ሁለቱ ምስሎች በየካቲት 20/2016 በምስራቅ ወለጋ ጊዳ አያና ወረዳ ተፈፀመ የተባለውን ጥቃት አያሳዩም

በናኦል ጌታቸው

________________________________________________________________________________

የተጠቀሰው መረጃ ፦ ሁለት ፎቶዎች የረቡዕ የካቲት 20/2016ቱ የምስራቅ ወለጋ ጊዳ አያና ወረዳ ጥቃት የሚያስረዱ ተደርገው በፌስቡክ ላይ ተሰራጭተዋል።

ብያኔ ሁለቱ ምስሎች በየካቲት 20/2016 ዓ.ም. በምስራቅ ወለጋ ጊዳ አያና ወረዳ ከተፈፀመው ጥቃት ጋር የሚያያዙ ባለመሆናቸውን ፤ ሐሰት ሲል MFC በይኗቸዋል።

_________________________________________________________________________________

በርካታ የፌስቡክ አካውንቶች “በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ በንፁሀን ላይ የደረሰ ጥቃትን” በማውገዝ ሀዘናቸውን የገለፁ ሲሆን ፤ በፅሁፋቸውም ሁለት ምስሎችን እያያያዙ በየካቲት 21/2016 ፖስት አድርገዋል (በስክሪንሾቱ በሚታየው መልኩ)። ለአብነትም Sagalee Wareegamtoota WangeelaaGemechisa HirpaDaandii ElemooJabaa KeenyaSiraaji EliyaasiHamatamaan Leenca ፣ በመሳሰሉት አካውንቶች የተለጠፉትን ፖስቶች መጥቀስ የሚቻል ሲሆን ፣ እያንዳንዳቸውም ከ 20 እስከ 87 የሚደርሱ ግብረ መለሶች አግኝተዋል።

ምስል 1 :- ይህ ምስል Sagalee Wareegamtoota Wangeelaa የተባለውና 6,900 ተከታዮች ያሉት አካውንት በ “ጊዳ አያናው” ጥቃት ማዘኑን የገለፀበት ሲሆን በፅሁፉ መጨረሻም “ማሳሰቢያ” በማለት ምስሎቹ የጊዳ አያና መሆናቸውን የሚገልፅበት ስክሪንሾት ነው

በአፋን ኦሮሞ ተፅፈው የተዘዋወሩት ፅሁፎች ፤ ክስተቱ መፈፀሙንና የሶስት ሰዎች ሕይወት “ፋኖ ናቸው” በተባሉ ታጣቂዎች መፈፀሙን ከስፍራው መረጃ ማግኘታቸውን የተለያዩ ዘገባዎች ወጥተዋል። ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ የአካባቢውን ነዋሪዎች ዋቢ አድርጎ እንደዘገበውም ጥቃቱ የተፈፀመው ረቡእ የካቲት 20/2016 ነው (ይህንን መስፈንጠሪያ ይመልከቱ)።

ይሁን እንጂ የተለያዩ የፌስቡክ አካውንቶቹ የተጠቀሰውን ጥቃት ለማስረዳት የተጠቀሟቸው ሁለቱ ምስሎች ግን የቆዩ በመሆናቸው ፎቶዎቹ ረቡዕ የካቲት 20/2016 ዓ.ም. ተፈፀመ ለተባለው ክስተት ማስረጃ ተደርገው መቅረባቸው አሳሳች ነው።

በምዕራቡ የኢትዮጵያ ክፍል በተለይም በምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ ለበርካታ አመታት የዘለቀ ግጭትና የሰላም መደፍረስ መኖሩ የሚታወቅ ነው። ግጭቶቹም አንዴ በመንግስት እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት መካከል ፤ ሌላ ጊዜ በፋኖ ኃይሎችና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት መካከል እና በሌሎች ኢ-መደበኛ ታጣቂዎች መካከል ሲደረግም ቆይቷል። በነዚህ ጥቃቶችም የበርካታ ንፁሐን ዜጎች ህይወት ማለፉንም በተለያዩ ጊዜያት የሚወጡ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ርፖርት ያመለክታል። 

በተመሳሳይም በዚሁ ሳምንት የካቲት 20/2016 በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ጊዳ አያና ወረዳ በተፈፀመ እና “የፋኖ ታጣቂዎች ፈፅመውታል” በተባለው ጥቃት የ3 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተዘግቧል። የፌስቡክ ፖስቶቹም በዚህ አውድ ውስጥ የተሰራጩ ናቸው። 

ይሁንና የጎግል ምስል ማፋለጊያ (Google Reverse Image Search) ውጤት እንደሚያሳየው ፤ ምስሎቹ ከሁለት ወራት በፊት ከህዳር 30/2016 በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲዘዋወር ነበር (እነዚህን ማስፈንጠሪያዎች ተጠቅመው ይመልከቷቸው)።

