የተሰራጨው ቪዲዮ “የአማራ የዘር ማጥፋትን” አያሳይም

በናኦል ጌታቸው

የተሰጠቀው መረጃ፦ Ethiopian Lecturer Union (ሲተረጎም የኢትዮጵያ መምህራን ህብረት) የተባለ አንድ ግለሰብ በሌሎች ግለሰቦች የሚሰቃይበትን አሰቃቂ ቪዲዮ በማጋራት “የአማራ የዘር ማጥፋት [በአብይ አህመድ አማካይነት] በኢትዮጵያ እየተጠናከረ መሆኑን በመግለፅ መረጃውን አሰራጭቷል።

ብያኔ፦ ቪዲዮው አንድ ግለሰብ በሊቢያ የሕገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች እገታ ተፈፅሞበት እየተሰቃየ የሚታይበት በመሆኑ ልጥፉ ሐሰት ነው።

በX አካውንቱ ላይ ከ5,900 በላይ ተከታዮች ያለዉ Ethiopian Lecturer Union (ሲተረጎም የኢትዮጵያ መምህራን ህብረት) አንድ ግለሰብ በሌሎች ግለሰቦች የሚሰቃይበትን አሰቃቂ ቪዲዮ አጋርቷል። በመጋቢት 15/2016 ዓ.ም. የተጋራው ይህ ቪዲዮ በእንግሊዘኛ የተፃፈ መግለጫም አብሮት ተያይዟል። በእንግሊዝኛ የተጻፈው ፅሁፉም ሲተረጎም: “…. የአማራው የዘር ማጥፋት በኢትዮጵያ እየተጠናከረ ነው። አብይ አህመድ (የኦሮሞ ብሄረሰብ ተወላጅ) በአማራው ላይ ያነጣጠረ የዘር ማጽዳት ድጋፍ እያደረገ ነው፣ ዘግናኝ ድርጊቶችም ቀጥለዋል።…” የሚል ነው። ከላይ የተጠቀሰው ልጥፍም ይህ ፅሁፍ እስከሚታተምበት ዕለት ድረስ ከ48,000 በላይ ዕይታ ሲያገኝ ከ350 ጊዜ በላይ ተደጋግሞ ተጋርቷል።

ምስል 1፡ የX አካውንቱ ያሰራጨው ቪዲዮ

በመሆኑም በX አካውንቱ በተጠቀሰው መሰረት አሰቃቂው ቪዲዮው “በአብይ አህመድ ስለሚደገፍ የአማራ የዘር ማፅዳት” በተባለዉ ጋር ተያያዥነት ያለው መሆን አለመሆኑን MultiFactCheck (MFC) አጣርቷል።

Refugees in Libya የተሰኘውና በሊቢያ አካባቢ ስላሉ ስደተኞች መግለጫዎችን በማውጣት የሚታወቀው ተቋም በX አካውንቱ እንዲሁም በዌብሳይቱ ላይ በተጠቀሰው አሰቃቂ ቪዲዮ ላይ እየተሰቃየ ስለሚታየው ግለሰብ የሚገልፅ ፅሁፍ ይፋ አድርጓል።

ምስል 2፡ Refugees in Libya ካጋራው ፅሁፍ የተወሰደ ስክሪንሹት

በተቋሙ ፅሁፍም እንደተመላከተው በቪዲዮው ላይ እየተሰቃየ የሚታየው ግለሰብ ጌዲዮን ሳሙኤል የተባለ እና በሐዋሳ የተወለደ የ28 ዓመት ወጣት ሲሆን ቤተሰቦቹን ለመርዳት በማሰብ በጥር 28/2016 ዓ.ም. ከሐገር ወጥቷል። በየካቲት 20ም ጌዲዮን በአጋቾች በሊቢያ መያዙንና 15,000 ዶላር እንዲከፍሉ ለእናቱ በስልክ ተነገራቸው። የተጠየቀውን ገንዘብም ለመክፈል ባለመቻሉ አጋቾች ጌዲዮን እየተሰቃየ የሚታይበትን ቪዲዮ ወደ ቤተሰቡ ልከዋል። 

ጉዳዩን ይበልጥ ለማጣራት MFC የጌዲዮን ሳሙኤል እናት የሆኑትን ወ/ሮ ገነት ጥላሁንን በስልክ ያነጋገረ ሲሆን “… በሄደ በ17 ቀኑ ስልክ ተደወለልኝ። ‘ሊቢያ ላይ ተይዟልና 950 ሺሕ ብር ተጠይቋል’ ብሎ ጓደኛው ነገረኝ። …. እንደገናም ለ4ኛ ጊዜ ደግሞ ወደ ታች ዘቅዝቀው እየገረፉት ቪዲዮ ልከውልኝ ‘ተሽጧል 1.7 ሚሊዮን ብር አምጭ’ ብለው ደወሉ። …” በማለት ምላሽ የሰጡ ሲሆን ፤ በርከት ላለ ጊዜ እየደወሉ ታጋቹ በተለያየ መንገድ የሚሰቃይበትን ቪዲዮ እየላኩ ገንዘብ እንዲከፍሉ መጠየቃቸውንም ለመረዳት ተችሏል። 

ከዚህም በተጨማሪ ወ/ሮ ገነት ወደ ማህበራዊ ሚዲያው በመውጣት እርዳታ ሲጠይቁና ሁኔታውን ሲያስረዱም የሚታዩበት ቪዲዮ ተጋርቷል።

ምስል 3፡ የታጋቹ እናት ወ/ሮ ገነት ጥላሁን እርዳታ ለመጠየቅ በማህበራዊ ሚዲያ ካሰራጩት ቪዲዮ የተወሰደ ስክሪንሹት

ምስል 3፡ የታጋቹ ጌዲዮን ሳሙኤል የቀደመ ፎቶግራፍ

በመሆኑም በEthiopian Lecturer Union የተጋራው ቪዲዮ “በአብይ አህመድ ስለሚደገፍ የአማራ የዘር ማፅዳት” በተባለዉ ጋር ተያያዥነት ያለው ሳይሆን ፤ በሊቢያ የሕገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች እገታ ተፈፅሞበት እየተሰቃየ የሚታይ ግለሰብን የሚያሳይ በመሆኑ ልጥፉ ሐሰት መሆኑን MFC አረጋግጧል።

We at the MFC strive to verify misleading and false claims so that people get fact-based information and make an informed decision as well. In the process of our work, accuracy and transparency hold a central role. Therefore, if you see errors in our content, please write to us at [email protected] so that our team will make corrections.

Share post on Social media

See related posts

Akkawuntiin TikTooki tokko viidiyoo “misooma koridaraa finfinetti” jedhu qoode. Viidiyoon akkawuntii TikTookii kun qoode taatee
Fuulli feesbuukii tokko barreffama ‘’Aangoo qeerroo: Diinonni keenya qabeenya biyyaa balleessaa jiru. Duguuggaa sanyii raawwachuuf

ABOUT MFC

MultiFactCheck

(MFC) is an independent fact-checking organization which is launched to pin-point, track-down, scrutinize, investigate, interrogate, publish and distribute the factual accuracy of claims made by public figures. MFC’s project has geographical priorities. Our work mainly focuses on nations in the Horn of Africa and their diaspora community who reside abroad. We operates from various regions of Africa, Europe and North America. Through a multitude of professional proficiency, MFC deploys best practices of journalism, scholarship and expertise in order to flag, investigate and publish a fact.