Federal Police Archives - MultiFactCheck https://multifactcheck.org/category/federal-police/ Shed Light on the Truth. Wed, 11 Sep 2024 14:41:22 +0000 en-US hourly 1 https://wordpress.org/?v=6.7.1 https://multifactcheck.org/wp-content/uploads/2021/07/cropped-multifactcheck-1-150x150.jpeg Federal Police Archives - MultiFactCheck https://multifactcheck.org/category/federal-police/ 32 32 የኢትዮጵያ አየር መንገድን ህግ በመጣስ የተከሰሰው “ጆን ዳንኤል” ከእስር ተለቋል? https://multifactcheck.org/%e1%8b%a8%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%8a%a0%e1%8b%a8%e1%88%ad-%e1%88%98%e1%8a%95%e1%8c%88%e1%8b%b5%e1%8a%95-%e1%88%85%e1%8c%8d-%e1%89%a0%e1%88%98%e1%8c%a3%e1%88%b5-%e1%8b%a8/ Wed, 11 Sep 2024 14:41:20 +0000 https://multifactcheck.org/?p=8529 የሲቪል አቬሽን ህግ በመጣስ እና በሽብር ወንጀል የተከሰሰው ዮሐንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል) ከእስር መለቀቁን የሚገልጽ ቪዲዮ በፌስቡክ ተሰራጭቷል። ተጠርጣሪውን ጨምሮ በክስ መዝገቡ የተከሰሱ ስድስት ግለሰቦች በጊዜ ቀጠሮ ላይ ይገኛሉ።

The post የኢትዮጵያ አየር መንገድን ህግ በመጣስ የተከሰሰው “ጆን ዳንኤል” ከእስር ተለቋል? appeared first on MultiFactCheck.

]]>
በፋሲል አረጋይ

የተጠቀሰው መረጃ፦ የሲቪል አቬሽን ህግ በመጣስ እና በሽብር ወንጀል የተከሰሰው ዮሐንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል) ከእስር መለቀቁን የሚገልጽ ቪዲዮ በፌስቡክ ተሰራጭቷል

ብያኔ:- ሐሰት – ተጠርጣሪውን ጨምሮ በክስ መዝገቡ የተከሰሱ ስድስት ግለሰቦች በጊዜ ቀጠሮ ላይ ይገኛሉ

ነሃሴ 16 ቀን 2016 ዓ/ም ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ ሊደረግ በነበረ በረራ ሁከት እና ብጥብጥ ፈጥረዋል እንዲሁም በሽብር ወንጀል ተሳትፎ አላቸው በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የሚታወቀው ዮሐንስ ዳንኤልን (ጆን ዳንኤል) ጨምሮ 6 ግለሰቦች ክስ ተመስርቶባቸዋል።

በወቅቱም በነበረው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ምክንያት አውሮፕላኑ መብረር እንደማይችል የአየር መንገዱ የበረራ ደህንነት ሰራተኞች በሚገልጹበት ጊዜ ተሳፋሪዎቹ ከአውሮፕላን “አንወርድም” በማለት ከሰራተኞቹ ጋር ውዝግብ ውስጥ ሲገቡ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በማህበራዊ ሚዲያ ተሰራጭቷል።

ይሄንን ተከትሎም የአዲስ አበባ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን በእነዮሀንስ ዳንኤል ላይ በሽብርተኝነት እና የአቬሽን ሕግን መተላለፍ በሚል በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ክስ መስርቶባቸዋል።

ነሃሴ 23 ቀን 2016 ዓ/ም 34ሺ ተከታዮች ያሉት “yuti nass” የሚል ስያሜ ያለው የፌስቡክ ገጽ  “በዋስ ተለቅቄያለሁ አድናቄዎቼ አመሰግናለሁ” ከሚል ጽሑፍ ጋር 23 ሴኮንድ ርዝመት ያለውን የዮሃንስ ዳንኤል ቪዲዮ ለጥፏል። ይሄ ጽሑፍ ለንባብ እስከበቃበት ቪዲዮው 1.5 ሚሊየን ዕይታ እና 34ሺ ግብረ መልስ አግኝቷል። በተጨማሪም 2600 አስተያየት ያገኘው ልጥፉ ለሌሎች የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ተደራሽ እንዲሆን 331 ጊዜ ተጋርቷል።

በተጨማሪም መረጃው ከፌስቡክ በተጨማሪም በዩቲውብ እና ቲክቶክ ላይ መሰራጨቱን የጉግል ምስል ማሰሻ (Google Lens) ያሳያል።


