ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የበጎ አድራጎት ስራ በመስራት የሚታወቀው ማስተር አብነት ሽልማት እየሰጠ ነው?

ፋሲል አረጋይ

የተጠቀሰው መረጃ፦ በማስተር አብነት ስም የተከፈቱ የቴሌግራም ግሩፖች ሽልማት እየሰጡ እንደሆነ የሚገልጽ መረጃ አሰራጭተዋል።

ብያኔነገር ግን የቴሌግራም ግሩፖቹ ተመሳስለው የተከፈቱ መሆናቸው የተረጋገጠ ሲሆን ያቀረቡት የሽልማት አይነት እና መጠን ሐሰት ነው።

ከ 138 ሺ በላይ አባላት ያሉት “Master Abinet Kebede” የተባለ የቴሌግራም ግሩፕ ግንቦት 13 ቀን 2016 ዓ/ም “…50 ሰዎች አድ ላደረገ 5ሺህ ብር እንልካለን” የሚል መረጃ አጋርቷል

ይሄው የቴሌግራም ግሩፕ በተመሳሳይ ቀን “ዮሴፍ በቀለ የተባለ ግለሰብ ሽልማቱን በፍጥነት ተቀብሏል ሌሎቻችሁም ፍጠኑ…” የሚል የላኪው ማንነት እንዳይታይ የተሸፈነ የንግድ ባንክ የሞባይል ባንኪንግ የገንዘብ ዝውውርን የሚያሳይ ምስል ለጥፏል

MFC ባካሄደው የዳሰሳ ጥናት መሰረት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በበጎ ስራዎቹ በሚታወቀው ማስተር አብነት ስም የተከፈቱ ከ 15 በላይ የቴሌግራም ግሩፖችን አግኝቷል። በተመሳሳይ እነዚህ ግሩፖች የቴሌግራም ተጠቃሚዎች ወደ ግሩፑ ሰዎችን አባል ሲያደርጉ ከፍተኛ መጠን ያለው ሽልማት እንደሚያገኙ የሚገልጹ አጓጊ ልጥፎችን የያዙ ናቸው።

ከMFC የቴሌግራም ግሩፖቹን በተመለከተ ጥያቄ የቀረበለት ማስተር አብነት ከቲክቶክፌስቡክ እና የዩቲውብ ቻናል ውጪ ምንም አይነት የቴሌግራም ግሩፕ እንደሌለው ገልጿል።

በተጨማሪ MFC ባደረገው ማጣራት “Master Abenet Kebede”  የተባለው የቴሌግራም ግሩፑ የካቲት 23 እና 24 2015 ዓ/ም ስያሜውን ወደ “Safaricom ሳፋሪኮም”  በመለወጥ ተመሳሳይ ተግባር ፈጽሟል

ቲክቶክ ላይ ከ2.6 ሚሊየን በላይ ፣ ፌስቡክ ላይ 704ሺ ተከታዮች እንዲሁም ዩቲውብ ላይ ከ172ሺ በላይ ሰብስክራይበሮች ባሉት እና በበጎ አድራጎት ስራዎቹ በሚታወቀው ማስተር አብነት ስም ተመሳስለው የተከፈቱት እነዚህ የቴሌግራም ግሩፖች የተለያዩ ሽልማቶችን መስጠታቸውን ለመግለጽ የገንዘብ ዝውውር የተደረገበት በሚል የተቀናበሩ የንግድ ባንክ የሞባይል ባንኪንግ ገንዘብ ዝውውር መግለጫ ምስሎችን እንደሚጠቀሙ MFC አረጋግጧል።

ከታች በምስሉ ላይ እንደሚታየው ትክክለኛው የንግድ ባንክ የሞባይል ባንኪንግ ገንዘብ ዝውውር መግለጫ የጽሁፍ ፎንት እና በቴሌግራም ግሩፑ ለሽልማት የተከፈለ በሚል የቀረበው የገንዘብ ዝውውር መግለጫ ተመሳሳይ አይደለም።

በመሆኑም ከ130 ሺ በላይ አባላት ያሉትን ጨምሮ በማስተር አብነት ስም የተከፈቱት የቴሌግራም ግሩፖች በየማስተር አብነት ከበደ  አለመሆናቸውን MFC አረጋግጧል።

MFC ከዚህ ቀደም የታዋቂ ሰዎችን ማንነት በማስመሰል የቴሌግራም ግሩፖችን በመክፈት ይጠቀም የነበረ ማንነቱ እንዳይገለጽ የጠየቀ ግለሰብን በጉዳዩ ላይ ያነጋገረ ሲሆን ግሩፖቹ በዋነኛነት ለሁለት አላማ እንደሚውሉ ተናግሯል።

የመጀመሪያው የግሩፑ አባላት ቁጥር ሲያድግ ለሽያጭ ማቅረብ ሲሆን ሁለተኛው የቴሌግራም ግሩፑ በታዋቂው ሰው ማንነት የአባላት ቁጥሩ እንዲያድግ ከተደረገ በኋላ ስያሜውን በመቀየር የተለያዩ እቃዎችን መሸጫ እንደሚሆንም ገልጾልናል።

We at the MFC strive to verify misleading and false claims so that people get fact-based information and make an informed decision as well. In the process of our work, accuracy and transparency hold a central role. Therefore, if you see errors in our content, please write to us at [email protected] so that our team will make corrections.

Share post on Social media

See related posts

Akkawuntiin TikTooki tokko viidiyoo “misooma koridaraa finfinetti” jedhu qoode. Viidiyoon akkawuntii TikTookii kun qoode taatee
Fuulli feesbuukii tokko barreffama ‘’Aangoo qeerroo: Diinonni keenya qabeenya biyyaa balleessaa jiru. Duguuggaa sanyii raawwachuuf

ABOUT MFC

MultiFactCheck

(MFC) is an independent fact-checking organization which is launched to pin-point, track-down, scrutinize, investigate, interrogate, publish and distribute the factual accuracy of claims made by public figures. MFC’s project has geographical priorities. Our work mainly focuses on nations in the Horn of Africa and their diaspora community who reside abroad. We operates from various regions of Africa, Europe and North America. Through a multitude of professional proficiency, MFC deploys best practices of journalism, scholarship and expertise in order to flag, investigate and publish a fact.