የመከላከያ ሰራዊት ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት እንደደረሰ ያሳያል በሚል የቀረበው ምስል ትክክለኛ ነው?

Thumbnail Image for a fact-checked article about the ENDF vehicles damaged in Tigray
በፋሲል አረጋይ

የተጠቀሰው መረጃ

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ ከተለያዩ ጽሑፎች ጋር የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት እንደደረሰ ፤ እና “Before/After” ከሚል ገለጻ እና ቅንብር ጋር ልጥፎች ተጋርተዋል፡፡

ብያኔ

ሐሰት

“After” በሚል የኢትዮጵያ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች መውደማቸውን እንደሚያሳይ የቀረበው ምስል ከኢትዮጵያ ጋር ቀጥተኛ ትይይዝ የሌለው ሲሆን በሱዳን ኮርዶፋን ግዛት የደረሰን ውድመት የሚያሳይ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች መውደማቸውን እንደሚያሳይ የቀረበው ምስል

ምስል-1:- የኢትዮጵያ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች መውደማቸውን እንደሚያሳይ የቀረበው ምስል

በጥቅምት 2/2019 ዓ.ም. ጀምሮ ፌስቡክና ቲክቶክን ጨምሮ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ በተለያዩ አካውንቶች ከሁለት ፎቶዎች የተቀናበረ ምስል ሲጋሩ ታይተዋል። ልጥፎቹም “አትመኑ ብለን አልነበር” ፣ “(TDF) ታላቁ ሀይል እገሰገሰ ነው” ፣ “ከተሞችን ያዝኩ ለማለት በገፍ የገባው ሰራዊት እያለቀ ነው። ውጊያው ገና አሁን የተጀመረ ይመስላል።… ” ወዘተ። ከሚሉ ጽሑፎች ጋር የተጋሩ ሲሆኑ ፤ የመልዕክታቸው ማዕከልም የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ወደ ሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ለውጊያ መጓዛቸውንና በኋላ ግን ከፍተኛ ጥቃትና ውድመት እንደደረሰባቸው ማሳየት ነው።

እነዚህም ልጥፎች ከተሰራጩበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ ግብረመልሶችን ያገኙ ሲሆን የብዙዎችንም ትኰረት ስበዋል፡፡

የማጣራት ስራ እና ግኝቶች

የMFC የሐቅ ማጣራት ቡድን አባላት የመረጃውን እውነተኛነት ለማረጋገጥ ምስሎቹን የፈተሹ ሲሆን ለዚህም የጉግል ምስል ፍለጋ እና ማጣሪያ መሳሪያን ተጠቅመዋል፡፡

በማጣራት ሂደቱ የሚከተሉት ግኝቶች ተገኝተዋል፡፡

ሀ. “Before” የተባለው ምስል ምንጭ

● በልጥፎቹ ምስል ላይ ከላይ በኩል “Before” በሚል ተያይዞ የቀረበው ፎቶ ቢያንስ ከመስከረም 16 አንስቶ በኢንተርኔት ላይ በተለያዩ አካውንቶች አማካይነት ሲዘዋወር ከነበረ ቪዲዮ ላይ ስክሪንሾት ተደርጎ የተወሰደ ነው፡፡

● እነዚህ ቪዲዮዎችም እንደሚያሳዩት ወታደራዊ ከባድ መሳሪያዎች በከባድ የጭነት መኪናዎች ላይ ተጭነ ሲጓጓዙ የሚያሳዩ ናቸው፡፡

ለ. “After” የተባለው ምስል ምንጭ

● በምስሉ ከታች በኩል ውድመት ደርሷል በሚል “After” ተብሎ የቀረበው ምስል ከኢትዮጵያ ወይም ከመከላከያ ኃይል ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌለው ነው። የጉግል ሌንስ ማጣሪያ እና “ሱዳን ትሪቡን” መረጃ እንደሚያረጋግጠው ይህ ምስል በሱዳን ኮርዶፋን ግዛት ውስጥ በነበረው ወታደራዊ ግጭት ምክንያት የደረሰን ውድመት የሚያሳይ ሲሆን በሰኔ 13 2018 ዓ.ም. በሱዳን ሰራዊት ማህበራዊ ሚዲያ በኩል የተሰራጨ ነው፡፡

