Search
Close this search box.

ወደ አማራ ክልል ሰራዊት እየገባ ነው በሚል የተሰራጨው መረጃ ሀሰት ነው

በፋሲል አረጋይ

የተጠቀሰው መረጃ፦ የኦሮሚያ ኃይል ወደ አማራ ክልል ለወረራ እየገባ እንደሆነ የሚገልጽ ጽሁፍ ከቪዲዮ መረጃ ጋር በ”X” ማህበራዊ ሚዲያ ተሰራጭቷል

ብያኔ:- ነገር ግን ጽሁፉ የጥላቻ ንግግር ሲሆን የቪዲዮ መረጃው ከአራት አመት በፊት የኦሮሚያ ፖሊስ ምርቃት ስነ-ስርዓት የሚያሳይ በመሆኑ MFC ሀሰት ሲል ፈርጆታል።

በአማራ ክልል በመንግስት  ኃይላት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የቀጠለውን ግጭት መነሻ በማድረግ “Tordit- ቶ” የሚል ስያሜ ያለው የ”X” አካውንት  “ይህ ስብስብ ለተዘጋጀበት 10ኛው የኦሮሞ ወረራ ስምሪት ወስዶ ወደ አማራ ክልል በመትመም ላይ ነው። የጭፍጨፋውን ፊሽካ አብይ አህመድ ነፍቶ አስጀምሯል። ይህ ስብስብ ለኮንቬንሽናል ጦርነት አይደለም የተዘጋጀው። የጀኖሳይድ አርሚ ነው።” በማለት አንድ ቪዲዮ አሰራጭቷል (ይሄንን ማስፈንጠሪያ ይመልከቱ)

 

ተቀማጭነቱን በአዲስ አበባ ኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የሚተዳደረው የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (OBN) አርማ ባለበት በዚህ ቪዲዮ ላይ ከ35 በላይ በሆነ ረድፍ የተደረደሩ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል የደንብ ልብስ የለበሱ “ወታደሮች” ይታያሉ።  (ይሄንን ማስፈንጠሪያ ይመልከቱ)

MFC በልጥፉ ይዘት እና በቪዲዮው ላይ ማጣራት አድርጓል። በዚህም መልዕክቱ የተዛባ እና የጥላቻ ንግግር መሆኑን እንዲሁም ቪዲዮው በአሁኑ ወቅት ወደ አማራ ክልል እየገባ ያለ ጦር ነው ተብሎ የቀረበው መረጃ የተዛባ እና ሀሰተኛ መሆኑን አረጋግጧል።

የጥላቻ ንግግር

የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል የተባለ ሀገር በቀል ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት በመጋቢት 2013 ዓ/ም ለህትመት ባበቃው የጸረ ጥላቻ ንግግር እና የተዛቡ መረጃዎች መለያ መመሪያ (ለማንበብ ይሄንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ) የጥላቻ ንግግር ማህበረሰባዊና የዘር ውጥረቶችን እንደሚያባብስ እንዲሁም ለጥቃት እንደሚያነሳሳ ይገልጻል።

ተቋሙ በዚሁ ሰነዱ የጥላቻ ንግግር ተለይቶ የሚታወቅባቸው ባህሪዎች ንግግሩ ማንነት ላይ ያነጣጠረ ፣ ነውጥን የሚያበረታታ ፣ የፍረጃ ቃላትን የያዘ ፣ መልዕክቱ የደረሳቸው ተደራሲያን እርምጃ እንዲወስዱ የሚያበረታታ መሆኑን ይገልጻል።

በመሆኑም በዚሁ የ”X” አካውንት የተላለፈው መልዕክት ብሄር ላይ ያነጣጠረ ፣ ነውጥን የሚያበረታታ እና የፍረጃ ቃላትን በመጠቀም የጥላቻ መልዕክት አስተላልፏል።

ከአውድ ውጪ የተወሰደ ቪዲዮ

ከላይ ከተገለጸው መረጃ ጋር ተያይዞ የቀረበው የቪዲዮ ግብዓት ወደ አማራ ክልል እየገባ ያለ ጦር ሳይሆን የኦሮሚያ ክልል መንግስት ከአራት አመት በፊት የካቲት 29 ቀን 2012 ዓ/ም በቡልቡላ ማሰልጠኛ ማዕከል ለ30 ጊዜ የፖሊስ አባላትን ባስመረቀበት ወቅት የተቀረጸ መሆኑን MFC አረጋግጧል። (ይሄንን ማስፈንጠሪያ ይመልከቱ)

የክልሎችን የልዩ ኃይል አደረጃጀት ለመበተን እና በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ወይንም በመደበኛው የፖሊስ የጸጥታ መዋቅር ውስጥ የማደራጀት ውሳኔ መወሰኑን ተከትሎ በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ “የፋኖ” አደረጃጀቶች ውሳኔውን በመቃወም ከፌደራል መንግስት ጋር ግጭት ውስጥ መግባታቸው ይታወቃል።

በክልሉ የተቀሰቀሰው ግጭት ተከትሎ በሐምሌ 25  2015 ዓ/ም በክልሉ እንዲሁም እንደ አስፈላጊነቱ በመላው ኢትዮጵያ ተግባራዊ የሚሆን ለስድስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን  የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ጥር 24 2016 ዓ/ም ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ለተጨማሪ አራት ወራት እንዲራዘም አድርጎ ክልሉ በአስቸኳይ አዋጅ ስር ቆይቷል።

በአማራ ክልል በመንግስት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል አሁንም ድረስ በዘለቀው ግጭት የበርካታ ንጹሃን ህይወት ማለፉን ፣ ንብረት መውደሙን እንዲሁም ዜጎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና አለም አቀፍ ተቋማት ይፋ አድርገዋል።

We at the MFC strive to verify misleading and false claims so that people get fact-based information and make an informed decision as well. In the process of our work, accuracy and transparency hold a central role. Therefore, if you see errors in our content, please write to us at [email protected] so that our team will make corrections.

Share post on Social media

See related posts

ጎንደር ላይ ፋኖን የሚቃወም ሰልፍ እንደተደረ የሚገልጽ ጽሁፍ ከቪዲዮ መረጃ ጋር በ “X” ማህበራዊ ሚዲያ

ABOUT MFC

MultiFactCheck

(MFC) is an independent fact-checking organization which is launched to pin-point, track-down, scrutinize, investigate, interrogate, publish and distribute the factual accuracy of claims made by public figures. MFC’s project has geographical priorities. Our work mainly focuses on nations in the Horn of Africa and their diaspora community who reside abroad. We operates from various regions of Africa, Europe and North America. Through a multitude of professional proficiency, MFC deploys best practices of journalism, scholarship and expertise in order to flag, investigate and publish a fact.

Follow Us