የኢትዮጵያ አየር መንገድን ህግ በመጣስ የተከሰሰው “ጆን ዳንኤል” ከእስር ተለቋል?

በፋሲል አረጋይ

የተጠቀሰው መረጃ፦ የሲቪል አቬሽን ህግ በመጣስ እና በሽብር ወንጀል የተከሰሰው ዮሐንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል) ከእስር መለቀቁን የሚገልጽ ቪዲዮ በፌስቡክ ተሰራጭቷል

ብያኔ:- ሐሰት – ተጠርጣሪውን ጨምሮ በክስ መዝገቡ የተከሰሱ ስድስት ግለሰቦች በጊዜ ቀጠሮ ላይ ይገኛሉ

ነሃሴ 16 ቀን 2016 ዓ/ም ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ ሊደረግ በነበረ በረራ ሁከት እና ብጥብጥ ፈጥረዋል እንዲሁም በሽብር ወንጀል ተሳትፎ አላቸው በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የሚታወቀው ዮሐንስ ዳንኤልን (ጆን ዳንኤል) ጨምሮ 6 ግለሰቦች ክስ ተመስርቶባቸዋል።

በወቅቱም በነበረው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ምክንያት አውሮፕላኑ መብረር እንደማይችል የአየር መንገዱ የበረራ ደህንነት ሰራተኞች በሚገልጹበት ጊዜ ተሳፋሪዎቹ ከአውሮፕላን “አንወርድም” በማለት ከሰራተኞቹ ጋር ውዝግብ ውስጥ ሲገቡ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በማህበራዊ ሚዲያ ተሰራጭቷል።

ይሄንን ተከትሎም የአዲስ አበባ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን በእነዮሀንስ ዳንኤል ላይ በሽብርተኝነት እና የአቬሽን ሕግን መተላለፍ በሚል በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ክስ መስርቶባቸዋል።

ነሃሴ 23 ቀን 2016 ዓ/ም 34ሺ ተከታዮች ያሉት “yuti nass” የሚል ስያሜ ያለው የፌስቡክ ገጽ  “በዋስ ተለቅቄያለሁ አድናቄዎቼ አመሰግናለሁ” ከሚል ጽሑፍ ጋር 23 ሴኮንድ ርዝመት ያለውን የዮሃንስ ዳንኤል ቪዲዮ ለጥፏል። ይሄ ጽሑፍ ለንባብ እስከበቃበት ቪዲዮው 1.5 ሚሊየን ዕይታ እና 34ሺ ግብረ መልስ አግኝቷል። በተጨማሪም 2600 አስተያየት ያገኘው ልጥፉ ለሌሎች የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ተደራሽ እንዲሆን 331 ጊዜ ተጋርቷል።

በተጨማሪም መረጃው ከፌስቡክ በተጨማሪም በዩቲውብ እና ቲክቶክ ላይ መሰራጨቱን የጉግል ምስል ማሰሻ (Google Lens) ያሳያል።


በመረጃው ላይ እንደቀረበው ጆን ዳንኤል በሚል የማህበራዊ ሚዲያ ስም የሚታወቀው ዮሐንስ ዳንኤል በዋስ ተለቋል? የሚለውን MFC አጣርቷል። 

በዚህም ትክክለኛው ቪዲዮ የተለጠፈው ከአንድ አመት በፊት ነሃሴ 15 ፣ 2015 ዓ/ም 2.3 ሚሊየን ተከታይ ባለው የዮሐንስ ዳንኤል የቲክቶክ አካውንት መሆኑን MFC አረጋግጧል። የ 43 ሴኮንድ ርዝመት ያለው ቪዲዮ ዮሐንስ ዳንኤል በማህበራዊ ሚዲያ የሚያደርገውን የበጎ አድራጎት ስራ በተመለከተ የሚሰጠውን ማብራሪያ ያሳያል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ ከተከሰተው ጉዳይ በኋላ በማግስቱ ነሃሴ 16 ፣ 2016 ዓ/ም የአዲስ አበባ ፖሊስ እነ ዮሐንስ ዳንኤልን በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በማቅረብ “የአየር መንገዱን የአየር መንገዱን ሥራ በማስተጓጎል ወንጀል” መጠርጠራቸውን በመግለጽ፣ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ጠይቆባቸው ነበር፡፡

እነ ዮሐንስ ዳንኤልም በጠበቆቻቸው በኩል የዋስትና ጥያቄ አቅርበዋል። የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤቱም የ20 ሺህ ብር ዋስትና በማስያዝ እንዲወጡ ቢፈቅድም የተጠረጠሩበት አየር መንገዱን በማወክ ብቻ ሳይሆን በሽብር ወንጀል እንደሆነ በመግለጽ ከእስር ሳይለቀቁ ጉዳዩን የፌደራል ፖሊስ እንዲይዝ ተደርጎ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት እንዲቀርቡ ተደርጎ ክርክር ተደርጓል።

ነሃሴ 21 ቀን 2016 ዓ/ም በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡት ተጠርጣሪዎቹ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የፈቀደው  የዋስትና መብት እንዲጸናላቸው ጠይቀዋል። ፍርድ ቤቱ የዋስትና ፈቃዱ የተሰጠው ‹‹ሁከትና ብጥብጥ›› በሚል ለቀረበለት ክርክር እንጂ፣ በሽብርተኝነት ስለመጠርጠራቸው ስለማያስረዳ በሚል ለፌደራል ፖሊስ መርማሪ ቡድን የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ ለ ጳጉሜ 4 ፣ 2016 ዓ/ም ቀጠሮ ሰጥቷል።

በመሆኑም በማህበራዊ ሚዲያ የተላለፈው ቪዲዮ የቆየ ሲሆን በቪዲዮው ላይ ዮሐንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል) ከቀረበበት የሽብር እና የአቬሽን ህግ ጥሰት ክስ ጋር በተገናኘ በዋስ እንደተለቀቀ ተደርጎ የቀረበው መረጃ ሐሰት መሆኑን MFC አረጋግጧል።

We at the MFC strive to verify misleading and false claims so that people get fact-based information and make an informed decision as well. In the process of our work, accuracy and transparency hold a central role. Therefore, if you see errors in our content, please write to us at [email protected] so that our team will make corrections.

Share post on Social media

See related posts

Akkawuntiin TikTooki tokko viidiyoo “misooma koridaraa finfinetti” jedhu qoode. Viidiyoon akkawuntii TikTookii kun qoode taatee
Fuulli feesbuukii tokko barreffama ‘’Aangoo qeerroo: Diinonni keenya qabeenya biyyaa balleessaa jiru. Duguuggaa sanyii raawwachuuf

ABOUT MFC

MultiFactCheck

(MFC) is an independent fact-checking organization which is launched to pin-point, track-down, scrutinize, investigate, interrogate, publish and distribute the factual accuracy of claims made by public figures. MFC’s project has geographical priorities. Our work mainly focuses on nations in the Horn of Africa and their diaspora community who reside abroad. We operates from various regions of Africa, Europe and North America. Through a multitude of professional proficiency, MFC deploys best practices of journalism, scholarship and expertise in order to flag, investigate and publish a fact.