ምስሎቹም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በተሰራጨው መልኩ ‘የተከሰተን ግደያ’ የሚያሳይ ሳይሆን በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት ምክንያት ‘ሕፃፅ’ በተባለ የትግራይ አካባቢ በኤርትራ ሰራዊት ተፈፅሟል ያሉትን “የሰብአዊ መብት ጥሰት” ከሚዳስስ ፊልም ላይ የተወሰደ ቀረፃ መሆኑን ሕፃፅ የተሰኘው ፊልም ዳይሬክተር Resom Aredom በፌስቡክ ላይ አጋርቷል።

ምስል 2 :- ይህ ምስል የፊልሙ ፀሐፊና ዳይሬክተር እንደሆነ የሚናገረው ርእሶም አረዶም በማህበራዊ ሚዲያው ላይ በተሳሳተ መልኩ ስለተዘዋወሩት ሁለቱ ፎቶዎች ያጋራበት ስክሪንሾት ሲሆን ፣ የተፃፈው የትግርኛ ፅሁፍም በፎቶዎቹ ላይ የሚታዩት የፊልሙ ኣባላት መሆናቸውን ይገልፃል። 

እንደዚሁም የፊልሙ ፕሮዲዩሰር እንደሆነ የሚገልፀው TK Adver ከአንድ ወር በፊት ስለሚዘዋወረው ፎቶ በFeb 2 እንዲህ ብሎ አጋርቶ ነበር። “ይህ ምስል የተወሰደው በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ፊልም በምንሰራበት ወቅት ነው። አንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ይህንን ምስል ለፖለቲካዊ መልእክቶች እየተጠቀሙበት ነው።”

ምስል 3 :- ይህ ምስል “ሕፃፅ” የተሰኘው በትግርኛ ቋንቋ የተሰራው ፊልም ፖስተር መሆኑን የፊልሙ አባላት ካጋሩት መረጃዎች ለማወቅ ተችሏል።

ሌሎች ከቀረፃ ጀርባ ምስሎችንም ስንምለከት ተመሳሳይ ተዋናዮችና የፊልም ካሜራ የያዙ ባለሙያዎችን እንመለከታለን (ከታች ያለውን ስክሪንሾት ይመልከቱ)።

ሁለት አመት በዘለቀውና በፕሪቶሪያው ስምምነት ማብቂያ ያገኘው የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስትና የትግራይ ሀይሎች ጦርነት ብዙ ደም ያፋሰሰ መሆኑ የሚታወስ ነው። በተለይም ከኢትዮጵያ ጎን ተሰልፎ የትግራይን ሀይሎች ሲዋጋ የነበረው የኤርትራ ሰራዊት በትግራይ ክልል በንፁሀን ላይ የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈፅሟል ተብሎ በተለያዩ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ሪፖርቶች ሲወጡ ቆይተዋል። 

ከእነዚህ መካከልም አንደኛው በኤርትራ ሰራዊት በሕፃፅ ከተማ ተፈጽሟል የተባለው ጭፍጨፋ ነው። ይህም “ሕፃፅ” የተሰኘው ፊልም ይህንን ክስተት የሚዘግብ እንደሆነ ዳይሬክተር እንደሆነ የሚገልፀው ርእሶም ኣረዶም ባደረጋቸው ቃለ መጠይቆች ገልጿል።

በመሆኑም MFC የተዘዋወሩትን ፎቶዎች በመመርመር ሁለቱ ምስሎች በየካቲት 20/2016 ዓም በምስራቅ ወለጋ ጊዳ አያና ወረዳ ከተፈፀመው ጥቃት ጋር የሚያያዙ አለመሆናቸውን በማረጋገጡ ፤ ሐሰት ሲል በይኗቸዋል።

We at the MFC strive to verify misleading and false claims so that people get fact-based information and make an informed decision as well. In the process of our work, accuracy and transparency hold a central role. Therefore, if you see errors in our content, please write to us at [email protected] so that our team will make corrections.

Share post on Social media

See related posts

Akkawuntiin TikTooki tokko viidiyoo “misooma koridaraa finfinetti” jedhu qoode. Viidiyoon akkawuntii TikTookii kun qoode taatee
Fuulli feesbuukii tokko barreffama ‘’Aangoo qeerroo: Diinonni keenya qabeenya biyyaa balleessaa jiru. Duguuggaa sanyii raawwachuuf

ABOUT MFC

MultiFactCheck

(MFC) is an independent fact-checking organization which is launched to pin-point, track-down, scrutinize, investigate, interrogate, publish and distribute the factual accuracy of claims made by public figures. MFC’s project has geographical priorities. Our work mainly focuses on nations in the Horn of Africa and their diaspora community who reside abroad. We operates from various regions of Africa, Europe and North America. Through a multitude of professional proficiency, MFC deploys best practices of journalism, scholarship and expertise in order to flag, investigate and publish a fact.