● ሁነቱ የተፈጠረበት ስፍራ በሱዳን ድንበር ውስጥ የሚገኝ ሆኖ ሳለ ፤ ፎቶው በኢንተርኔት ላይ የተለቀቀበት ጊዜ ደግሞ ከአሁኑ የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት አስቀድሞ ቢሆነም ሆን ተብሎ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ተሽከርካሪዎች ላይ የደረሰ ጥቃት እንዲመስል ተደርጎ ቀርቧል።

ከሱዳን ትሪቢዩን ዌብሳይት የተወሰደ ሲሆን ፣ በሰኔ 13 2018 ዓ.ም. በሱዳን ሰራዊት ማህበራዊ ሚዲያ በኩል የተሰራጨ ምስል

ምስል-2፡- ከሱዳን ትሪቢዩን ዌብሳይት የተወሰደ ሲሆን ፣ በሰኔ 13 2018 ዓ.ም. በሱዳን ሰራዊት ማህበራዊ ሚዲያ በኩል የተሰራጨ ምስል

አውድ

የኢትዮጵያ መንግስት ከመስከረም 13/ 2029 ዓ.ም. ጀምሮ ከህወሓት እና ከተባበሩት አማጺ ቡድኖች ጋር እንዳዲስ ወዳገረሸ ውጊያ ከገባ በኋላ፣ የፌዴራል መንግሥት ኃይልና አጋሮቹ በሰሜኑ የትግራይ ክልል ወታደራዊ እርምጃቸውን አጠናክረው መቀጠላቸው ተዘግቧል። በተለይም አዲግራት ከተማን ጨምሮ ወደ አንዳንድ የክልሉ ከተሞች መግባታቸውን እና የክልሉን ዋና ከተማ መቀሌን እና አካባቢውን መቆጣጠራቸው ተገልጿል።

በዚህ የፀጥታ ቀውስ መባባስ ሳቢያ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሙሉ በሙሉ የተቋረጠ ሲሆን ፤ ኢትዮጵያ – ኤርትራ አማጺ ቡድኖችን እየደገፈች ነው ስትል ፣ የኤርትራ ወታደራዊ ኃይሎች ወደ ሰሜናዊ ኢትዮጵያ ድንበር መሻገራቸውን መረጃዎች አሳይተዋል። አስመራ ይህንን ውንጀላ ያስተባበለች ሲሆን ፣ ኢትዮጵያ በበኩሏ በኤርትራ ኃይሎች ላይ የድሮን ጥቃቶችን መፈጸሟ እና የኤርትራ ዲፕሎማቶችን ከሀገር ማባረሯ ሁለቱ አገራት ወደ ጦርነት ሊገቡ ይችላሉ የሚል ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል።

በአዲስ አበባ ከተማም ከዚህ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ድንገተኛ ፍንዳታዎች እና የደህንነት ስጋቶች መከሰታቸው ሲዘገብ ፤ ሁኔታው ወደ ሰፊና ቀጠናዊ ጦርነት እንዳያመራ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ጣልቃ እንዲገባ ሁለቱም አገራት ጥሪ አቅርበዋል። ዓለም አቀፍ ተቋማትም በሰሜኑ ክፍል ያለው የጸጥታ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን እያሳሰቡ ይገኛሉ።

ማጠቃለያ

MFC በማህበራዊ ሚዲያው ላይ የተሰራጨውን ይህንን ምስል እና ጽሑፍ የተሳሳተ እና ልጥፉም የተሰራጨበት ተነሳስቶት (Intention) ሰዎችን ለማደናገር የተደረገ በመሆኑ ሐሰት ሲል በይኖታል።

Accuracy & Transparency Commitment

We at the MFC strive to verify misleading and false claims so that people get fact-based information and make an informed decision as well. In the process of our work, accuracy and transparency hold a central role. Therefore, if you see errors in our content, please write to us at info@multifactcheck.org so that our team will make corrections.

Share post on Social media

See related posts

MultiFact Check's work countering disinformation in Ethiopia has been featured in a France 24 English
A brief weekly summary of political, security, and humanitarian developments around the Horn of Africa

ABOUT MFC

MultiFactCheck

(MFC) is an independent fact-checking organization which is launched to pin-point, track-down, scrutinize, investigate, interrogate, publish and distribute the factual accuracy of claims made by public figures. MFC’s project has geographical priorities. Our work mainly focuses on nations in the Horn of Africa and their diaspora community who reside abroad. We operates from various regions of Africa, Europe and North America. Through a multitude of professional proficiency, MFC deploys best practices of journalism, scholarship and expertise in order to flag, investigate and publish a fact.