ቪዲዮው በባህር ዳር የተደረገን የድሮን ጥቃት አያሳይም

በናኦል ጌታቸው

የተጠቀሰው መረጃ፦ አንድ በእሳት የተያያዘን ህንፃ የሚያሳይ ቪዲዮ “ፋኖን ሰበብ በማድረግ በባህር ዳር ከተማ የተደረገ የድሮን ጥቃት” ከሚል ፅሁፍ ጋር በቲክቶክና በX (ትዊተር) ላይ በባህርዳር ከተማ የተከሰተ ተደርጎ ተዘዋውሯል።

ብያኔ፦ MultiFactCheck (MFC) ባደረገው ማጣራት ቪዲዮው ከሁለት አመት በፊት በአዲስ አበባ የተከሰተ የእሳት አደጋ እንጂ በባህር ዳር የተከሰተ የድሮን ጥቃትን የሚያሳይ ባለመሆኑ ሐሰት ሲል ሁለቱን ይዘቶች በይኗቸዋል።

Zemedkun Bekele በሚል ስም የተከፈተና ከ28,300 በላይ ተከታዮች ያሉት የቲክቶክ አካውንት አንድ ህንፃ የእሳት አደጋ የደረሰበት እና እሳቱን በውሃ እያጠፉ የሚታዩ የእሳት አደጋ ሰራተኞችን የሚያሳየን ቪዲዮ “ፋኖን ሰበብ በማድረግ በባህር ዳር ከተማ የተደረገ የድሮን ጥቃት” ከሚል ፅሁፍ ጋር አያይዞ በየካቲት 28/2016 በስክሪንሾቱ በሚታየው መልኩ አጋርቷል። ቪዲዮውም ከ159,000 ጊዜ በላይ ዕይታ ያገኘ ሲሆን ፤ ከ3,700 ጊዜ በላይም ተጋርቷል። 

በተመሳሳይ ይህንኑ ቪዲዮ Elizabeth Altaye የሚል ስም ያለው እና ከ17,900 በላይ ተከታዮች ያሉት የX (በቀድሞው ትዊተር) አካውንት “ባህር ዳር “ ከሚል ፅሁፍ ጋር ትዊት አድርጓል። ትዊቱም ከ19,000 በላይ ዕይታና ከ230 በላይ ጊዜ ሪትዊት አግኝቷል።

ይሁን አንጂ MFC የመረጃውን እውነተኝነት ለማረጋገጥ ከቪዲዮው ስክሪንሾቶችን በመውሰድ ፤ በጎግል ምስል ማፋለጊያ ማጣራት አድርጓል። በመሆኑም ተመሳሳይ ቪዲዮዎች በጥቅምት 21/2014 ዓም. መጋራታቸውን ለመረዳት ተችሏል። (እነዚህን ማስፈንጠሪያዎች ተጠቅመው ይመልከቱ። ) 

በተጨማሪም እንደ Addis Media Network እና ፋና ያሉ የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች በወቅቱ የዘገቡትን ዘገባዎች ጭምር ተመልክቷል። 

ይህ ከሁለት አመት በፊት የተከሰተው የእሳት አደጋ በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ መሳለሚያ እህል በረንዳ በሚባለው አካባቢ “አማኑኤል ፀጋ” በተባለ ባለአራት ወለል ህንፃ ላይ የተከሰተ ነው። 

ከሁለት አመት በፊት የእሳት አደጋ እንደደረሰበት የተዘገበው የ”የአማኑኤል ፀጋ የንግድ ማዕከል” ምስል – ከAMN የተወሰደ

በተጨማሪም ከአዲስ አበባ እሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ባገኘነው መረጃ መሠረት ምስሉ ከሁለት አመት በፊት የተከሰተን የእሳት አደጋ የሚያሳይ መሆኑን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ንጋቱ ማሞ ለMFC አረጋግጠዋል።

በመሆኑም የቲክቶክ አካውንቱ በጠቀሰው መሠረት ክስተቱ በባህር ዳር ከተማ የደረሰ የድሮን ጥቃት ሳይሆን ፤ ከአመታት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ የደረሰ የእሳት አደጋ መሆኑን በማረጋገጡ MFC በዚህ ሰሞን የተዘዋወሩትን እነዚህን ይዘቶች ሐሰት ሲል በይኗቸዋል። 

በአማራ ክልል ያለው ግጭት በመንግስትና ራሳቸውን “ፋኖ” ብለው በሚጠሩ የክልሉ አማፂ ኃይሎች መካከል በሚያዝያ 2015 የተጀመረ ነው።

የግጭቱም ዋነኛ መንስኤ ተደርጎ የሚወሰደው የፌዴራሉ መንግስት የክልል ልዩ ኃይሎችን ትጥቅ አስፈታለሁ በማለቱና በክልሉ ያሉ ኃይሎች ውሳኔውን ባለመቀበላቸው ነው።

We at the MFC strive to verify misleading and false claims so that people get fact-based information and make an informed decision as well. In the process of our work, accuracy and transparency hold a central role. Therefore, if you see errors in our content, please write to us at [email protected] so that our team will make corrections.

Share post on Social media

See related posts

Fuulli feesbuukii tokko barreffama ‘’Aangoo qeerroo: Diinonni keenya qabeenya biyyaa balleessaa jiru. Duguuggaa sanyii raawwachuuf
የሲቪል አቬሽን ህግ በመጣስ እና በሽብር ወንጀል የተከሰሰው ዮሐንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል) ከእስር መለቀቁን የሚገልጽ

ABOUT MFC

MultiFactCheck

(MFC) is an independent fact-checking organization which is launched to pin-point, track-down, scrutinize, investigate, interrogate, publish and distribute the factual accuracy of claims made by public figures. MFC’s project has geographical priorities. Our work mainly focuses on nations in the Horn of Africa and their diaspora community who reside abroad. We operates from various regions of Africa, Europe and North America. Through a multitude of professional proficiency, MFC deploys best practices of journalism, scholarship and expertise in order to flag, investigate and publish a fact.