ምስሉ በአማራ ክልል የተደረገ የጦር ኦፕሬሽንን ያሳያል?

በፋሲል አረጋይ

የተጠቀሰው መረጃ፦ በድምሩ ከሰባ ሰባት ሺህ (77,000) በላይ ተጠቃሚዎች ያሉት ሁለት የፌስቡክ ገጾች በአማራ ክልል ወሎ ዞን “ጃውሳ” የሚል መጠሪያ የተሰጠው ቡድን ላይ “ጥምር ጦሩ የማጽዳት እርምጃ እየወሰደ ነው” በማለት አንድ ምስል ለጥፈዋል። መረጃው የኢፌድሪ መከላከያ ሠራዊት በአካባቢው በሚገኙ ታጣቂዎች ላይ የጋራ ዘመቻ እያካሄደ መሆኑን ይጠቁማል።

ብያኔ፦ ምስሉ አሁን በአማራ ክልል ያለውን ወታደራዊ ዘመቻ የሚያሳይ አይደለም። በመሆኑም ምስሉ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት የነበረን ሁኔታ የሚያሳይ እንጂ ወቅታዊውን በአማራ ክልል ወሎ ዞን ከሚገኙ ታጣቂዎች ጋር እየተደረገ ያለውን ውጊያ የሚያሳይ አይደለም። በመሆኑም MFC ምስሉን አሳሳች ሲል በይፋ በይኖታል።

የማጣራት ስራ እና ግኝቶቹ

ከ41 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገጽ መስከረም 14 ቀን 2018 ዓ/ም “ሰበር መረጃ” በማለት በአማራ ክልል ወሎ ዞን “ጃውሳ” የሚል መጠሪያ የሰጠውን ቡድን ”ጥምር ጦሩ እያጸዳው ነው” በማለት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት መለያ ደንብ ልብስ የለበሱ እና ጦር መሳሪያ የያዙ ወታደሮች የሚታዩበትን ምስል ለጥፏል።

መረጃው ይሄ ዘገባ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ ከሁለት ሺህ አምስት መቶ (2500) በላይ ግብረ መልስ ያገኘ ሲሆን ከአንድ ሺህ ሁለት መቶ (1200) አስተያየትም ተሰጥቶበታል። ይሄው መረጃ ከገጹ ተከታዮች ውጪ ሌሎች የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ተደራሽ እንዲሆን ሃምሳ አንድ  (51) ጊዜ ተጋርቷል። (እዚህ ይመልከቱ)

በተመሳሳይ ሰላሳ ስድስት ሺህ (36,000) ተከታዮች ያሉት  “Raya Press” የሚል መጠሪያ ያለው የፌስቡክ ገጽ ይሄንኑ መረጃ ከምስሉ ጋር የለጠፈ ሲሆን የአንባቢን ትኩረት በሚስብ መልኩም አጋርቶታል። ይሄው መረጃ ይህ ዘገባ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ ከሶስት መቶ ሃምሳ (350) በላይ ግብረ መልስ ያገኝ ሲሆን ሁለት መቶ ሃያ (220) አስተያየቶችም ተሰጥቶበታል። (እዚህ ይመልከቱ)

ምስሉ በአማራ ክልል በጥምር ጦር የተደረገ የኦፕሬሽን ዘመቻን ያሳያል?

በፌስቡክ ገጾቹ ለተላለፈው መረጃ አባሪ ተደርጎ የቀረበው ምስል ላይ MultiFact Check (MFC) የማጣራት ስራ ሰርቷል። MFC ባካሄደው የመጀመሪያ ደረጃ የGoogle Lens ምስል ማሰሻ ምስሉ ከአንድ አመት በፊት ጀምሮ ለቀረቡ የማህበራዊ ሚዲያ ልጥፎች ማሳያ ተደርጎ ሲቀርብ መቆየቱን አረጋግጧል።

ምስሉ መቼ እና በማን የተወሰደ ነው?

MFC ምስሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለበትን ጊዜ እና ምስሉን በካሜራ ያስቀረው አካል ማን ነው? የሚለውን ምላሽ ለማግኘት ከጎግል ምስል ማሰሻ በተጨማሪ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና መደበኛ መገናኛ ብዙሃን ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ጥልቅ ዳሰሳ አድርጓል።

በዚህም ለመጀመሪያ ጊዜ ምስሉ ጥቅም ላይ የዋለው ሐምሌ 7 ቀን 2014 ዓ/ም በኢፌድሪ መከላከያ ሠራዊት የፌስቡክ ገጽ ነው። ምስሉ ከሕወሃት ኃይል ጋር በነበረው ጦርነት የ6ኛ ዕዝ የሰራዊት አባላትን የሚያሳይ ሲሆን በወቅቱ የዕዙ ዋና አዛኝ የነበሩት ሜጄር ጀኔራል ተስፋዬ ወልደማሪያምን አስተያየት ያካተተ ዘገባ ላይ ነበር ጥቅም ላይ የዋለው።

በመረጃው ላይም በግልጽ ዘገባው በማን እንደተሰራ እና ፎቶግራፉ በማን እንደተነሳ ተቀምጧል። በተጨማሪም የምስሉ ባለቤት የኢፌድሪ መከላከያ ሠራዊት እንደሆነ የሚያሳይ  አርማ ይታያል። (እዚህ ይመልከቱ)


