Amharic Archives - MultiFactCheck https://multifactcheck.org/tag/amharic/ Shed Light on the Truth. Mon, 02 Sep 2024 15:21:58 +0000 en-US hourly 1 https://wordpress.org/?v=6.7.1 https://multifactcheck.org/wp-content/uploads/2021/07/cropped-multifactcheck-1-150x150.jpeg Amharic Archives - MultiFactCheck https://multifactcheck.org/tag/amharic/ 32 32 እያንዳንዷን ችግኝ ያረፈበትን ቦታ የሚያሳይ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ተደርጓል? https://multifactcheck.org/%e1%8a%a5%e1%8b%ab%e1%8a%95%e1%8b%b3%e1%8a%95%e1%8b%b7%e1%8a%95-%e1%89%bd%e1%8c%8d%e1%8a%9d-%e1%8b%ab%e1%88%a8%e1%8d%88%e1%89%a0%e1%89%b5%e1%8a%95-%e1%89%a6%e1%89%b3-%e1%8b%a8%e1%88%9a%e1%8b%ab/ Tue, 27 Aug 2024 18:05:08 +0000 https://multifactcheck.org/?p=8416 በፋሲል አረጋይ የተጠቀሰው መረጃ፡ ኢቢሲ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ በ2016 የችግኝ መርሃ ግብር እያንዳንዷ ችግኝ ያረፈችበትን ቦታ መለየት የሚያስችል ቴክኖሎጂ ተግባራዊ መደረጉን ዘግቧል ብያኔ፡  የቀረበው ዜና አሳሳች ሲሆን ችግኝ የተተከለባቸውን አጠቃላይ ስፍራዎችን መለየት የሚያስችል በካርታ የማካለል ስራ ብቻ ነው የተደረገው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ነሃሴ 17 ቀን 2016 በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ በኩል “እያንዳንዷ ችግኝ ያረፈችበትን ቦታ […]

The post እያንዳንዷን ችግኝ ያረፈበትን ቦታ የሚያሳይ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ተደርጓል? appeared first on MultiFactCheck.

]]>
በፋሲል አረጋይ

የተጠቀሰው መረጃ፡ ኢቢሲ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ በ2016 የችግኝ መርሃ ግብር እያንዳንዷ ችግኝ ያረፈችበትን ቦታ መለየት የሚያስችል ቴክኖሎጂ ተግባራዊ መደረጉን ዘግቧል

ብያኔ፡  የቀረበው ዜና አሳሳች ሲሆን ችግኝ የተተከለባቸውን አጠቃላይ ስፍራዎችን መለየት የሚያስችል በካርታ የማካለል ስራ ብቻ ነው የተደረገው

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ነሃሴ 17 ቀን 2016 በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ በኩል “እያንዳንዷ ችግኝ ያረፈችበትን ቦታ መለየት የሚያስችል ቴክኖሎጂ ተግባራዊ  መደረጉ ተገለጸ” የሚል ዜና አጋርቷል

መረጃው ይህ ጽሑፍ ለንባብ እስከበቃበት ጊዜ ድረስ 3300 (ሶስት ሺህ ሶስት መቶ) ግብረ መልስ ሲያገኝ 808 (ስምንት መቶ ስምንት) አስተያየት ተሰጥቶበታል። እንዲሁም ለሌሎች የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ተደራሽ እንዲሆን 124 (አንድ መቶ ሃያ አራት) ጊዜ ተጋርቷል።

MFC ባካሄደው ዳሰሳ ከ10 በላይ የዜና ማሰራጫ የፌስቡክ ገጾች ሙሉ ዜናውን በመውሰድ ለተከታዮቻቸው ተደራሽ እንዲሆን ለጥፈዋል። የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችም በዜናው ልጥፍ አስተያየት መስጫ ስር መረጃው እንዲጣራ ጠይቀዋል።

በመሆኑም MFC በዚህ አመት በተከናወነው የ”አረንጓዴ አሻራ” ችግኝ የመትከል መርሃ ግብር እያንዳንዷ ችግኝ ያረፈችበትን ቦታ መለየት የሚያስችል ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ተደርጓል? የሚለውን ጥያቄ በመያዝ የማጣራት ስራ አድርጓል።

ማንነታቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ኃላፊ ጉዳዩን በተመለከተ ዝርዝር ሙያዊ ማብራሪያ ለMFC ሰጥተዋል።

“የዜናው ርዕስ የቀረበበት መንገድ ስህተት ነው” ያሉት ኃላፊው “በዜናው መጨረሻ ላይ 8454 (ስምንት ሺህ አራት መቶ ሃምሳ አራት) ቦታዎች በካርታ መለየቱን ይገልጻል ፥ ይህም ማለት ለምሳሌ መስቀል አደባባይ አካባቢ የተተከለ ሳይት ካለ ሙሉ ሳይቱ Map ተደርጓል ማለት ነው” ብለዋል።

“ቴክኒካል በሆነ መንገድ የእያንዳንዱን ችግኝ ሎንግቲውድ እና ላቲቲውድ መዝግቦ Map ማድረግ የሚቻል ቢሆንም እንደዛ አልተደረገም ከፍተኛ ወጪም ይጠይቃል” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

“በዜናው ላይ ለማለት የተፈለገው የተተከለበት ቦታ ከዚህ በፊት እንደነበረው እዚህ ቦታ ተተክሏል ብቻ ሳይሆን ጆኦ ሪፈራል ተደርጓል ማለትም የት የት እንደተተከሉ ካርታ ላይ ማወቅ ይቻላል’ በማለት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት በይፋ አረንጓዴ አሻራ በሚል ንቅናቄ የችግኝ ተከላ የጀመረው በ 2011 ዓ/ም ሲሆን የ 2016 ዓ/ምን ሳይጨምር በድምሩ 22 ቢሊየን 500 ሚሊየን ችግኝ እንደተተከለ ይገልጻል። መንግስት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩ በ 2011 ከተተከሉ ችግኞች ከ83 በመቶ በላይ እንዲሁም በ2012 ከተተከሉት 79 በመቶ የሚሆኑት መጽደቃቸውን ቢገልጽም ገለልተኛ ዓለም አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ጥናት ተቋማት አይስማሙ።

ተቀማጭነቱን በእንግሊዝ ሀገር ለንደን ያደረገው International Institute for Environment and Development (IIED) ባልደረባ የሆኑት ጄምስ ሜይርስ “በመንግስት የቀረቡት አሃዞች አስተማማኝ አይደሉም ፥ ችግኞች ከተተከሉ በኋላ ስላለው ሁኔታ መከታተል የሚያስችል ዘዴ መዘጋጀት አለበት” ብለዋል (ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎች ከBBC አማርኛ እዚህ ይመልከቱ)።

The post እያንዳንዷን ችግኝ ያረፈበትን ቦታ የሚያሳይ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ተደርጓል? appeared first on MultiFactCheck.

]]>
በጋዜጠኛ መሳይ የተሰራጨው ምስል የአማራ አርሶ አደሮችን ያሳያል? https://multifactcheck.org/%e1%89%a0%e1%8c%8b%e1%8b%9c%e1%8c%a0%e1%8a%9b-%e1%88%98%e1%88%b3%e1%8b%ad-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%88%b0%e1%88%ab%e1%8c%a8%e1%8b%8d-%e1%88%9d%e1%88%b5%e1%88%8d-%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%88%9b%e1%88%ab/ Wed, 21 Aug 2024 15:28:44 +0000 https://multifactcheck.org/?p=8400 ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን “የአማራ ህዝብ ተነስቷል። የአማራ አርሶ አደር ሆ ብሎ ወጥቷል” የሚል መረጃ ከአንድ ምስል ጋር ከ224ሺ በላይ ተከታዮች ባለው የፌስቡክ ገጽ ላይ አጋርቷል። ምስሉ የቆየ ሲሆን አሁናዊ በሆነው የአማራ ክልል የትጥቅ ግጭት ላይ ለመሳተፍ  የወጣ አርሶ አደርን የሚያሳይ አይደለም።

The post በጋዜጠኛ መሳይ የተሰራጨው ምስል የአማራ አርሶ አደሮችን ያሳያል? appeared first on MultiFactCheck.

