውን ሁለተኛ ገጽ በፎቶ ማቀናበሪያ መሳሪያ ይዘቱን በመቀየር ለታራሚዎች የተላለፈ ማሳሰቢያ እንደሆነ በማስመሰል ቀርቧል።

አውድ

በኢህአዴግ የስልጣን ዘመን ከነበሩ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የነበረው ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ ለማካሄድ ጥሪ በማቅረብ ይታወቃል። በተለይም ግንቦት 25 ቀን 2005 እና ሚያዚያ 19 ቀን 2006 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ አካሂዶ እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ (ተጨማሪ እዚህ እና እዚህ ይመልከቱ)

በተመሳሳይ የፖለቲካ ፓርቲው ህዳር 5 ቀን 2007 ዓ/ም የአደባባይ ስብሰባ ለማድረግ ጥሪ አስተላልፎ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ይሄንኑ ጉዳይ አስታውቆ ነበር። የከተማው አስተዳደር የጸጥታ አስከባሪዎች እጥረትን በምክንያትነት በመጥቀስ ፈቃድ መከልከሉን ተከትሎ አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበር በዚህም የከተማ አስተዳደሩ ከላይ የሚታየውን የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እንደጻፈ እንዲሁም ሰማያዊ ፓርቲ በደብዳቤ ምላሽ እንደሰጠ መረጃዎች ያሳያሉ። (ለተጨማሪ መረጃ እዚህ ይመልከቱ)

ሰማያዊ ፓርቲ ታህሳስ 21 ቀን 2011 ዓ/ም ባካሄደው ሁለተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ወቅት ነበር ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ጥምር ሀገራዊ ፓርቲ ለመመስረት በሚል ምክንያት የፈረሰው።

መደምደሚያ

በከፍተኛ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ሰዎች ወደ ማረሚያ ቤቶች እየገቡ ስለሆነ ሁሉም ታራሚዎች ንብረታቸውን እንዲጠብቁ ማሳሰቢያ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንደተሰጠ ተደርጎ የቀረበው ደብዳቤ ተቀናብሮ የተዘጋጀ መሆኑን በማረጋገጥ MFC ሐስተ ሲል በይኖታል።

ከሐሰተኛ መረጃ ስርጭት ጋር በተገኛኘ ከሚያጋጥሙ ጉዳዮች መካከል በዲጂታል መንገድ የሚቀርቡ ደብዳቤዎች ላይ የሚደረግ የይዘት ቅየራ አንዱ ነው። በማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በኩል የሚተላለፉ መሰል የደብዳቤ አይነቶችን ከማጋራታችን በፊት የሚተላለፉ የደብዳቤ ምስሎች መሰረታዊ የሚባሉ የደብዳቤ ይዘቶች ማለትም ቀንየደብዳቤ ቁጥርደብዳቤው የተጻፈለት አካልየተጻፈበት ጉዳይማህተምየኃላፊ ስም እና ፊርማ የተካተተበት መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው።

We at the MFC strive to verify misleading and false claims so that people get fact-based information and make an informed decision as well. In the process of our work, accuracy and transparency hold a central role. Therefore, if you see errors in our content, please write to us at info@multifactcheck.org so that our team will make corrections.

Share post on Social media

See related posts

ABOUT MFC

MultiFactCheck

(MFC) is an independent fact-checking organization which is launched to pin-point, track-down, scrutinize, investigate, interrogate, publish and distribute the factual accuracy of claims made by public figures. MFC’s project has geographical priorities. Our work mainly focuses on nations in the Horn of Africa and their diaspora community who reside abroad. We operates from various regions of Africa, Europe and North America. Through a multitude of professional proficiency, MFC deploys best practices of journalism, scholarship and expertise in order to flag, investigate and publish a fact.