በአርሲ የተገደሉ የኦርቶዶክስ አማኞች ተብሎ የተሰራጨው ምስል ትክክል ነው?

Thumbnail of a fact-checked article about violence in Arsi

በፋሲል አረጋይ

የተጠቀሰው መረጃ፦ በአርሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀገረ ስብከት ስር የሚገኙ አማኞች ተገድለዋል ከሚል ዜና ጋር ሁለት ምስሎች በፌስቡክ ተሰራጭቷል።

ብያኔ፦ ምስሉ በአሁኑ ወቅት በአርሲ ሀገረ ስብከት የተገደሉ ኦርቶዶክሳውያንን የሚያሳይ አይደለም። በመሆኑም MFC  ምስሉን  አሳሳች ሲል በይኖታል።

በምስሎቹ ላይ የተደረገ ማጣራት እና ግኝቶች

በማህበራዊ ሚዲያዎች በአርሲ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ግድያ እንደተፈጸመባቸው የሚገልጹ መረጃዎች ከተለያዩ ምስሎች ጋር እየተሰራጨ ይገኛል።

በተለይም አርባ ስምንት ሺህ (48,000) ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገጽ ጥቅምት 18 ቀን 2018 “በአርሲ ዞን ኖኖ ጃዊ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ 14 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አማኞች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል።” በማለት አንድ ምስል ለጥፏል። (እዚህ ይመልከቱ) ይሄ ዘገባ እስከተዘጋጀበት ወቅት መረጃው 1,300 ግብረመልስ ሲያገኝ 145 ጊዜ በሌሎች የፌስቡክ ተጠቃሚ ገጾች ተጋርቷል።

በተጨማሪም በፖለቲካ እንቅስቃሴው የሚታወቀው ይድነቃቸው ከበደ የተባለ ግለሰብ 107 ሺህ ተከታዮች ባሉት የፌስቡክ ገጹ “በምስራቅ አርሲ የሚገደሉ ኦርቶዶክሳውያን ቁጥር እየጨመረ ነው” በማለት መረጃውን ከሌላ ምስል ጋር ለጥፏል። (እዚህ ይመልከቱ)

በአርሲ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች መገደልን በተመለከተ የወጣውን መረጃ MultiFact Check (MFC) ከገለልተኛ ወገን ማረጋገጥ አልቻለም። ሆኖም እንደ መሰረት ሚዲያ ያሉ የዜና ገጾች ማህበረ ቅዱሳንን ዋቢ በማድረግ በአርሲ በሚገኘው ሀገረ ስብከት ውስጥ አማኞች መገደላቸውን ዘግበዋል። (እዚህ ይመልከቱ)

MFC ከላይ የተገለጹት የፌስቡክ ገጾች ካስተላለፉት መረጃ ጋር የተጠቀሙት ምስል ላይ ባካሄደው የመጀመሪያ ደረጃ ማጣራት ምስሎቹ በአርሲ ከተማ ከሰሞኑ የተገደሉ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት አማኞችን የማያሳይ እንደሆነ አረጋግጧል።

የጎግል ሌንስን በመጠቀም በተደረገ ተጨማሪ የማጣራት ስራ የመጀመሪያው ምስል ከሶስት ዓመት በፊት መስከረም 15 ቀን 2015 በምስራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ላይ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት አገልጋዮች እና አማኞች በተገደሉበት ወቅት የተነሳ መሆኑን ያሳያል። በዚህም በወቅቱ ድርጊቱ እንደተፈጸመ በመግለጽ የዜና ሽፋን በሰጡ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት ጥቅም ላይ ውሏል። (እዚህእዚህእዚህ እና እዚህ ይመልከቱ)

በሌላ በኩል MFC ይደነቃቸው ከበደ በተባለው ግለሰብ የፌስቡክ ገጽ ላይ መረጃውን በተመለከተ የቀረበው ምስል ላይ ምርመራ አድርጓል። በዚህም በግለሰቡ እንደቀረበው ምስሉ በምስራቅ አርሲ ዞን የተገደሉ የኦርቶዶክስ አማኞችን የሚያሳይ አለመሆኑ ተረጋግጧል።

ምንም እንኳን የምስሉ ባለቤት ማን እንደሆነ ባይታወቅም በጎንደር ከተማ የተገደሉ ዜጎች እንደሆኑ ከሚገልጽ መረጃ ጋር ከሶስት ወራት በፊት በማህበራዊ ሚዲያ ተለጥፎ የነበረ ሲሆን በአርሲ ተፈጽሟል ከተባለው የአማኞች ሞት ጋር የሚገናኝ አይደለም። (ለምሳሌ እዚህ እና እዚህ ይመልከቱ)

መደምደሚያ

) በአርሲ ሀገረ ስብከት ውስጥ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ላይ ግድያ መፈጸሙን የቤተ ክርስቲያኗ ማህበራት እና የዜና ምንጮች ዘግበዋል።

) ምንም እንኳን አማኞች እንደተገደሉ የሚገልጽ መረጃ ቢኖርም የፌስቡክ ገጾቹ የተጠቀሟቸው ምስሎች በአርሲ የተገደሉ የኦርቶዶክስ አማኞችን የሚያሳዩ እንዳልሆነ የጎግል ሌንስ ምስል ማጣሪያ አረጋግጧል።

በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱት ሁለት የፌስቡክ ገጾች የለጠፏቸው ምስሎች በአርሲ ሀገረ ስብከት ውስጥ የተገደሉ የኦርቶዶክስ አማኞችን የማያሳይ በመሆኑ MFC መረጃውን አሳሳች ሲል በይኖታል።

ማህበራዊ ሚዲያ መረጃዎችን በቀላሉ ለብዙ ሰዎች ለማስተላለፍ ቀላል እና ፈጣን አማራጭ መሆኑ ይታወቃል። ሆኖም ከቴክኖሎጂ ዕድገት ጋር ተያይዞ ዜጎች በቀላሉ መረጃዎችን የሚቀባበሉባቸው እነዚህ ዲጂታል መድረኮች ለሀሰተኛ መረጃ ስርጭት ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ ነው። በመሆኑም በእነዚህ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ መረጃዎችን የሚያጋሩ ተጠቃሚዎች ስለሚያስተላልፉት የምስል ፣ ቪዲዮ እና የጽሁፍ መረጃ አስፈላጊውን ማጣራት እንዲያደርጉና ተደራሲ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችም የመረጃውን ይዘት በመመርመርና ምንጩን በማጣራት የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን እንዲከላከሉ MFC ያሳስባል።

We at the MFC strive to verify misleading and false claims so that people get fact-based information and make an informed decision as well. In the process of our work, accuracy and transparency hold a central role. Therefore, if you see errors in our content, please write to us at info@multifactcheck.org so that our team will make corrections.

Share post on Social media

See related posts

በአርሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀገረ ስብከት ስር የሚገኙ አማኞች ተገድለዋል ከሚል ዜና ጋር ሁለት
On October 19, 2025, an X account named "ⓉⓃ @tesfanews" with 40.5K followers posted: "Ethiopia’s

ABOUT MFC

MultiFactCheck

(MFC) is an independent fact-checking organization which is launched to pin-point, track-down, scrutinize, investigate, interrogate, publish and distribute the factual accuracy of claims made by public figures. MFC’s project has geographical priorities. Our work mainly focuses on nations in the Horn of Africa and their diaspora community who reside abroad. We operates from various regions of Africa, Europe and North America. Through a multitude of professional proficiency, MFC deploys best practices of journalism, scholarship and expertise in order to flag, investigate and publish a fact.