Amhara Region Archives - MultiFactCheck https://multifactcheck.org/tag/amhara-region/ Shed Light on the Truth. Mon, 02 Sep 2024 16:59:24 +0000 en-US hourly 1 https://wordpress.org/?v=6.7.1 https://multifactcheck.org/wp-content/uploads/2021/07/cropped-multifactcheck-1-150x150.jpeg Amhara Region Archives - MultiFactCheck https://multifactcheck.org/tag/amhara-region/ 32 32 ሐሰት ፦ ምስሉ የጎጃም መንገድ መዘጋቱን አያሳይም https://multifactcheck.org/%e1%88%90%e1%88%b0%e1%89%b5-%e1%8d%a6-%e1%88%9d%e1%88%b5%e1%88%89-%e1%8b%a8%e1%8c%8e%e1%8c%83%e1%88%9d-%e1%88%98%e1%8a%95%e1%8c%88%e1%8b%b5-%e1%88%98%e1%8b%98%e1%8c%8b%e1%89%b1%e1%8a%95-%e1%8a%a0/ Wed, 28 Feb 2024 08:53:09 +0000 https://multifactcheck.org/?p=7655 በመሆኑም MultiFactCheck ልጥፉን መርምሮ ምስሉ የቆየ እና ከወቅቱ የአማራ ክልል ግጭት ጋር የማይያያዝ መሆኑን ያረጋገጠ ሲሆን ፤ በልጥፉ እንደተገለፀውም “ጎጃምን መንገድ መዘጋት” የማያሳይ በመሆኑ ሐሰት ብሎታል።

The post ሐሰት ፦ ምስሉ የጎጃም መንገድ መዘጋቱን አያሳይም appeared first on MultiFactCheck.

]]>

በናኦል ጌታቸው

ግርማ አየለ (Girma Ayele GA) የተሰኘዉ ፣ ፌስቡክ ላይ ከ2,500 በላይ ተከታይ ያለው ግለሰብ፣ አንድ ምስል የያዘ ልጥፍ (post) በማያያዝ “ጎጃም መንገዱን ጥርቅም ነው” ከሚል ገለፃ ጋር አጋርቷል። ይህ ከአማራ ክልል ግጭት ጋር በተያያዘ በጎጃም መንገዶች በድንጋይ መዘጋታቸውን የሚገልፀውና የካቲት 17/2016 ዓ.ም. የተጋራው ልጥፍ ይህ ፅሁፍ እስከሚወጣበት ቀን ድረስ ከ44 በላይ ጊዜ ሲጋራ ከ577 በላይ ግብረ መልሶችም አግኝቷል  (ምስሉን ታች ከሚታየዉ ስክርንሾት ይመልከቱ)።

ይሁን እንጂ ምስሉ የቆየ እና ከአራት አመታት በፊት ጥቅም ላይ የዋለ በመሆኑ ፤ እንዲሁም ከወቅቱ የአማራ ክልል ጦርነት ጋር ተያያዥነት ያለው ባለመሆኑ ልጥፉ ሐሰት ነው።

MultiFactCheckም ልጥፉን የመረመረ ሲሆን ምስሉ ፅሁፉን የማይደግፍ ሆኖም አግኝቶታል።

የጎግል ምስል ማፋለጊያ (Google reverse image search) ውጤት እንደሚያሳየው ምስሉ ከአራት አመታት በፊት በኦሮሚያ በነበረዉ ተቃውሞ በጥቅምት 12/2012 ዓ.ም. በፌስቡክ ላይ “#Ambo gaafa xiiqii” ወይም “#አምቦ በተቃውሞ ጊዜ” በሚል ፅሁፍ  ተጋርቷል። 

በመሆኑም MultiFactCheck ልጥፉን መርምሮ ምስሉ የቆየ እና ከወቅቱ የአማራ ክልል ግጭት ጋር የማይያያዝ መሆኑን ያረጋገጠ ሲሆን ፤ በልጥፉ እንደተገለፀውም “ጎጃምን መንገድ መዘጋት” የማያሳይ በመሆኑ ሐሰት ብሎታል።

በመንግስትና ራሳቸውን “ፋኖ” ብለው በሚጠሩ የክልሉ ታጣቂ ኃይሎች መካከል ከሚያዝያ 2015 ጀምሮ በአማራ ክልል በመሳሪያ የተደገፈ ጦርነት መኖሩ ይታወቃል።

የፌዴራሉ መንግስት የክልል ልዩ ኃይሎችን ትጥቅ ለማስፈታት የወሰነውን ውሳኔ ባልተቀበሉ የአማራ ክልል ኃይሎች ከመንግስት ጋር እያደረጉት ያለው ጦርነትም ቀጥሎ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች እየተደረገ ሲሆን ፤ ከላይ የጠቀስነውም ትዊት በዚህ አውድ ውስጥ የተዘዋወረ ነው።

The post ሐሰት ፦ ምስሉ የጎጃም መንገድ መዘጋቱን አያሳይም appeared first on MultiFactCheck.