]]>
በፋሲል አረጋይ

የተጠቀሰው መረጃ፡ ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን “የአማራ ህዝብ ተነስቷል። የአማራ አርሶ አደር ሆ ብሎ ወጥቷል” የሚል መረጃ ከአንድ ምስል ጋር ከ224ሺ በላይ ተከታዮች ባለው የፌስቡክ ገጽ ላይ አጋርቷል

ብያኔ፡ ምስሉ የቆየ ሲሆን አሁናዊ በሆነው የአማራ ክልል የትጥቅ ግጭት ላይ ለመሳተፍ  የወጣ አርሶ አደርን የሚያሳይ አይደለም።

የቀድሞው ኢሳት ቴሌቭዥን ጣብያ ጋዜጠኛ እና በአሁን ሰዓት Anchor Media የተባለ የዩቲውብ ሚዲያ አዘጋጅ መሳይ መኮንን ከ224ሺ በላይ ተከታዮች ባለው የፌስቡክ ገጹ በኩል ነሐሴ 3 ቀን 2016 ዓ/ም “ይናገራል ፎቶ” የሚል ጽሑፍ ከአንድ ምስል ጋር አጋርቷል። 

ጋዜጠኛው በዚሁ ልጥፍ ላይ “ጃውሳ እያልክ አትጃጃል። ፎጤ ብለህም አትለፋደድ። የአማራ ህዝብ ተነስቷል። የአማራ አርሶ አደር ሆ ብሎ ወጥቷል” በማለት ይገልጻል።

መረጃው ይህ ጽሑፍ ለንባብ እስከበቃበት ድረስ ከሁለት ሺ ስድስት መቶ በላይ ግብረ መልስ አግኝቷል። 89 ጊዜም ለሌሎች የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ተደራሽ እንዲሆን ተጋርቷል።

በአማራ ክልል በፌደራል መንግስት የፀጥታ ኃይሎች እና የጦር መሳሪያ ታጥቀው በሚንቀሳቀሱ የፋኖ ታጣቂዎች መካከል ለአንድ አመት የዘለቀ ግጭት እንዳለ ይታወቃል  (እዚህ ያንብቡ)።

ከጋዜጠኛ መሳይ መኮንን የፌስቡክ ልጥፍ ጋር ተያይዞ የቀረበው ምስል አሁን ላይ “የአማራ አርሶ አደር ሆ ብሎ…” መውጣቱን ያሳያል? በሚለው አውድ ዙሪያ MFC የማጣራት ስራ ሰርቷል። በዚህም ከጋዜጠኛው ሃሳብ ጋር ተያይዞ የቀረበው ምስል በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለውን በጦር መሳሪያ የታገዘ ግጭት የማያሳይ አሳሳች ምስል መሆኑ ተረጋግጧል።

ምስሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በማህበራዊ ሚዲያ ጥቅም ላይ የዋለው ከ7 አመታት በፊት የካቲት 30, 2009 ዓ/ም (March 9, 2017) “ወጀራት.com” በተባለ የፌስቡክ ገጽ ላይ ነው። በተጨማሪም የፌስቡክ ገጹ በድጋሚ ምስሉን በመጋቢት 3, 2009 ዓ/ም (March 12, 2017) “የወጀራት ሽማግሌዎች ጀግኖች ፣ እምቢ ባዮች እና ልባሞች” የሚል ይዘት ካለው ግጥም ጋር አጋርቶታል (ይሄንን እና ይሄንን ይመልከቱ)። 

በተጨማሪም የጉግል ምስል ማሰሻ (Google Lens) ምስሉ በተለያየ ጊዜ በማህበራዊ ሚዲያ ለተሰራጩ መረጃዎች አባሪ ሆኖ ጥቅም ላይ እንደዋለ ያሳያል።

በመሆኑም “የአማራ ህዝብ ተነስቷል ፥ የአማራ አርሶ አደር ሆ ብሎ ወጥቷል” በሚል በጋዜጠኛ መሳይ መኮንን የተጋራው ምስል የቆየ እና በአሁኑ ሰዓት በአማራ ክልል በፌደራል የጸጥታ ኃይሎች እና በክልሉ በሚገኙ ታጣቂዎች መካከል በሚካሄደው ውጊያ ተሳታፊ ለመሆን የወጣ ህዝብን የሚያሳይ አይደለም።

የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በተለይም ደግሞ ጋዜጠኞች በማህበራዊ ትስስር ገጾቻቸው ላይ የሚያጋሯቸውን የጽሁፍ ፣ ምስል እንዲሁም ቪዲዮ መረጃዎች ከማሰራጨታቸው በፊት አስፈላጊውን የማጣራት ስራ እንዲያከናውኑ እና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመቀነስ የበኩላቸውን እንዲወጡ MFC ያሳስባል።

ባለፈው ዓመት ሚያዚያ ወር የክልል ልዩ ኃይል አደረጃጀት እንዲፈርስ እና በመደበኛ የጸጥታ መዋቅር ውስጥ ተካቶ እንዲደራጅ የፌደራል መንግስት ውሳኔ ማስተላለፉን ተከትሎ ነበር በአማራ ክልል ጦርነት የተቀሰቀሰው።

ከሀምሌ 2015 ጀምሮ የታወጀው እና በክልሉ እንዲሁም እንደ አስፈላጊነቱ በመላው ሀገሪቱ ተፈጸሚ እንዲሆን ለ10 ወራት ተግባራዊ የተደረገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ባሳለፍነው ግንቦት ወር የተፈጻሚነት ጊዜው አብቅቷል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከሰኔ 2015 እስከ ሰኔ 2016 የሀገሪቱን ሰብዓዊ መብቶችን በተመለከተ ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርት በአማራ ክልል በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በተለምዶ “ፋኖ” ተብሎ በሚታወቁ የታጠቁ ኃይሎች መካከል የሚካሄደው የትጥቅ ግጭት በክልሉ ሁሉም ዞኖች መስፋፋቱን ይገልጻል። ይሄው በትጥቅ የታገዘ ግጭትም በሲቪል ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ጠቁሟል (ሙሉ ሪፖርቱን ይመልከቱ)።

The post በጋዜጠኛ መሳይ የተሰራጨው ምስል የአማራ አርሶ አደሮችን ያሳያል? appeared first on MultiFactCheck.

]]>
በቲክቶክ የተሰራጨው ቪዲዮ በጎፋ የደረሰውን አደጋ ያሳያል? https://multifactcheck.org/%e1%89%a0%e1%89%b2%e1%8a%ad%e1%89%b6%e1%8a%ad-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%88%b0%e1%88%ab%e1%8c%a8%e1%8b%8d-%e1%89%aa%e1%8b%b2%e1%8b%ae-%e1%89%a0%e1%8c%8e%e1%8d%8b-%e1%8b%a8%e1%8b%b0%e1%88%a8%e1%88%b0/ Sat, 03 Aug 2024 16:43:45 +0000 https://multifactcheck.org/?p=8386 በጎፋ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የሟቾች ቁጥር 300 ደርሷል ከሚል መረጃ ጋር አንድ ቪዲዮ በቲክቶክ ተሰራጭቷል። መረጃው በተሰራጨበት ወቅት የሟቾች ቁጥር 300 መድረሱ አልተረጋገጠም ከመረጃው ጋርም የተያያዘው ቪዲዮ እ.አ.አ በ 2022 በህንድ ግዛት የተከሰተ የመሬት መንሸራተት የሚያሳይ ነው።

The post በቲክቶክ የተሰራጨው ቪዲዮ በጎፋ የደረሰውን አደጋ ያሳያል? appeared first on MultiFactCheck.

