በቲክቶክ የተሰራጨው ቪዲዮ በጎፋ የደረሰውን አደጋ ያሳያል?

በፋሲል አረጋይ

የተጠቀሰው መረጃ፡ በጎፋ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የሟቾች ቁጥር 300 ደርሷል ከሚል መረጃ ጋር አንድ ቪዲዮ በቲክቶክ ተሰራጭቷል

ብያኔ፡ መረጃው በተሰራጨበት ወቅት የሟቾች ቁጥር 300 መድረሱ አልተረጋገጠም ከመረጃው ጋርም የተያያዘው ቪዲዮ እ.አ.አ በ 2022 በህንድ ግዛት የተከሰተ የመሬት መንሸራተት የሚያሳይ ነው።

ሐምሌ 18 ቀን 2016 ዓ/ም ከ99ሺ በላይ ተከታዮች ያሉት የቲክቶክ አካውንት “በጎፋ ዞን መሬት መንሸራተት የሞቱት 300 ሰው ደረሰ” ከሚል ጽሑፍ ጋር የመሬት መንሸራተት ሲከሰት የሚያሳይ ቪዲዮ አጋርቷል

ይህ ጽሑፍ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ ቪዲዮው ከ 2 ሚሊየን 500ሺ በላይ ሰው የተመለከተው ሲሆን ከ186ሺ በላይ ግብረ መልስ እና 4664 አስተያየት ሲያገኝ ከ118ሺ ጊዜ በላይ ተጋርቷል።


ሆኖም ምንም እንኳን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን የመሬት መንሸራተት አደጋ የተከሰተ ቢሆንም ይህ ጽሁፍ ለንባብ እስከበቃበት ጊዜ ድረስ በአደጋው ህይወታቸው ያለፈው ሰዎች ቁጥር 257 ሲሆን ከመረጃው ጋር ተያይዞ የቀረበው ቪዲዮ ሀሰተኛ እና በጎፋ ያለውን አደጋ የሚያሳይ አለመሆኑን አረጋግጠናል።

MFC የተለያዩ የሀቅ ማጣሪያ መንገዶችን በመጠቀም አጣርቶ  የቪዲዮውን ትክክለኛ መረጃ አግኝቷል። በዚህም ቪዲዮው ለመጀመሪያ ጊዜ የተጋራው CNN News 18 በተባለው ከ7 ሚሊየን 800ሺ በላይ ሰብስክራይበር ባለው የህንድ የዜና አውታር ይፋዊ የዩቲውብ ገጽ ላይ ነው። (እዚህ ይመልከቱ)


በዚህም ቪዲዮው እ.ኤ.አ በ2022 በሰሜናዊ ምስራቅ ህንድ በምትገኘው ሜጋሊያ ግዛት የደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋን የሚያሳይ ነው።

በመሆኑም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን የደረሰውን የመሬት መንሸራተት አደጋ ከሚገልጽ መረጃ ጋር የተጋራውን ቪዲዮ MFC ሀሰት በማለት በይኖታል።

ሐምሌ 14 2016 ዓ/ም በክልሉ ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተቀበሩ ሰዎችን ለማውጣት በማግስቱ ሐምሌ 15 2016 ዓ/ም በተሰባሰቡ የአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ለሁለተኛ ጊዜ የመሬት መንሸራተት አደጋ ደርሶባቸዋል።

ይህ ጽሑፍ ለንባብ እስከበቃበት ጊዜ ድረስ ከ250 በላይ ሰዎች ህይወት በአደጋው ተቀጥፏል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ቢሮ ኦቻ (OCHA) በአደጋው የሞቱ ዜጎች ቁጥር እስከ 500 ሊደርስ እንደሚችል ጠቁሟል። (እዚህ ይመልከቱ)

የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የሚመለከቷቸው መረጃዎች ላይ ግበረመልስ ከመስጠታቸው እና ከማጋራታቸው አስቀድመው የመረጃውን እና ከመረጃው ጋር ተያይዘው የሚቀርቡ የምስል እና ቪዲዮ ማስረጃዎችን እንዲመረምሩ እንዲሁም ትክክለኛነታቸውን እንዲያረጋግጡ MFC ያበረታታል።

We at the MFC strive to verify misleading and false claims so that people get fact-based information and make an informed decision as well. In the process of our work, accuracy and transparency hold a central role. Therefore, if you see errors in our content, please write to us at [email protected] so that our team will make corrections.

Share post on Social media

See related posts

Fuulli feesbuukii tokko barreffama ‘’Aangoo qeerroo: Diinonni keenya qabeenya biyyaa balleessaa jiru. Duguuggaa sanyii raawwachuuf
የሲቪል አቬሽን ህግ በመጣስ እና በሽብር ወንጀል የተከሰሰው ዮሐንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል) ከእስር መለቀቁን የሚገልጽ

ABOUT MFC

MultiFactCheck

(MFC) is an independent fact-checking organization which is launched to pin-point, track-down, scrutinize, investigate, interrogate, publish and distribute the factual accuracy of claims made by public figures. MFC’s project has geographical priorities. Our work mainly focuses on nations in the Horn of Africa and their diaspora community who reside abroad. We operates from various regions of Africa, Europe and North America. Through a multitude of professional proficiency, MFC deploys best practices of journalism, scholarship and expertise in order to flag, investigate and publish a fact.