]]>
ሐሰት ፦ ምስሎቹ በዚህ ሳምንት የጦር መሳሪያዎች በፋኖ ኃይሎች መማረካቸውን አያሳዩም https://multifactcheck.org/%e1%88%90%e1%88%b0%e1%89%b5-%e1%8d%a6-%e1%88%9d%e1%88%b5%e1%88%8e%e1%89%b9-%e1%89%a0%e1%8b%9a%e1%88%85-%e1%88%b3%e1%88%9d%e1%8a%95%e1%89%b5-%e1%8b%a8%e1%8c%a6%e1%88%ad-%e1%88%98%e1%88%b3%e1%88%aa/ Tue, 27 Feb 2024 08:54:00 +0000 https://multifactcheck.org/?p=7659 በመሆኑም MultiFactCheck ልጥፉን መርምሮ ምስሎቹ ፤ የፋኖ ኃይሎች መሳሪያዎችን ከመከላከያ ሰራዊት ጎጃም ውስጥ በተጠቀሰው ቀን ስለመማረካቸው እንደማያሳዩ እና ሐሰት መሆናቸውን አረጋግጧል።

The post ሐሰት ፦ ምስሎቹ በዚህ ሳምንት የጦር መሳሪያዎች በፋኖ ኃይሎች መማረካቸውን አያሳዩም appeared first on MultiFactCheck.

]]>
በናኦል ጌታቸው

ቀድሞ ትዊተር በተሰኘውና X በተባለው የማህበራዊ ሚዲያ መድረክ ከ18,500 በላይ ተከታዮች ያሉት “የአማራ ፋኖ ጠቅላይ እዝ Official Page!” የተባለዉ አካውንት “ሰበር ዜና! በጎጃም ዕዝ አስደናቂ ጀብዶችን ፈፅመናል! ለ3ቀን በሰነበተው የጎጃም ውጊያ በቲሊሊ፣ በቋሪት፣ ደጋ ዳሞት የአገዛዙን ጦር በመበተን እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተተኳሾችን በመማረክ 1 ዙ23 አቃጥለን በርካታ የቡድን መሳሪያዎችን ማርከናል” የሚልን ልጥፍ (post) ከሁለት ምስሎች ጋር ፤ በየካቲት 13, 2016 ዓ.ም. ለጥፏል። ይህ ፅሁፍ እስከወጣበትም ቀን ድረስ ትዊቱ ከ15,500 በላይ ተመልካች ሲያገኝ ከ100 ጊዜ በላይም ተጋርቷል (ምስሎቹን ታች ከሚታየዉ ስክርንሾት ይመልከቱ)

ይሁን እንጂ ፤ ምስሎቹ የቆዩ እና ከዚህ ቀደም አገልገሎት ላይ የዋሉ ከመሆናቸውም በተጨማሪ በወቅቱ ያለውን የአማራ ክልል ግጭት አያሳዩም። በመሆኑም ልጥፉ ሐሰት ነው።

MultiFactCheckም ልጥፉን የመረመረ ሲሆን ምስሎቹ ፅሁፉን የማይደግፉ ሆኖም አግኝቷቸዋል።

የመጀመሪያው ምስል 

የጎግል ምስል ማፋለጊያ (Google reverse image search) ውጤት ምስሉ በዚሁ አካውንት ከሳምንታት በፊት የካቲት 1 ፣ በሸዋ ምንጃር ውስጥ የተማረከ መሳሪያ ተደርጎ ተለጥፎ ነበር። እንደገናም በቅርቡ የካቲት 18ም “በሸዋ መንዝና ጅሩ” የተማረከ መሣሪያ በሚል ልጥፍ ጋር አብሮ ተጋርቷል።

ሁለተኛው ምስል

የጎግል ምስል ማፋለጊያ (Google reverse image search) ውጤት እንደሚያመለክተው ሁለተኛው ምስል ለመጀመሪያ ጊዜ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተጋራው በፌስቡክ ላይ ጥቅምት 18, 2014 ዓ.ም. ሲሆን ይህም ይህ የአማራ ክልል ግጭት ከመከሰቱ ከአመት በፊት ነው። ምስሉም በተመሳሳይ ቀን በተለያዩ ገፆችም ተጋርቷል። (በዚህ ማስፈንጠሪያ እና በዚህ ማስፈንጠሪያ ተጠቅመው መመልከት ይችላሉ።)

በመሆኑም MultiFactCheck ልጥፉን መርምሮ ምስሎቹ ፤ የፋኖ ኃይሎች መሳሪያዎችን ከመከላከያ ሰራዊት ጎጃም ውስጥ በተጠቀሰው ቀን ስለመማረካቸው እንደማያሳዩ እና ሐሰት መሆናቸውን አረጋግጧል።

በአማራ ክልል ያለው ግጭት በመንግስትና ራሳቸውን “ፋኖ” ብለው በሚጠሩ የክልሉ አማፂ ኃይሎች መካከል በሚያዝያ 2015 የተጀመረ ነው።

የግጭቱም ዋነኛ መንስኤ ተደርጎ የሚወሰደው የፌዴራሉ መንግስት የክልል ልዩ ኃይሎችን ትጥቅ አስፈታለሁ በማለቱና በክልሉ ያሉ ኃይሎች ውሳኔውን ባለመቀበላቸው ነው። ይህም በጦር መሳሪያ የተደገፈ ግጭት/ጦርነት በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች አሁን ድረስ የቀጠለ ሲሆን ፤ ከላይ የጠቀስነውም ትዊት በዚህ አውድ ውስጥ የተዘዋወረ ነው።

The post ሐሰት ፦ ምስሎቹ በዚህ ሳምንት የጦር መሳሪያዎች በፋኖ ኃይሎች መማረካቸውን አያሳዩም appeared first on MultiFactCheck.

]]>