]]>
በፋሲል አረጋይ

የተጠቀሰው መረጃ፡ በጎፋ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የሟቾች ቁጥር 300 ደርሷል ከሚል መረጃ ጋር አንድ ቪዲዮ በቲክቶክ ተሰራጭቷል

ብያኔ፡ መረጃው በተሰራጨበት ወቅት የሟቾች ቁጥር 300 መድረሱ አልተረጋገጠም ከመረጃው ጋርም የተያያዘው ቪዲዮ እ.አ.አ በ 2022 በህንድ ግዛት የተከሰተ የመሬት መንሸራተት የሚያሳይ ነው።

ሐምሌ 18 ቀን 2016 ዓ/ም ከ99ሺ በላይ ተከታዮች ያሉት የቲክቶክ አካውንት “በጎፋ ዞን መሬት መንሸራተት የሞቱት 300 ሰው ደረሰ” ከሚል ጽሑፍ ጋር የመሬት መንሸራተት ሲከሰት የሚያሳይ ቪዲዮ አጋርቷል

ይህ ጽሑፍ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ ቪዲዮው ከ 2 ሚሊየን 500ሺ በላይ ሰው የተመለከተው ሲሆን ከ186ሺ በላይ ግብረ መልስ እና 4664 አስተያየት ሲያገኝ ከ118ሺ ጊዜ በላይ ተጋርቷል።


ሆኖም ምንም እንኳን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን የመሬት መንሸራተት አደጋ የተከሰተ ቢሆንም ይህ ጽሁፍ ለንባብ እስከበቃበት ጊዜ ድረስ በአደጋው ህይወታቸው ያለፈው ሰዎች ቁጥር 257 ሲሆን ከመረጃው ጋር ተያይዞ የቀረበው ቪዲዮ ሀሰተኛ እና በጎፋ ያለውን አደጋ የሚያሳይ አለመሆኑን አረጋግጠናል።

MFC የተለያዩ የሀቅ ማጣሪያ መንገዶችን በመጠቀም አጣርቶ  የቪዲዮውን ትክክለኛ መረጃ አግኝቷል። በዚህም ቪዲዮው ለመጀመሪያ ጊዜ የተጋራው CNN News 18 በተባለው ከ7 ሚሊየን 800ሺ በላይ ሰብስክራይበር ባለው የህንድ የዜና አውታር ይፋዊ የዩቲውብ ገጽ ላይ ነው። (እዚህ ይመልከቱ)


በዚህም ቪዲዮው እ.ኤ.አ በ2022 በሰሜናዊ ምስራቅ ህንድ በምትገኘው ሜጋሊያ ግዛት የደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋን የሚያሳይ ነው።

በመሆኑም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን የደረሰውን የመሬት መንሸራተት አደጋ ከሚገልጽ መረጃ ጋር የተጋራውን ቪዲዮ MFC ሀሰት በማለት በይኖታል።

ሐምሌ 14 2016 ዓ/ም በክልሉ ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተቀበሩ ሰዎችን ለማውጣት በማግስቱ ሐምሌ 15 2016 ዓ/ም በተሰባሰቡ የአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ለሁለተኛ ጊዜ የመሬት መንሸራተት አደጋ ደርሶባቸዋል።

ይህ ጽሑፍ ለንባብ እስከበቃበት ጊዜ ድረስ ከ250 በላይ ሰዎች ህይወት በአደጋው ተቀጥፏል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ቢሮ ኦቻ (OCHA) በአደጋው የሞቱ ዜጎች ቁጥር እስከ 500 ሊደርስ እንደሚችል ጠቁሟል። (እዚህ ይመልከቱ)

የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የሚመለከቷቸው መረጃዎች ላይ ግበረመልስ ከመስጠታቸው እና ከማጋራታቸው አስቀድመው የመረጃውን እና ከመረጃው ጋር ተያይዘው የሚቀርቡ የምስል እና ቪዲዮ ማስረጃዎችን እንዲመረምሩ እንዲሁም ትክክለኛነታቸውን እንዲያረጋግጡ MFC ያበረታታል።

The post በቲክቶክ የተሰራጨው ቪዲዮ በጎፋ የደረሰውን አደጋ ያሳያል? appeared first on MultiFactCheck.

]]>
ቪዲዮው በጎንደር ፋኖን በመቃወም የተደረገ ሰልፍን ያሳያል? https://multifactcheck.org/%e1%89%aa%e1%8b%b2%e1%8b%ae%e1%8b%8d-%e1%89%a0%e1%8c%8e%e1%8a%95%e1%8b%b0%e1%88%ad-%e1%8d%8b%e1%8a%96%e1%8a%95-%e1%89%a0%e1%88%98%e1%89%83%e1%8b%88%e1%88%9d-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%8b%b0%e1%88%a8/ Tue, 25 Jun 2024 18:17:23 +0000 https://multifactcheck.org/?p=8179 ጎንደር ላይ ፋኖን የሚቃወም ሰልፍ እንደተደረ የሚገልጽ ጽሁፍ ከቪዲዮ መረጃ ጋር በ “X” ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተጋርቷል። ይሁን እንጅ የተጋራው የቪዲዮ መረጃ በራያ አላማጣ የህወሃት ታጣቂዎችን በመቃወም የተደረገ ሰልፍን የሚያሳይ ነው።

The post ቪዲዮው በጎንደር ፋኖን በመቃወም የተደረገ ሰልፍን ያሳያል? appeared first on MultiFactCheck.

]]>
ፋሲል አረጋይ

የተጠቀሰው መረጃ፡ ጎንደር ላይ ፋኖን የሚቃወም ሰልፍ እንደተደረ የሚገልጽ ጽሁፍ ከቪዲዮ መረጃ ጋር በ “X” ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተጋርቷል።

ብያኔ፡ የተጋራው የቪዲዮ መረጃ በራያ አላማጣ የህወሃት ታጣቂዎችን በመቃወም የተደረገ ሰልፍን የሚያሳይ ነው።

ሰኔ 2 ቀን 2016 ዓ/ም Habitsh Gurmu የሚል ስያሜ ያለው የX ማህበራዊ መገናኛ ዘዴ አካውንት “ፋኖን የሚቃወም ሰልፍ በጎንደር” የሚል መረጃ ከቪዲዮ ማስረጃ ጋር አጋርቷል

የ 22 ሴኮንድ ርዝመት ባለው ቪዲዮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች የተለያዩ መፈክሮች ይዘው ይታያሉ። በዚሁ ቪዲዮ ላይም አንድ ግለሰብ “የታጠቁ ኃይሎች ፥ ትምህርት ቤት ላይ የመሸጉ ኃይሎች በ24 ሰዓታት ውስጥ ለቀው ይውጡልን” የሚል መፈክር ሲያሰማ ህዝቡም ሲያስተጋባ ይደመጣል።

MFC የመረጃውን ትክክለኛነት ለማጣራት የGoogle Reverse Image መረጃ ማጣሪያን የተጠቀመ ሲሆን ቪዲዮው የተቀረጸው ሰኔ 2 ፣ 2016 ዓ/ም ቢሆንም በጎንደር ፋኖን በመቃወም የተደረገ ሰልፍ አለመሆኑን አረጋግጧል።

ቪዲዮው ለመጀመሪያ ጊዜ የተጋራው በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን “የአላማጣ ከተማ ነዋሪዎች በሕወሓት እየተፈጸመ ያለውን ግፍ በሕዝባዊ ሰልፍ አውግዘዋል” ከሚል ርዕስ ጋር ነው።

በተጨማሪም ከዚህ በታች ባለው ምስል እንደሚታየው የሰልፉ ተሳታፊዎች በእጅ የያዟቸው መፈክሮች ሰልፉ ህወሃትን ለመቃወም የተካሄደ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል። 

በመሆኑም የፋኖ ሃይሎችን የሚቃወም ሰልፍ በጎንደር ከተማ ተካሄደ በሚል ከቪዲዮ ማስረጃ ጋር የቀረበውን ልጥፍ ሀሰት መሆኑን MFC አረጋግጧል።

ሰላማዊ ሰልፉ ከመደረጉ አስቀድሞ ግንቦት ወር ላይ የህወሃት ኃይሎች በአላማጣ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ መስፈራቸው ተዘግቧል

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ኃይሎች ከሰፈሩባቸው የአላማጣ ከተማ አቅራቢያ ስፍራዎች ለቀው እንዲወጡ አስተዳደራቸው መወሰኑን ይፋ አድርገው ነበር።

የትግራይ እና የአማራ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ በሚያነሱበት የራያ አካባቢዎች ባለፉት ጥቂት ወራት በነበሩ አለመረጋጋቶች ከ50 ሺ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት መረጃ ያሳያል

The post ቪዲዮው በጎንደር ፋኖን በመቃወም የተደረገ ሰልፍን ያሳያል? appeared first on MultiFactCheck.

