ቪዲዮው ‘ዘመቻ ውብአንተ’ በአዲስ አበባ መጀመሩን አያሳይም

በናኦል ጌታቸው

የተጠቀሰው መረጃ: Amhara Youth Association (ወይም በአማርኛ የአማራ ወጣቶች ማህበር) የተባለ እና በርካታ ተከታዮች ያሉት የX አካውንት “ዘመቻ ውባንተ” በአዲስ አበባ መጀመሩን ከቪዲዮ ጋር ትዊት አድርጓል። 

ብያኔ: የተለጠፈው ቪዲዮ የቆየ እና ከአሁኑ የአማራ ክልል ግጭት ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው በመሆኑ ሐሰት ነው። 

Amhara Youth Association (ወይም በአማርኛ የአማራ ወጣቶች ማህበር) የሚል ስም ያለውና ከ 36,000 በላይ ተከታዮች ያሉት የX አካውንት, አዲስ አበባ “ዘመቻ ውባንተ” እየተባለ የሚጠራን የውጊያ ዘመቻ መቀላቀሉን የያዘ ትዊት ቪዲዮ አያይዞ በመጋቢት 13/2016  አጋርቷል። ይህም ልጥፍ ይህ ፅሁፍ እስከሚታተምበት ዕለት ድረስ ከ 25,000 በላይ ዕይታ ያገኘ ሲሆን ከ110 ጊዜ በላይም በድጋሚ ተጋርቷል።

ከቪዲዮው ጋር የተያያዘው ፅሑፍም እንዲህ ይነበባል። “ዘመቻ ውብአንተ በአዲስ አበባ ተጀመረ! በመጨረሻም ቢሆን የፒያሳ ወጣቶች ከእንቅልፋቸው እየነቁ ነው። ተቃውሞ እየተቀጣጠለ ነው። አንድ ባለስልጣናት የሚንቀሳቀሱበት አውቶቡስ ላይ የቦንብ ጥቃት መድረሱን አረጋግጠናል”

ይሁን እንጂ ፤ (MultiFactCheck (MFC) የተጠቀሰውን መረጃ እውነተኝነት Fake news debunker by InVID & WeVerifyን በመጠቀም አጣርቷል። ውጤቱም እንደሚያሳየው ቪዲዮው መስከረም 4/2011 ዓ.ም የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮች ወደሐገር ውስጥ በሚመለሱበት ወቅት “ቄሮ” እየተባሉ በሚጠሩ የኦሮሞ ወጣቶችና በአዲስ አበባ ወጣቶች መሐከል የተፈጠረውን ግጭት ከሚያሳየው ቪዲዮ ላይ የተወሰደ ሲሆን ፤ በትዊተር ላይ እንደተሰራጨው በዚህ ጊዜ ከሚካሄደው የአማራ ክልል ግጭት ጋር የሚያያዝ አይደለም።

ከአምስት አመት በፊት የነበረን ክስተት የሚያሳየው ይህ ቪዲዮ በዕለቱ መስከረም 4/2011 ዓ.ም ፌስቡክን (ይህንን መስፈንጠሪያ ይመልከቱ ) እና ዩቲዩብን (ይህንን መስፈንጠሪያ ይመልከቱ) ጨምሮ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ሲሰራጭ ነበር።

በመሆኑም ፤ MFC የተጠቀሰው መረጃ ሐሰት መሆኑን አረጋግጧል።

አውድ

የአማራ ክልል ካለፈው ዓመት ሰኔ ጀምሮ በግጭትና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ ይገኛል። በዚህም የመንግስትና ራሳቸውን “ፋኖ” ብለው በሚጠሩ ታጣቂ ኃይሎች መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት ፣ ውብአንተ አባተ የተባለና ከፋኖ ኃይሎች መሪዎች አንዱ የሆነው መገደሉ ሲዘገብ ቆይቷል።

ከዚህም ጋር ተያይዞ ታጣቂዎቹ በዚሁ መሪያቸው ስም የተሰየመ የውጊያ ዘመቻ መጀመራቸውን በየማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲያጋሩ ይስተዋላል። ይህም ከላይ የተጠቀሰው መረጃም በዚህ አውድ ውስጥ የተሰራጨ ነው።

We at the MFC strive to verify misleading and false claims so that people get fact-based information and make an informed decision as well. In the process of our work, accuracy and transparency hold a central role. Therefore, if you see errors in our content, please write to us at [email protected] so that our team will make corrections.

Share post on Social media

See related posts

Fuulli feesbuukii tokko barreffama ‘’Aangoo qeerroo: Diinonni keenya qabeenya biyyaa balleessaa jiru. Duguuggaa sanyii raawwachuuf
የሲቪል አቬሽን ህግ በመጣስ እና በሽብር ወንጀል የተከሰሰው ዮሐንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል) ከእስር መለቀቁን የሚገልጽ

ABOUT MFC

MultiFactCheck

(MFC) is an independent fact-checking organization which is launched to pin-point, track-down, scrutinize, investigate, interrogate, publish and distribute the factual accuracy of claims made by public figures. MFC’s project has geographical priorities. Our work mainly focuses on nations in the Horn of Africa and their diaspora community who reside abroad. We operates from various regions of Africa, Europe and North America. Through a multitude of professional proficiency, MFC deploys best practices of journalism, scholarship and expertise in order to flag, investigate and publish a fact.