Search
Close this search box.

ቀይ መስቀል ማኀበር ለፋኖ የምስጋና ደብዳቤ እንደላከ ተደርጎ የተሰራጨው ምስል በፎቶሾፕ የተቀናበረ ነው

በናኦል ጌታቸው

የተጠቀሰው መረጃ፦ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ለፋኖ ታጣቂ ኃይል የምስጋና ደብዳቤ እንደላከ የሚገልፅ የደብዳቤ ፎቶ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ተሰራጭተዋል። 

ብያኔ፦ ምስሉ በፎቶሾፕ የተቀናበረ በመሆኑ የተጠቀሰው መረጃ ሐሰት ነው።

AmharaAquila የሚል ስም ያለው እና ከ16,000 በላይ ተከታዮች ያሉት የX አካውንት “የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ለፋኖ አድናቆቱን ገለፀ” የሚል ትርጉም ያለው የእንግሊዘኛ ፅሁፍ ከምስል ጋር በመጋቢት 26/ 2016 ዓ.ም. ለጥፏል። 

ከተጠቀሰው የX ፖስት ላይ በሚያዝያ 2 የተወሰደ ስክሪንሾት

ይህም ፖስት ከ140 ጊዜ በላይ ተደጋግሞ የተጋራ ሲሆን ከ12,100 በላይ ዕይታም አግኝቷል።

በተጨማሪም ይኸው ምስል በቲክቶክ ላይ የተሰራጨ ሲሆን ፤ ከ1,200 ጊዜ በላይ ተጋርቶ ከ30,000 በላይ ዕይታዎችም አግኝቷል። 

በተመሳሳይም ምስሉ በፌስቡክ ላይ በተለያዩ አካውንቶች አማካይነት የተዛመተ መሆኑን ለማየት ተችሏል። (ለአብነትም ይህንንይህንንይህንን እና የመሳሰሉትን መስፈንጠሪያዎች ይመልከቷቸው።)

ይሁን እንጂ ምስሉ [በፎቶሾፕ] የተቀናበረ በመሆኑ እና ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል በተገኘው መረጃ መሰረት ሐሰት መሆኑ ተረጋግጧል። 

Invid Forensicን በመጠቀም MultiFactCheck (MFC) ምስሉን የመረመረ ሲሆን ከታች በምትመለኩት መልኩ በፎቶሾፕ የተቀናበሩ ቦታዎችን አመልክተዋል። 

ምስሉን በInVID we verify መሳሪያ ምስሎች በፎቶሾፖች መቀናበራቸውን በሚመረምረው Forensic ሲመረመር የተገኘውን ውጤት በመጋቢት 2 የተወሰደ ስክሪንሾት ፤ ምስሉም በውኃ ሰማያዊ ቀለም ምልክት ያደረገባቸው በፎቶሾፕ መጨመራቸው የሚገልፅ ነው።

ከዚህም በተጨማሪም MFC የቀይ መስቀል ማህበር የበጎ አድራጎት ፣ ዲፕሎማሲና ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ የሆኑትን አቶ መስፍን ደጀኔን በስልክ ያነጋገረ ሲሆን “ምስሉ ፎቶሾፕ ተሰርቶ ነው። [በደብዳቤው ላይ የተጠቀሰው] ሰውየው በሌላ ዲፓርትመንት ውስጥ የሚሰራ ነው። እንደዚህ አይነት ደብዳቤ የመፃፍ ማንዴትም [ስልጣንም] የለንም” ሲሉ አረጋግጠውልናል። 

በተያያዘም የተሰራጨውን ደብዳቤ ለማጤን ብንሞክር የሚከተሉትን ሁነቶች ለማስተዋል እንችላለን። 

  1. ከታች በምስሉ ላይ እንደተመላከተው ይፋዊ ደብዳቤዎች ሲፃፉ የማይስተዋሉ ስህተቶቾን መመልከታችን በችኮላ ከሚሰሩ የሀሰት ፎቶሾፕ ምስሎች አንዱ እንደሆነ ለመገንዘብ ይረዳናል። ለአብነትም፦
    • በቀይ ያሰመርንባቸውን ስንመለከት ፣ በቃላት መካከል ሊኖር የሚገባ ክፍተት ባለመጠቀምና ሁለት ቃላትን በተደጋጋሚ አያይዞ መፃፍ 
    • በሰማያዊ የተሰመረባቸውን ስንመለከት ፣ ተደጋጋሚ የቃላት ስህተቶች
    • በአረንጓዴ የተሰመረባቸውን ስንመለከት ፣ ተቋማት የማይጠቀሟቸው ያልተመረጡ ቃላትና የፊደል መረጣ ስህተትን ለማስተዋል ይቻላል።
  2. በቀስቱ የተመላከቱትን ስንመለከት ፣ ፕሮፌሽናል ደብዳቤዎች ሲፃፉ የሚከተሉትን አንድ ወጥ ፎንት የመጠቀምን ስርዓት ያልተከተለና የተዘበራረቀ የፎንት አጠቃቀም ፣ ተገቢ ያለሆነ የአንቀፅ አጠቃቀምን ልብ ለማለት እንችላለን።
  1. በአማርኛ ለሚፃፍ ደብዳቤ በእንግሊዘኛ የህዳግ ስምና የመልካም ምኞት መፃፉም አስቀድሞ በእንግሊዘኛ የተዘጋጀን የቆየ ደብዳቤ በፎቶሾፕ አርትኦት ለመሰራቱ እንደመረጃ ግብዓት ይሆናል።

በመሆኑም MFC የተጠቀሰውን ምስል እውነተኝነት በማጣራት ሂደት ውስጥ በInVID መሳሪያ ፣ በተቋሙ ኃላፊ የምስክር ቃል እና ተጨማሪ በተደረገው ምርመራ መረጃውን ሐሰት ሲል በይኖታል።  

የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችም መሰል መረጃዎችን ሲመለከቱ ፈጥኖ ከማመንና ከማጋራት በፊት የመረጃውን እውነተኝነት ለማጣራት መረጃውን በትኩረት እንዲመለከቱ እንዲሁም ወደ ተጠቀሰው ተቋም ይፋዊ ድረ ገፅ በመሄድ እንዲያጣሩ እንመክራለን።

We at the MFC strive to verify misleading and false claims so that people get fact-based information and make an informed decision as well. In the process of our work, accuracy and transparency hold a central role. Therefore, if you see errors in our content, please write to us at [email protected] so that our team will make corrections.

Share post on Social media

See related posts

ጎንደር ላይ ፋኖን የሚቃወም ሰልፍ እንደተደረ የሚገልጽ ጽሁፍ ከቪዲዮ መረጃ ጋር በ “X” ማህበራዊ ሚዲያ

ABOUT MFC

MultiFactCheck

(MFC) is an independent fact-checking organization which is launched to pin-point, track-down, scrutinize, investigate, interrogate, publish and distribute the factual accuracy of claims made by public figures. MFC’s project has geographical priorities. Our work mainly focuses on nations in the Horn of Africa and their diaspora community who reside abroad. We operates from various regions of Africa, Europe and North America. Through a multitude of professional proficiency, MFC deploys best practices of journalism, scholarship and expertise in order to flag, investigate and publish a fact.

Follow Us