]]>
ወደ አማራ ክልል ሰራዊት እየገባ ነው በሚል የተሰራጨው መረጃ ሀሰት ነው https://multifactcheck.org/%e1%8b%88%e1%8b%b0-%e1%8a%a0%e1%88%9b%e1%88%ab-%e1%8a%ad%e1%88%8d%e1%88%8d-%e1%88%b0%e1%88%ab%e1%8b%8a%e1%89%b5-%e1%8a%a5%e1%8b%a8%e1%8c%88%e1%89%a3-%e1%8a%90%e1%8b%8d-%e1%89%a0%e1%88%9a%e1%88%8d/ Sat, 22 Jun 2024 14:02:11 +0000 https://multifactcheck.org/?p=8149 የኦሮሚያ ኃይል ወደ አማራ ክልል ለወረራ እየገባ እንደሆነ የሚገልጽ ጽሁፍ ከቪዲዮ መረጃ ጋር በ”X” ማህበራዊ ሚዲያ ተሰራጭቷል። ነገር ግን ጽሁፉ የጥላቻ ንግግር ሲሆን የቪዲዮ መረጃው ከአራት አመት በፊት የኦሮሚያ ፖሊስ ምርቃት ስነ-ስርዓት የሚያሳይ በመሆኑ MFC ሀሰት ሲል ፈርጆታል።

The post ወደ አማራ ክልል ሰራዊት እየገባ ነው በሚል የተሰራጨው መረጃ ሀሰት ነው appeared first on MultiFactCheck.

]]>
በፋሲል አረጋይ

የተጠቀሰው መረጃ፦ የኦሮሚያ ኃይል ወደ አማራ ክልል ለወረራ እየገባ እንደሆነ የሚገልጽ ጽሁፍ ከቪዲዮ መረጃ ጋር በ”X” ማህበራዊ ሚዲያ ተሰራጭቷል

ብያኔ:- ነገር ግን ጽሁፉ የጥላቻ ንግግር ሲሆን የቪዲዮ መረጃው ከአራት አመት በፊት የኦሮሚያ ፖሊስ ምርቃት ስነ-ስርዓት የሚያሳይ በመሆኑ MFC ሀሰት ሲል ፈርጆታል።

በአማራ ክልል በመንግስት  ኃይላት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የቀጠለውን ግጭት መነሻ በማድረግ “Tordit- ቶ” የሚል ስያሜ ያለው የ”X” አካውንት  “ይህ ስብስብ ለተዘጋጀበት 10ኛው የኦሮሞ ወረራ ስምሪት ወስዶ ወደ አማራ ክልል በመትመም ላይ ነው። የጭፍጨፋውን ፊሽካ አብይ አህመድ ነፍቶ አስጀምሯል። ይህ ስብስብ ለኮንቬንሽናል ጦርነት አይደለም የተዘጋጀው። የጀኖሳይድ አርሚ ነው።” በማለት አንድ ቪዲዮ አሰራጭቷል (ይሄንን ማስፈንጠሪያ ይመልከቱ)

 

ተቀማጭነቱን በአዲስ አበባ ኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የሚተዳደረው የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (OBN) አርማ ባለበት በዚህ ቪዲዮ ላይ ከ35 በላይ በሆነ ረድፍ የተደረደሩ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል የደንብ ልብስ የለበሱ “ወታደሮች” ይታያሉ።  (ይሄንን ማስፈንጠሪያ ይመልከቱ)

MFC በልጥፉ ይዘት እና በቪዲዮው ላይ ማጣራት አድርጓል። በዚህም መልዕክቱ የተዛባ እና የጥላቻ ንግግር መሆኑን እንዲሁም ቪዲዮው በአሁኑ ወቅት ወደ አማራ ክልል እየገባ ያለ ጦር ነው ተብሎ የቀረበው መረጃ የተዛባ እና ሀሰተኛ መሆኑን አረጋግጧል።

የጥላቻ ንግግር

የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል የተባለ ሀገር በቀል ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት በመጋቢት 2013 ዓ/ም ለህትመት ባበቃው የጸረ ጥላቻ ንግግር እና የተዛቡ መረጃዎች መለያ መመሪያ (ለማንበብ ይሄንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ) የጥላቻ ንግግር ማህበረሰባዊና የዘር ውጥረቶችን እንደሚያባብስ እንዲሁም ለጥቃት እንደሚያነሳሳ ይገልጻል።

ተቋሙ በዚሁ ሰነዱ የጥላቻ ንግግር ተለይቶ የሚታወቅባቸው ባህሪዎች ንግግሩ ማንነት ላይ ያነጣጠረ ፣ ነውጥን የሚያበረታታ ፣ የፍረጃ ቃላትን የያዘ ፣ መልዕክቱ የደረሳቸው ተደራሲያን እርምጃ እንዲወስዱ የሚያበረታታ መሆኑን ይገልጻል።

በመሆኑም በዚሁ የ”X” አካውንት የተላለፈው መልዕክት ብሄር ላይ ያነጣጠረ ፣ ነውጥን የሚያበረታታ እና የፍረጃ ቃላትን በመጠቀም የጥላቻ መልዕክት አስተላልፏል።

ከአውድ ውጪ የተወሰደ ቪዲዮ

ከላይ ከተገለጸው መረጃ ጋር ተያይዞ የቀረበው የቪዲዮ ግብዓት ወደ አማራ ክልል እየገባ ያለ ጦር ሳይሆን የኦሮሚያ ክልል መንግስት ከአራት አመት በፊት የካቲት 29 ቀን 2012 ዓ/ም በቡልቡላ ማሰልጠኛ ማዕከል ለ30 ጊዜ የፖሊስ አባላትን ባስመረቀበት ወቅት የተቀረጸ መሆኑን MFC አረጋግጧል። (ይሄንን ማስፈንጠሪያ ይመልከቱ)

የክልሎችን የልዩ ኃይል አደረጃጀት ለመበተን እና በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ወይንም በመደበኛው የፖሊስ የጸጥታ መዋቅር ውስጥ የማደራጀት ውሳኔ መወሰኑን ተከትሎ በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ “የፋኖ” አደረጃጀቶች ውሳኔውን በመቃወም ከፌደራል መንግስት ጋር ግጭት ውስጥ መግባታቸው ይታወቃል።

በክልሉ የተቀሰቀሰው ግጭት ተከትሎ በሐምሌ 25  2015 ዓ/ም በክልሉ እንዲሁም እንደ አስፈላጊነቱ በመላው ኢትዮጵያ ተግባራዊ የሚሆን ለስድስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን  የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ጥር 24 2016 ዓ/ም ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ለተጨማሪ አራት ወራት እንዲራዘም አድርጎ ክልሉ በአስቸኳይ አዋጅ ስር ቆይቷል።

በአማራ ክልል በመንግስት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል አሁንም ድረስ በዘለቀው ግጭት የበርካታ ንጹሃን ህይወት ማለፉን ፣ ንብረት መውደሙን እንዲሁም ዜጎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና አለም አቀፍ ተቋማት ይፋ አድርገዋል።

The post ወደ አማራ ክልል ሰራዊት እየገባ ነው በሚል የተሰራጨው መረጃ ሀሰት ነው appeared first on MultiFactCheck.

