ሐሰት ፦ ምስሎቹ በዚህ ሳምንት የጦር መሳሪያዎች በፋኖ ኃይሎች መማረካቸውን አያሳዩም

በናኦል ጌታቸው

ቀድሞ ትዊተር በተሰኘውና X በተባለው የማህበራዊ ሚዲያ መድረክ ከ18,500 በላይ ተከታዮች ያሉት “የአማራ ፋኖ ጠቅላይ እዝ Official Page!” የተባለዉ አካውንት “ሰበር ዜና! በጎጃም ዕዝ አስደናቂ ጀብዶችን ፈፅመናል! ለ3ቀን በሰነበተው የጎጃም ውጊያ በቲሊሊ፣ በቋሪት፣ ደጋ ዳሞት የአገዛዙን ጦር በመበተን እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተተኳሾችን በመማረክ 1 ዙ23 አቃጥለን በርካታ የቡድን መሳሪያዎችን ማርከናል” የሚልን ልጥፍ (post) ከሁለት ምስሎች ጋር ፤ በየካቲት 13, 2016 ዓ.ም. ለጥፏል። ይህ ፅሁፍ እስከወጣበትም ቀን ድረስ ትዊቱ ከ15,500 በላይ ተመልካች ሲያገኝ ከ100 ጊዜ በላይም ተጋርቷል (ምስሎቹን ታች ከሚታየዉ ስክርንሾት ይመልከቱ)

ይሁን እንጂ ፤ ምስሎቹ የቆዩ እና ከዚህ ቀደም አገልገሎት ላይ የዋሉ ከመሆናቸውም በተጨማሪ በወቅቱ ያለውን የአማራ ክልል ግጭት አያሳዩም። በመሆኑም ልጥፉ ሐሰት ነው።

MultiFactCheckም ልጥፉን የመረመረ ሲሆን ምስሎቹ ፅሁፉን የማይደግፉ ሆኖም አግኝቷቸዋል።

የመጀመሪያው ምስል 

የጎግል ምስል ማፋለጊያ (Google reverse image search) ውጤት ምስሉ በዚሁ አካውንት ከሳምንታት በፊት የካቲት 1 ፣ በሸዋ ምንጃር ውስጥ የተማረከ መሳሪያ ተደርጎ ተለጥፎ ነበር። እንደገናም በቅርቡ የካቲት 18ም “በሸዋ መንዝና ጅሩ” የተማረከ መሣሪያ በሚል ልጥፍ ጋር አብሮ ተጋርቷል።

ሁለተኛው ምስል

የጎግል ምስል ማፋለጊያ (Google reverse image search) ውጤት እንደሚያመለክተው ሁለተኛው ምስል ለመጀመሪያ ጊዜ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተጋራው በፌስቡክ ላይ ጥቅምት 18, 2014 ዓ.ም. ሲሆን ይህም ይህ የአማራ ክልል ግጭት ከመከሰቱ ከአመት በፊት ነው። ምስሉም በተመሳሳይ ቀን በተለያዩ ገፆችም ተጋርቷል። (በዚህ ማስፈንጠሪያ እና በዚህ ማስፈንጠሪያ ተጠቅመው መመልከት ይችላሉ።)

በመሆኑም MultiFactCheck ልጥፉን መርምሮ ምስሎቹ ፤ የፋኖ ኃይሎች መሳሪያዎችን ከመከላከያ ሰራዊት ጎጃም ውስጥ በተጠቀሰው ቀን ስለመማረካቸው እንደማያሳዩ እና ሐሰት መሆናቸውን አረጋግጧል።

በአማራ ክልል ያለው ግጭት በመንግስትና ራሳቸውን “ፋኖ” ብለው በሚጠሩ የክልሉ አማፂ ኃይሎች መካከል በሚያዝያ 2015 የተጀመረ ነው።

የግጭቱም ዋነኛ መንስኤ ተደርጎ የሚወሰደው የፌዴራሉ መንግስት የክልል ልዩ ኃይሎችን ትጥቅ አስፈታለሁ በማለቱና በክልሉ ያሉ ኃይሎች ውሳኔውን ባለመቀበላቸው ነው። ይህም በጦር መሳሪያ የተደገፈ ግጭት/ጦርነት በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች አሁን ድረስ የቀጠለ ሲሆን ፤ ከላይ የጠቀስነውም ትዊት በዚህ አውድ ውስጥ የተዘዋወረ ነው።

We at the MFC strive to verify misleading and false claims so that people get fact-based information and make an informed decision as well. In the process of our work, accuracy and transparency hold a central role. Therefore, if you see errors in our content, please write to us at [email protected] so that our team will make corrections.

Share post on Social media

See related posts

Akkawuntiin TikTooki tokko viidiyoo “misooma koridaraa finfinetti” jedhu qoode. Viidiyoon akkawuntii TikTookii kun qoode taatee
Fuulli feesbuukii tokko barreffama ‘’Aangoo qeerroo: Diinonni keenya qabeenya biyyaa balleessaa jiru. Duguuggaa sanyii raawwachuuf

ABOUT MFC

MultiFactCheck

(MFC) is an independent fact-checking organization which is launched to pin-point, track-down, scrutinize, investigate, interrogate, publish and distribute the factual accuracy of claims made by public figures. MFC’s project has geographical priorities. Our work mainly focuses on nations in the Horn of Africa and their diaspora community who reside abroad. We operates from various regions of Africa, Europe and North America. Through a multitude of professional proficiency, MFC deploys best practices of journalism, scholarship and expertise in order to flag, investigate and publish a fact.