መደምደሚያ

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረጉ የሀሰት መረጃዎች ዘመቻዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተራቀቁ መጥተዋል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የበይነመረብ ተጠቃሚ ሲሆኑ፣ የተቀነባበሩ ይዘቶችም በፍጥነት ይሰራጫሉ። የተለያዩ አንጃዎች ደጋፊዎች በርከት ያሉ የሐሰት የይገባኛል ጥያቄዎችን ያሰራጫሉ። ጥያቄዎቹን ለማሰራጨት ማህበራዊ ሚዲያን ይጠቀማሉ። ብዙ ጊዜ ምስሎችን እና ቪዲዮዎችን ለመቀየር በተለያዩ ዘዴዎች ይገለገላሉ። በእነዚህም ስልቶች የተሳሳቱ መረጃዎችን በማሰራጨት እና በግጭቶች ላይ የህዝቡን ግንዛቤ በማዛባት የሰላም ጥረትን ያበላሻሉ።

በዚህ መሰረት MFC በፌስቡክ ላይ ከተጋራው መረጃ ጋር የተያያዘውን ምስል ላይ የእውነታ ማረጋገጥ ፍተሻን አድርጓል:-
ሀ) የመጀመሪያ ግኝቶች፦ጎግል ሌንስን በመጠቀም የተገላቢጦሽ የምስል ፍለጋ ፎቶው ከአንድ አመት በላይ በኢንተርኔት ላይ ሲሰራጭ እንደነበረ አረጋግጧል።
ለ) ምንጭ መከታተያMFC ምስሉን ያገኘው ከኢፌድሪ መከላከያ ሠራዊት ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ የታተመው ከህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ጋር በተደረገው ጦርነት ሐምሌ 7 ቀን 2014 ዓ/ም ነው።
ሐ) ዋናው ዐውደ-ጽሑፍ፦ ምስሉ በኢፌድሪ መከላከያ ሠራዊት የ6ኛው የጦር ሰራዊት ዕዝ ወታደሮችን ያሳያል። በወቅቱ የክፍሉ አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ተስፋዬ ወልደማርያም አስተያየቶችን የያዘ ዘገባ አካል ነበር።
መ) የማጭበርበር ማስረጃ፦ የኢትዮጵያ ፌዴራል መከላከያ ሰራዊት አርማ አሳሳች ልጥፎቹ ላይ ከምስሉ ላይ ተነስቷል፣ ይህም ሆን ተብሎ ለማሳሳት ጥቅም ላይ የዋለ እንደሆነ ይጠቁማል።

ስለዚህ ከላይ የተጠቀሱት የፌስቡክ ገጾች ባስተላለፉት መረጃ የተጠቀሙት ምስል በአማራ ክልል ወሎ ዞን ላይ በታጣቂዎች ላይ የተፈጸመን ዘመቻ የሚያሳይ አይደለም። በመሆኑም ከላይ በተጠቀሱት አራት ግኝቶች መሰረት፣ MFC ልጥፉን በይፋ አሳሳች ሲል በይኖታል

አውድ

በኢትዮጵያ መንግስት እና የትግራይ ኃይሎች ለሁለት አመት የዘለቀው ጦርነት የ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እጅግ ደም አፋሳሽ ጦርነት ሲሆን የሟቾች ቁጥርን በተመለከተ ይፋዊ አሃዝ ባይኖርም ወደ ስድስት መቶ ሺህ  (600,000) ያህል ዜጎችን ህይወት እንደተቀጠፈ ዘገባዎች ያመለክታሉ። (እዚህ ይመልከቱ)

ጦርነቱ የኢትዮጵያ መንግስትን በመወከል አቶ ሬድዋን ሁሴን እንዲሁም የትግራይ ኃይሎች ቃል አቀባይ የነበሩ አቶ ጌታቸው ረዳ ደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ላይ በተፈጸሙት ስምምነት አብቅቷል።

ሆኖም የፌደራል መንግስቱ ከትግራይ ኃይሎች ጋር የፈጸመውን ስምምነት ተከትሎ የፌደራል መንግስት የአማራ ክልል ልዩ ሃይልን ትጥቅ ለማስፈታት የወሰደው እርምጃ በክልሉ ከሚገኙ ታጣቂ ኃይሎች ጋር ግጭት ውስጥ ገብቷል። ከሚያዚያ 2015 ዓ/ም ጀምሮ ከሁለት አመት በላይ ያስቆጠረው የፌደራል መንግስት እና የአማራ ክልል ታጣቂ ኃይሎች ግጭት በሰው ፣ መሰረተ ልማት ፣ ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ህይወት ላይ ከፍተኛ ውድመት እያደረሰ ቀጥሏል።

We at the MFC strive to verify misleading and false claims so that people get fact-based information and make an informed decision as well. In the process of our work, accuracy and transparency hold a central role. Therefore, if you see errors in our content, please write to us at info@multifactcheck.org so that our team will make corrections.

Share post on Social media

See related posts

በአርሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀገረ ስብከት ስር የሚገኙ አማኞች ተገድለዋል ከሚል ዜና ጋር ሁለት
On October 19, 2025, an X account named "ⓉⓃ @tesfanews" with 40.5K followers posted: "Ethiopia’s

ABOUT MFC

MultiFactCheck

(MFC) is an independent fact-checking organization which is launched to pin-point, track-down, scrutinize, investigate, interrogate, publish and distribute the factual accuracy of claims made by public figures. MFC’s project has geographical priorities. Our work mainly focuses on nations in the Horn of Africa and their diaspora community who reside abroad. We operates from various regions of Africa, Europe and North America. Through a multitude of professional proficiency, MFC deploys best practices of journalism, scholarship and expertise in order to flag, investigate and publish a fact.