]]>
እውን አቶ ታዲዮስ ታንቱ ከእስር ተፈትተዋል? https://multifactcheck.org/%e1%8a%a5%e1%8b%8d%e1%8a%95-%e1%8a%a0%e1%89%b6-%e1%89%b3%e1%8b%b2%e1%8b%ae%e1%88%b5-%e1%89%b3%e1%8a%95%e1%89%b1-%e1%8a%a8%e1%8a%a5%e1%88%b5%e1%88%ad-%e1%89%b0%e1%8d%88%e1%89%b5%e1%89%b0%e1%8b%8b/ Sat, 08 Jun 2024 17:04:53 +0000 https://multifactcheck.org/?p=8121 “አቶ ታዲዮስ ታንቱ ከእስር ተፈትተዋል” የሚሉ መረጃዎች በፌስቡክ እና በትዊተር ላይ እየተሰራጩ ይገኛሉ። ይሁን እንጂ መረጃዎቹ ሐሰት ናቸው።

The post እውን አቶ ታዲዮስ ታንቱ ከእስር ተፈትተዋል? appeared first on MultiFactCheck.

]]>
በናኦል ጌታቸው

የተጠቀሰው መረጃ፦ “አቶ ታዲዮስ ታንቱ ከእስር ተፈትተዋል” የሚሉ መረጃዎች በፌስቡክ እና በትዊተር ላይ እየተሰራጩ ይገኛሉ።

ብያኔ፦ መረጃዎቹ ሐሰት ናቸው።

“አቶ ታዲዮስ ታንቱ ከእስር ተፈትተዋል” የሚሉ መረጃዎች በፌስቡክ ( ለአብነት ይህንንይህንን ፣ ይህንንናይህንን መስፈንጠሪያዎች ተጠቅመው ይመልከቱ)  እና በትዊተር ላይ ( ለአብነትይህንንናይህንን መስፈንጠሪያዎች ተጠቅመው ይመልከቱ) በግንቦት 30/ 2016 አ.ም. ሲሰራጩ ውለዋል።

ይሁን እንጂ  በተለያዩ አካውንቶች የተሰራጨው መረጃ ሐሰት ነው።

መረጃዎቹ ሲሰራጩም ከአንድ ፎቶግራፍ ጋር መዘዋወራቸውን ለመመልከት ተችሏል። MFC ፎቶውን በGoogle Reverse Image ያጣራ ሲሆን ምስሉ ከሶስት አመት በፊት አቶ ታዲዮስ ከእስር መፈታታቸውን ተከትሎ በፌስቡክ ላይ የ“እንኳን አደረስዎ” መልእክት ሲያሰተላልፉ የተሰራጨ ምስል መሆኑን ለማወቅ ተችሏል (ለአብነት ይህንንይህንንይህንንይህንን መስፈንጠሪያዎች ተጠቅመው ይመልከቱ)። ይሁን እንጂ ፎቶው ለመጀመሪያ ጊዜ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በመታየቱን እንጂ በትክክል መቼ እንደተነሳ ለማወቅ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

በወቅቱ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በወንጀል ተጠርጥረው ከሚያዝያ 27 ቀን 2013 አንስቶ ለሰላሣ ቀናት በእስር ላይ ከቆዩ በኋላ በአራት ሺህ ብር ዋስትና ነበር የተለቀቁት

ከዚህም በተጨማሪ MFC  የአቶ ታዲዮስ ታንቱ ባለቤት የሆኑትን ወ/ሮ ጸጋ ሞገስን በስልክ ያነጋገረ ሲሆን መረጃው ሐሰተኛ መሆኑን አረጋግጠዋል። 

ከዚህም በተጨማሪ የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን በፌስቡክ ገጹ ላይ መግለጫ ያወጣ ሲሆን “አቶ ታዲዮስ ታንቱ በዛሬው ዕለት ከእስር ተፈቱ ተብሎ በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የተሠራጨው መረጃ ስህተት መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን” በማለት ገልጿል።

በመሆኑም ከላይ በተጠቀሱት መረጃዎች መሰረት MFC አቶ ታዲዮስ ታንቱ ከእስር ተፈትተዋል የሚለው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን አረጋግጧል። 

አውድ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በኢትዮጵያ የሚዲያና የፖለቲካ መድረክ የታወቁ ሰው ሲሆኑ ለረጅም ጊዜ አነጋጋሪ የታሪክ ሀሳቦችን በተለያዩ መድረኮችና ሚዲያዎች ላይ በመግለጽ ይታወቃሉ። በፍትሕ ጋዜጣ ፣ ፋክት መፅሔት ፣ ልዕልና ጋዜጣ ፣ አዲስ ታይምስ መፅሔትና እና በሌሎች የህትመት ሚዲያዎች ላይ የአርበኞችን ታሪክና ሌሎች ሀሳቦችን ሲፅፉ የቆዩ ሲሆን ከቅርብ አመታት ወዲህ ደግሞ በዩቲዩብ ሚዲያዎች በእንግድነት በመቅረብ አነጋጋሪ ቃለ መጠይቆችን ሲሰጡ ቆይተዋል። በዚህም ምክንያት በተለያዩ ጊዜያት ለእስር ሲዳረጉና ሲፈቱ ቆይተዋል። የአሁን እስርም በግንቦት 10/2014 የ “ጥላቻ ንግግር በማሰራጨትና የእርስ በእርስ ግጭት በመቀስቀስ” ወንጀል ተጠርጥረው ነው።

በ2012 አ.ም. በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኩል የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር አዋጅ መውጣቱ ይታወሳል። 

በ2012 አ.ም. በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኩል የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር አዋጅ መውጣቱ ይታወሳል። 

አዋጁ በተራ ቁጥር 4 ስር “ማንኛውም ሰው የጥላቻ ንግግርን በብሮድካስት፣ በህትመት ወይም በማህበራዊ ሚዲያዎች ወይም በሌላ ተመሳሳይ ዘዴዎች አማካኝነት በጽሁፍ፣ በምስል፣ በድምጽ ወይም በቪዲዮ ማሰራጨት የተከለከለ ነው፡፡” ይህን በማለት የጥላቻ ንግግር ስለመከልከሉ ያሰፈረ ሲሆን ፤ የጥላቻ ንግግር ያደረገ ማንኛውም ሰው እስከ ሁለት አመት በሚደርስ ቀላል እስራት ወይም ከብር 100 ሺ ያልበለጠ መቀጮ እንደሚቀጣ ፣ እንዲሁም በጥላቻ ንግግሩ ምክንያት ጥቃት የተፈጸመ እንደሆነ ቅጣቱ ከአንድ አመት እስከ አምስት አመት የሚደርስ ቀላል እስራት እንደሚሆንም አዋጁ አስቀምጧል።

The post እውን አቶ ታዲዮስ ታንቱ ከእስር ተፈትተዋል? appeared first on MultiFactCheck.

]]>
ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የበጎ አድራጎት ስራ በመስራት የሚታወቀው ማስተር አብነት ሽልማት እየሰጠ ነው? https://multifactcheck.org/%e1%88%9b%e1%88%85%e1%89%a0%e1%88%ab%e1%8b%8a-%e1%88%9a%e1%8b%b2%e1%8b%ab-%e1%88%8b%e1%8b%ad-%e1%8b%a8%e1%89%a0%e1%8c%8e-%e1%8a%a0%e1%8b%b5%e1%88%ab%e1%8c%8e%e1%89%b5-%e1%88%b5%e1%88%ab-%e1%89%a0/ Fri, 07 Jun 2024 14:24:55 +0000 https://multifactcheck.org/?p=8095 በማስተር አብነት ስም የተከፈቱ የቴሌግራም ግሩፖች ሽልማት እየሰጡ እንደሆነ የሚገልጽ መረጃ አሰራጭተዋል። ነገር ግን የቴሌግራም ግሩፖቹ ተመሳስለው የተከፈቱ መሆናቸው የተረጋገጠ ሲሆን ያቀረቡት የሽልማት አይነት እና መጠን ሐሰት ነው።

The post ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የበጎ አድራጎት ስራ በመስራት የሚታወቀው ማስተር አብነት ሽልማት እየሰጠ ነው? appeared first on MultiFactCheck.

