ሐሰት ፦ ምስሉ የጎጃም መንገድ መዘጋቱን አያሳይም

በናኦል ጌታቸው

ግርማ አየለ (Girma Ayele GA) የተሰኘዉ ፣ ፌስቡክ ላይ ከ2,500 በላይ ተከታይ ያለው ግለሰብ፣ አንድ ምስል የያዘ ልጥፍ (post) በማያያዝ “ጎጃም መንገዱን ጥርቅም ነው” ከሚል ገለፃ ጋር አጋርቷል። ይህ ከአማራ ክልል ግጭት ጋር በተያያዘ በጎጃም መንገዶች በድንጋይ መዘጋታቸውን የሚገልፀውና የካቲት 17/2016 ዓ.ም. የተጋራው ልጥፍ ይህ ፅሁፍ እስከሚወጣበት ቀን ድረስ ከ44 በላይ ጊዜ ሲጋራ ከ577 በላይ ግብረ መልሶችም አግኝቷል  (ምስሉን ታች ከሚታየዉ ስክርንሾት ይመልከቱ)።

ይሁን እንጂ ምስሉ የቆየ እና ከአራት አመታት በፊት ጥቅም ላይ የዋለ በመሆኑ ፤ እንዲሁም ከወቅቱ የአማራ ክልል ጦርነት ጋር ተያያዥነት ያለው ባለመሆኑ ልጥፉ ሐሰት ነው።

MultiFactCheckም ልጥፉን የመረመረ ሲሆን ምስሉ ፅሁፉን የማይደግፍ ሆኖም አግኝቶታል።

የጎግል ምስል ማፋለጊያ (Google reverse image search) ውጤት እንደሚያሳየው ምስሉ ከአራት አመታት በፊት በኦሮሚያ በነበረዉ ተቃውሞ በጥቅምት 12/2012 ዓ.ም. በፌስቡክ ላይ “#Ambo gaafa xiiqii” ወይም “#አምቦ በተቃውሞ ጊዜ” በሚል ፅሁፍ  ተጋርቷል። 

በመሆኑም MultiFactCheck ልጥፉን መርምሮ ምስሉ የቆየ እና ከወቅቱ የአማራ ክልል ግጭት ጋር የማይያያዝ መሆኑን ያረጋገጠ ሲሆን ፤ በልጥፉ እንደተገለፀውም “ጎጃምን መንገድ መዘጋት” የማያሳይ በመሆኑ ሐሰት ብሎታል።

በመንግስትና ራሳቸውን “ፋኖ” ብለው በሚጠሩ የክልሉ ታጣቂ ኃይሎች መካከል ከሚያዝያ 2015 ጀምሮ በአማራ ክልል በመሳሪያ የተደገፈ ጦርነት መኖሩ ይታወቃል።

የፌዴራሉ መንግስት የክልል ልዩ ኃይሎችን ትጥቅ ለማስፈታት የወሰነውን ውሳኔ ባልተቀበሉ የአማራ ክልል ኃይሎች ከመንግስት ጋር እያደረጉት ያለው ጦርነትም ቀጥሎ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች እየተደረገ ሲሆን ፤ ከላይ የጠቀስነውም ትዊት በዚህ አውድ ውስጥ የተዘዋወረ ነው።

We at the MFC strive to verify misleading and false claims so that people get fact-based information and make an informed decision as well. In the process of our work, accuracy and transparency hold a central role. Therefore, if you see errors in our content, please write to us at [email protected] so that our team will make corrections.

Share post on Social media

See related posts

Akkawuntiin TikTooki tokko viidiyoo “misooma koridaraa finfinetti” jedhu qoode. Viidiyoon akkawuntii TikTookii kun qoode taatee
Fuulli feesbuukii tokko barreffama ‘’Aangoo qeerroo: Diinonni keenya qabeenya biyyaa balleessaa jiru. Duguuggaa sanyii raawwachuuf

ABOUT MFC

MultiFactCheck

(MFC) is an independent fact-checking organization which is launched to pin-point, track-down, scrutinize, investigate, interrogate, publish and distribute the factual accuracy of claims made by public figures. MFC’s project has geographical priorities. Our work mainly focuses on nations in the Horn of Africa and their diaspora community who reside abroad. We operates from various regions of Africa, Europe and North America. Through a multitude of professional proficiency, MFC deploys best practices of journalism, scholarship and expertise in order to flag, investigate and publish a fact.