]]>
ፋሲል አረጋይ

የተጠቀሰው መረጃ፦ በማስተር አብነት ስም የተከፈቱ የቴሌግራም ግሩፖች ሽልማት እየሰጡ እንደሆነ የሚገልጽ መረጃ አሰራጭተዋል።

ብያኔነገር ግን የቴሌግራም ግሩፖቹ ተመሳስለው የተከፈቱ መሆናቸው የተረጋገጠ ሲሆን ያቀረቡት የሽልማት አይነት እና መጠን ሐሰት ነው።

ከ 138 ሺ በላይ አባላት ያሉት “Master Abinet Kebede” የተባለ የቴሌግራም ግሩፕ ግንቦት 13 ቀን 2016 ዓ/ም “…50 ሰዎች አድ ላደረገ 5ሺህ ብር እንልካለን” የሚል መረጃ አጋርቷል

ይሄው የቴሌግራም ግሩፕ በተመሳሳይ ቀን “ዮሴፍ በቀለ የተባለ ግለሰብ ሽልማቱን በፍጥነት ተቀብሏል ሌሎቻችሁም ፍጠኑ…” የሚል የላኪው ማንነት እንዳይታይ የተሸፈነ የንግድ ባንክ የሞባይል ባንኪንግ የገንዘብ ዝውውርን የሚያሳይ ምስል ለጥፏል

MFC ባካሄደው የዳሰሳ ጥናት መሰረት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በበጎ ስራዎቹ በሚታወቀው ማስተር አብነት ስም የተከፈቱ ከ 15 በላይ የቴሌግራም ግሩፖችን አግኝቷል። በተመሳሳይ እነዚህ ግሩፖች የቴሌግራም ተጠቃሚዎች ወደ ግሩፑ ሰዎችን አባል ሲያደርጉ ከፍተኛ መጠን ያለው ሽልማት እንደሚያገኙ የሚገልጹ አጓጊ ልጥፎችን የያዙ ናቸው።

ከMFC የቴሌግራም ግሩፖቹን በተመለከተ ጥያቄ የቀረበለት ማስተር አብነት ከቲክቶክፌስቡክ እና የዩቲውብ ቻናል ውጪ ምንም አይነት የቴሌግራም ግሩፕ እንደሌለው ገልጿል።

በተጨማሪ MFC ባደረገው ማጣራት “Master Abenet Kebede”  የተባለው የቴሌግራም ግሩፑ የካቲት 23 እና 24 2015 ዓ/ም ስያሜውን ወደ “Safaricom ሳፋሪኮም”  በመለወጥ ተመሳሳይ ተግባር ፈጽሟል

ቲክቶክ ላይ ከ2.6 ሚሊየን በላይ ፣ ፌስቡክ ላይ 704ሺ ተከታዮች እንዲሁም ዩቲውብ ላይ ከ172ሺ በላይ ሰብስክራይበሮች ባሉት እና በበጎ አድራጎት ስራዎቹ በሚታወቀው ማስተር አብነት ስም ተመሳስለው የተከፈቱት እነዚህ የቴሌግራም ግሩፖች የተለያዩ ሽልማቶችን መስጠታቸውን ለመግለጽ የገንዘብ ዝውውር የተደረገበት በሚል የተቀናበሩ የንግድ ባንክ የሞባይል ባንኪንግ ገንዘብ ዝውውር መግለጫ ምስሎችን እንደሚጠቀሙ MFC አረጋግጧል።

ከታች በምስሉ ላይ እንደሚታየው ትክክለኛው የንግድ ባንክ የሞባይል ባንኪንግ ገንዘብ ዝውውር መግለጫ የጽሁፍ ፎንት እና በቴሌግራም ግሩፑ ለሽልማት የተከፈለ በሚል የቀረበው የገንዘብ ዝውውር መግለጫ ተመሳሳይ አይደለም።

በመሆኑም ከ130 ሺ በላይ አባላት ያሉትን ጨምሮ በማስተር አብነት ስም የተከፈቱት የቴሌግራም ግሩፖች በየማስተር አብነት ከበደ  አለመሆናቸውን MFC አረጋግጧል።

MFC ከዚህ ቀደም የታዋቂ ሰዎችን ማንነት በማስመሰል የቴሌግራም ግሩፖችን በመክፈት ይጠቀም የነበረ ማንነቱ እንዳይገለጽ የጠየቀ ግለሰብን በጉዳዩ ላይ ያነጋገረ ሲሆን ግሩፖቹ በዋነኛነት ለሁለት አላማ እንደሚውሉ ተናግሯል።

የመጀመሪያው የግሩፑ አባላት ቁጥር ሲያድግ ለሽያጭ ማቅረብ ሲሆን ሁለተኛው የቴሌግራም ግሩፑ በታዋቂው ሰው ማንነት የአባላት ቁጥሩ እንዲያድግ ከተደረገ በኋላ ስያሜውን በመቀየር የተለያዩ እቃዎችን መሸጫ እንደሚሆንም ገልጾልናል።

The post ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የበጎ አድራጎት ስራ በመስራት የሚታወቀው ማስተር አብነት ሽልማት እየሰጠ ነው? appeared first on MultiFactCheck.

]]>
“በኢትዮጵያ የዘር ማጥፋት እየተካሄደ ነው” በሚል የተሰራጨው መስል የቆየ ነው https://multifactcheck.org/%e1%89%a0%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%8b%a8%e1%8b%98%e1%88%ad-%e1%88%9b%e1%8c%a5%e1%8d%8b%e1%89%b5-%e1%8a%a5%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%8a%ab%e1%88%84%e1%8b%b0-%e1%8a%90/ Fri, 03 May 2024 09:29:46 +0000 https://multifactcheck.org/?p=7987 አንድ የX አካውንት “በኢትዮጵያ የዘር ማጥፋት እየተካሄደ ነው” የሚል ትርጉም ካለው የእንግሊዘኛ ፅሁፍ ጋር በማያያዝ አንድ “ዘግናኝ” ይዘት ያለው ምስል ለጥፏል። ምስሉ (አሁን) በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለን "የዘር ማጥፋት" የሚያሳይ ሳይሆን ከአምስት አመት በፊት በሐሰተኛ መረጃ ምክንያት የደቦ ፍርድ ጥቃት ሰለባ የሆነን ግለሰብ ዘገናኝ ምስል የሚያሳይ በመሆኑ የተጠቀሰው መረጃ ሀሰት ነው።

The post “በኢትዮጵያ የዘር ማጥፋት እየተካሄደ ነው” በሚል የተሰራጨው መስል የቆየ ነው appeared first on MultiFactCheck.

]]>
የተጠቀሰው መረጃ፦ አንድ የX አካውንት “በኢትዮጵያ የዘር ማጥፋት እየተካሄደ ነው” የሚል ትርጉም ካለው የእንግሊዘኛ ፅሁፍ ጋር በማያያዝ አንድ “ዘግናኝ” ይዘት ያለው ምስል ለጥፏል።

በያኑ፦ ምስሉ (አሁን) በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለን “የዘር ማጥፋት” የሚያሳይ ሳይሆን ከአምስት አመት በፊት በሐሰተኛ መረጃ ምክንያት የደቦ ፍርድ ጥቃት ሰለባ የሆነን ግለሰብ ዘገናኝ ምስል የሚያሳይ በመሆኑ የተጠቀሰው መረጃ ሀሰት ነው።

Zoom Afrika, የሚል ስም ያለው እና ከ274,000 በላይ ተከታዮች ያሉት የX አካውንት “በኢትዮጵያ የዘር ማጥፋት እየተካሄደ ነው” የሚል ትርጉም ካለው የእንግሊዘኛ ፅሁፍ ጋር በማያያዝ ፎቶ አጋርቷል። ይህም ትዊት ይህ ፅሑፍ እስከሚታተም ድረስ ከ102,000 በላይ እይታዎች እና ከ800 በላይ ገብረ መልስ ሲያገኝ ከ480 ጊዜ በላይ ተጋርቷል። 

ይሁን እንጂ አካውንቱ ፅሁፉን እንዲድግፍለት ያያዘው ፎቶ የቆየ እና በሌላ አውድ ውስጥ የተፈጠረን ክስተት የሚያሳይ ነው።

MFC የጎግል ምስል ማፋለጊያ መሳሪያን በመጠቀም ምስሉን ለማጣራት ባደረገው ጥረት የመጀመሪያው የምስሉ ምንጭ ወይም ባለቤት ማን እንደሆነ ለማወቅ አልተቻለም። ይሁን እንጂ መሳሪያው ይህ ምስል ከአምስት አመታት በፊት የተሰራጩትን ጨምሮ በተለያዩ ጊዜያት መሰራጨቱን ያሳያል።

በመሆኑም ይህ ዘግናኝና አሳዛኝ ክስተትን የሚያሳየው ምስል ከአምስት አመታት በፊት በነሃሴ 6/2010 አ.ም በሻሸመኔ ከተማ በወቀቱ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ዳይሬክተር የነበረውን አቶ ጃዋር መሕመድን እና ለሌሎች የቡድኑ አባላት አቀባበል ለማድረግ በተዘጋጀ ስነ ስርዓት ላይ ከተከሰተ “የደቦ ፍርድ” የተወሰደ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። 

በእለቱም “ቦንብ ይዟል” በሚል ሐሰተኛ መረጃ ምክንያት በአንድ ግለሰብ ላይ በደቦ አሰቃቂ ግድያ በአደባባይ የተፈፀመ ሲሆን ምስሉ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ በስፋት ተዘዋውሯል። (ለአብነትም ይህንንይህንን እና ይህንን ማስፈንጠሪያ ይመልከቱ።)

በመሆኑም ምስሉ በX አካውንቱ እንደተጠቀሰው (አሁን) በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለን የዘር ማጥፋት የሚያሳይ ሳይሆን ከአምስት አመት ከ8 ወራት በፊት በሻሸመኔ ከተማ በሐሰተኛ መረጃ ምክንያት የደቦ ፍርድ ጥቃት ሰለባ የሆነን ግለሰብ ዘገናኝ ምስል የሚያሳይ በመሆኑ የተጠቀሰው መረጃ ሀሰት ነው።

The post “በኢትዮጵያ የዘር ማጥፋት እየተካሄደ ነው” በሚል የተሰራጨው መስል የቆየ ነው appeared first on MultiFactCheck.

]]>
ቪዲዮው በቦሌ የነበረውን የፋኖ ኦፕሬሽን አያሳይም https://multifactcheck.org/%e1%89%aa%e1%8b%b2%e1%8b%ae%e1%8b%8d-%e1%89%a0%e1%89%a6%e1%88%8c-%e1%8b%a8%e1%8a%90%e1%89%a0%e1%88%a8%e1%8b%8d%e1%8a%95-%e1%8b%a8%e1%8d%8b%e1%8a%96-%e1%8a%a6%e1%8d%95%e1%88%ac%e1%88%bd%e1%8a%95/ Fri, 19 Apr 2024 17:23:42 +0000 https://multifactcheck.org/?p=7971 አንድ ቪዲዮ በዕለቱ የነበረን “የፋኖ ኦፕሬሽን” እንደሚያሳይ ተደርጎ በX ማህበራዊ የትስስር መድረክ ተሰራጭቷል። የተጠቀሰው መረጃ ከ5 ወራት በፊት በአፍጋኒስታን የነበረን ሁኔታ የሚያሳይ እንጂ የአዲስ አበባን ክስተት የሚያሳይ ባለመሆኑ ሐሰት ነው።

The post ቪዲዮው በቦሌ የነበረውን የፋኖ ኦፕሬሽን አያሳይም appeared first on MultiFactCheck.

]]>
በናኦል ጌታቸው

የተጠቀሰው መረጃ ፦ አንድ ቪዲዮ በዕለቱ የነበረን “የፋኖ ኦፕሬሽን” እንደሚያሳይ ተደርጎ በX ማህበራዊ የትስስር መድረክ ተሰራጭቷል።

ብያኔ፦ የተጠቀሰው መረጃ ከ5 ወራት በፊት በአፍጋኒስታን የነበረን ሁኔታ የሚያሳይ እንጂ የአዲስ አበባን ክስተት የሚያሳይ ባለመሆኑ ሐሰት ነው።

Neba የሚል ስም ያለውና ከ4,400 በላይ ተከታዮች ያሉት የX አካውንት በሚያዝያ 4/2016 ዓ.ም. ቪዲዮ አጋርቷል። ይህ “የዛሬው ቦሌ ላይ የነበረው የ#Fano Operation ሙሉ ቪዲዮ” ከሚል ፅሁፍ ጋር የተጋራው ቪዲዮ ይህ የሀቅ ማጣራት ፅሁፍ እስከሚታተም ድረስ ብቻ ከ37,000 በላይ ዕይታ አግኝቷል። 

ይሁን እንጂ MFC ባደረገው ማጣራት ቪዲዮው በዕለቱ የነበረውን የቦሌ አዲስ አበባ ሁኔታ አያሳይም። 

ምስል፤ ከላይ በተጠቀሰው የX አካውንት ከተጋራው ይዘት በሚያዝያ 9/2016 የተወሰደ ስክሪንሾት 

ከቪዲዮው ላይ ስክሪንሾቶችን በመውሰድ በጎግል የምስል ማፋለጊያ መሳሪያ በተደረገው ማጣራት ፣ ቪዲዮው የሚያሳየው አፍጋኒስታንን እያስተዳደረ ያለው የታሊባን ታጣቂ ወታደሮች በባለጎማ መንሸራተቻ ጫማ ሆነው የዋና ከተማዋን የካቡልን ጎዳናዎች ሲቃኙ ራሳቸውን የቀረፁበትን የቪዲዮ ቅጂ ነው።

ይህም ከአምስት ወራት በፊት የሆነ ሲሆን ዘ ቴሌግራፍዘ ኢኮኖሚስት ፣ እና ሌሎች የሚዲያ ተቋማት በኩል በተሰራ ዘገባ የተሰራጨ ነው። 

ምስሎች: ከ The Telegraph እና The Economist የሚዲያ አውታር የዩቲዩብ ቻናሎች በሚያዝያ 9/2016 ዓ.ም. የተወሰዱ ስክሪንሾቶች

በተጨማሪም የተጠቀሰውን መረጃ ያሰራጨው አካውንት ከአፍጋኒስታን በተወሰደው ቪዲዮ ላይ ከአራት ወራት በፊት በአዲስ አበባ በነበረ “የታላቅ ሩጫ” ላይ የተሰማ “እየመጡ ነው እየመጡ ነው” የሚል የህብረት “ዜማ/ሆታ”ን ድምፅ በቅንብር አካትቶበታል።

በመሆኑም MFC ባደረገው ማጣራት የተጠቀሰው መረጃ ከ5 ወራት በፊት በአፍጋኒስታን የነበረን ሁኔታ የሚያሳይ እንጂ የአዲስ አበባን ክስተት የሚያሳይ ባለመሆኑ ሐሰት ሲል በይኖታል።

አውድ

ሚያዚያ 4/2016 ዓ.ም. በመሐል አዲስ አበባ ቦሌ አካባቢ ፖሊስ የፋኖ አባላት ናቸው ካላቸው ግለሰቦች ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርጎ ሁለቱን መግደሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቆ ነበር። 

የተለያዩ የሚዲያ አውታሮችም እንደዘገቡት በቦሌ ክፍለ ከተማ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ የፋኖ “አመራር” ናቸው በተባሉ ታጣቂዎች መካከል የተኩስ ልውውጥ የተደረገ ሲሆን ፤ በዚህም ከታጣቂዎቹም ከፖሊስም ወገን የሞቱ መኖራቸው ተዘግቧል። 

ይህም ክስተት በሁለቱ ወገን በተለያየ መልኩ ተዘግቧል። ይህም በመንግስት በኩል “በጽንፈኛው ኃይል አመራርና አባላት ላይ እርምጃ” እንደተወሰደ ተደርጎ ሲዘገብ ፤ በታጣቂዎቹ በኩል ደግሞ “ፋኖ በአዲስ አበባ ያከናወነው የወታደራዊ ኦፕሬሽን” ተደርጎ በየሚዲየው ተሰራጭቷል። 

ከላይ የተጠቀሰው መረጃም በዚህ አውድ የተሰራጨ ይዘት ነው።

The post ቪዲዮው በቦሌ የነበረውን የፋኖ ኦፕሬሽን አያሳይም appeared first on MultiFactCheck.

]]>
ቀይ መስቀል ማኀበር ለፋኖ የምስጋና ደብዳቤ እንደላከ ተደርጎ የተሰራጨው ምስል በፎቶሾፕ የተቀናበረ ነው https://multifactcheck.org/%e1%89%80%e1%8b%ad-%e1%88%98%e1%88%b5%e1%89%80%e1%88%8d-%e1%88%9b%e1%8a%80%e1%89%a0%e1%88%ad-%e1%88%88%e1%8d%8b%e1%8a%96-%e1%8b%a8%e1%88%9d%e1%88%b5%e1%8c%8b%e1%8a%93-%e1%8b%b0%e1%89%a5%e1%8b%b3/ Wed, 17 Apr 2024 16:48:19 +0000 https://multifactcheck.org/?p=7965 የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ለፋኖ ታጣቂ ኃይል የምስጋና ደብዳቤ እንደላከ የሚገልፅ የደብዳቤ ፎቶ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ተሰራጭተዋል። ምስሉ በፎቶሾፕ የተቀናበረ በመሆኑ የተጠቀሰው መረጃ ሐሰት ነው።

The post ቀይ መስቀል ማኀበር ለፋኖ የምስጋና ደብዳቤ እንደላከ ተደርጎ የተሰራጨው ምስል በፎቶሾፕ የተቀናበረ ነው appeared first on MultiFactCheck.

]]>
በናኦል ጌታቸው

የተጠቀሰው መረጃ፦ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ለፋኖ ታጣቂ ኃይል የምስጋና ደብዳቤ እንደላከ የሚገልፅ የደብዳቤ ፎቶ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ተሰራጭተዋል። 

ብያኔ፦ ምስሉ በፎቶሾፕ የተቀናበረ በመሆኑ የተጠቀሰው መረጃ ሐሰት ነው።

AmharaAquila የሚል ስም ያለው እና ከ16,000 በላይ ተከታዮች ያሉት የX አካውንት “የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ለፋኖ አድናቆቱን ገለፀ” የሚል ትርጉም ያለው የእንግሊዘኛ ፅሁፍ ከምስል ጋር በመጋቢት 26/ 2016 ዓ.ም. ለጥፏል። 

ከተጠቀሰው የX ፖስት ላይ በሚያዝያ 2 የተወሰደ ስክሪንሾት

ይህም ፖስት ከ140 ጊዜ በላይ ተደጋግሞ የተጋራ ሲሆን ከ12,100 በላይ ዕይታም አግኝቷል።

በተጨማሪም ይኸው ምስል በቲክቶክ ላይ የተሰራጨ ሲሆን ፤ ከ1,200 ጊዜ በላይ ተጋርቶ ከ30,000 በላይ ዕይታዎችም አግኝቷል። 

በተመሳሳይም ምስሉ በፌስቡክ ላይ በተለያዩ አካውንቶች አማካይነት የተዛመተ መሆኑን ለማየት ተችሏል። (ለአብነትም ይህንንይህንንይህንን እና የመሳሰሉትን መስፈንጠሪያዎች ይመልከቷቸው።)

ይሁን እንጂ ምስሉ [በፎቶሾፕ] የተቀናበረ በመሆኑ እና ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል በተገኘው መረጃ መሰረት ሐሰት መሆኑ ተረጋግጧል። 

Invid Forensicን በመጠቀም MultiFactCheck (MFC) ምስሉን የመረመረ ሲሆን ከታች በምትመለኩት መልኩ በፎቶሾፕ የተቀናበሩ ቦታዎችን አመልክተዋል። 

ምስሉን በInVID we verify መሳሪያ ምስሎች በፎቶሾፖች መቀናበራቸውን በሚመረምረው Forensic ሲመረመር የተገኘውን ውጤት በመጋቢት 2 የተወሰደ ስክሪንሾት ፤ ምስሉም በውኃ ሰማያዊ ቀለም ምልክት ያደረገባቸው በፎቶሾፕ መጨመራቸው የሚገልፅ ነው።

ከዚህም በተጨማሪም MFC የቀይ መስቀል ማህበር የበጎ አድራጎት ፣ ዲፕሎማሲና ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ የሆኑትን አቶ መስፍን ደጀኔን በስልክ ያነጋገረ ሲሆን “ምስሉ ፎቶሾፕ ተሰርቶ ነው። [በደብዳቤው ላይ የተጠቀሰው] ሰውየው በሌላ ዲፓርትመንት ውስጥ የሚሰራ ነው። እንደዚህ አይነት ደብዳቤ የመፃፍ ማንዴትም [ስልጣንም] የለንም” ሲሉ አረጋግጠውልናል። 

በተያያዘም የተሰራጨውን ደብዳቤ ለማጤን ብንሞክር የሚከተሉትን ሁነቶች ለማስተዋል እንችላለን። 

  1. ከታች በምስሉ ላይ እንደተመላከተው ይፋዊ ደብዳቤዎች ሲፃፉ የማይስተዋሉ ስህተቶቾን መመልከታችን በችኮላ ከሚሰሩ የሀሰት ፎቶሾፕ ምስሎች አንዱ እንደሆነ ለመገንዘብ ይረዳናል። ለአብነትም፦
    • በቀይ ያሰመርንባቸውን ስንመለከት ፣ በቃላት መካከል ሊኖር የሚገባ ክፍተት ባለመጠቀምና ሁለት ቃላትን በተደጋጋሚ አያይዞ መፃፍ 
    • በሰማያዊ የተሰመረባቸውን ስንመለከት ፣ ተደጋጋሚ የቃላት ስህተቶች
    • በአረንጓዴ የተሰመረባቸውን ስንመለከት ፣ ተቋማት የማይጠቀሟቸው ያልተመረጡ ቃላትና የፊደል መረጣ ስህተትን ለማስተዋል ይቻላል።
  2. በቀስቱ የተመላከቱትን ስንመለከት ፣ ፕሮፌሽናል ደብዳቤዎች ሲፃፉ የሚከተሉትን አንድ ወጥ ፎንት የመጠቀምን ስርዓት ያልተከተለና የተዘበራረቀ የፎንት አጠቃቀም ፣ ተገቢ ያለሆነ የአንቀፅ አጠቃቀምን ልብ ለማለት እንችላለን።
  1. በአማርኛ ለሚፃፍ ደብዳቤ በእንግሊዘኛ የህዳግ ስምና የመልካም ምኞት መፃፉም አስቀድሞ በእንግሊዘኛ የተዘጋጀን የቆየ ደብዳቤ በፎቶሾፕ አርትኦት ለመሰራቱ እንደመረጃ ግብዓት ይሆናል።

በመሆኑም MFC የተጠቀሰውን ምስል እውነተኝነት በማጣራት ሂደት ውስጥ በInVID መሳሪያ ፣ በተቋሙ ኃላፊ የምስክር ቃል እና ተጨማሪ በተደረገው ምርመራ መረጃውን ሐሰት ሲል በይኖታል።  

የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችም መሰል መረጃዎችን ሲመለከቱ ፈጥኖ ከማመንና ከማጋራት በፊት የመረጃውን እውነተኝነት ለማጣራት መረጃውን በትኩረት እንዲመለከቱ እንዲሁም ወደ ተጠቀሰው ተቋም ይፋዊ ድረ ገፅ በመሄድ እንዲያጣሩ እንመክራለን።

The post ቀይ መስቀል ማኀበር ለፋኖ የምስጋና ደብዳቤ እንደላከ ተደርጎ የተሰራጨው ምስል በፎቶሾፕ የተቀናበረ ነው appeared first on MultiFactCheck.

]]>