በመረጃው ላይ እንደቀረበው ጆን ዳንኤል በሚል የማህበራዊ ሚዲያ ስም የሚታወቀው ዮሐንስ ዳንኤል በዋስ ተለቋል? የሚለውን MFC አጣርቷል። 

በዚህም ትክክለኛው ቪዲዮ የተለጠፈው ከአንድ አመት በፊት ነሃሴ 15 ፣ 2015 ዓ/ም 2.3 ሚሊየን ተከታይ ባለው የዮሐንስ ዳንኤል የቲክቶክ አካውንት መሆኑን MFC አረጋግጧል። የ 43 ሴኮንድ ርዝመት ያለው ቪዲዮ ዮሐንስ ዳንኤል በማህበራዊ ሚዲያ የሚያደርገውን የበጎ አድራጎት ስራ በተመለከተ የሚሰጠውን ማብራሪያ ያሳያል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ ከተከሰተው ጉዳይ በኋላ በማግስቱ ነሃሴ 16 ፣ 2016 ዓ/ም የአዲስ አበባ ፖሊስ እነ ዮሐንስ ዳንኤልን በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በማቅረብ “የአየር መንገዱን የአየር መንገዱን ሥራ በማስተጓጎል ወንጀል” መጠርጠራቸውን በመግለጽ፣ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ጠይቆባቸው ነበር፡፡

እነ ዮሐንስ ዳንኤልም በጠበቆቻቸው በኩል የዋስትና ጥያቄ አቅርበዋል። የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤቱም የ20 ሺህ ብር ዋስትና በማስያዝ እንዲወጡ ቢፈቅድም የተጠረጠሩበት አየር መንገዱን በማወክ ብቻ ሳይሆን በሽብር ወንጀል እንደሆነ በመግለጽ ከእስር ሳይለቀቁ ጉዳዩን የፌደራል ፖሊስ እንዲይዝ ተደርጎ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት እንዲቀርቡ ተደርጎ ክርክር ተደርጓል።

ነሃሴ 21 ቀን 2016 ዓ/ም በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡት ተጠርጣሪዎቹ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የፈቀደው  የዋስትና መብት እንዲጸናላቸው ጠይቀዋል። ፍርድ ቤቱ የዋስትና ፈቃዱ የተሰጠው ‹‹ሁከትና ብጥብጥ›› በሚል ለቀረበለት ክርክር እንጂ፣ በሽብርተኝነት ስለመጠርጠራቸው ስለማያስረዳ በሚል ለፌደራል ፖሊስ መርማሪ ቡድን የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ ለ ጳጉሜ 4 ፣ 2016 ዓ/ም ቀጠሮ ሰጥቷል።

በመሆኑም በማህበራዊ ሚዲያ የተላለፈው ቪዲዮ የቆየ ሲሆን በቪዲዮው ላይ ዮሐንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል) ከቀረበበት የሽብር እና የአቬሽን ህግ ጥሰት ክስ ጋር በተገናኘ በዋስ እንደተለቀቀ ተደርጎ የቀረበው መረጃ ሐሰት መሆኑን MFC አረጋግጧል።

The post የኢትዮጵያ አየር መንገድን ህግ በመጣስ የተከሰሰው “ጆን ዳንኤል” ከእስር ተለቋል? appeared first on MultiFactCheck.

]]>
Image of Captured Soldier Not Fit the Claim https://multifactcheck.org/image-of-captured-soldiers-not-fit-the-claim/ Tue, 25 Jun 2024 16:48:59 +0000 https://multifactcheck.org/?p=8168 An X account claimed that "members of the 51st Regiment were destroyed in today's battle and that the pictured individuals were captured during an operation in Gondar." However, the image is outdated and unrelated to the current conflict in Amhara Regional State.

The post Image of Captured Soldier Not Fit the Claim appeared first on MultiFactCheck.

]]>
By Naol Getachew

Claim: An X account claimed that “members of the 51st Regiment were destroyed in today’s battle and that the pictured individuals were captured during an operation in Gondar.”

Verdict: False. The image is outdated and unrelated to the current conflict in Amhara.

An X account named “የአማራ ፋኖ ጠቅላይ እዝ Official Page!” with over 21,000 followers shared an image with an Amharic caption in which a soldier appears to narrate that they could not anymore fight against the Fano militiamen and members of the 51st Regiment were destroyed in a battle. The tweet gave an impression also that the pictured individual(s) was (were) captured during an operation in Gondar, a city located to the north of the Amhara Regional State. The post received over 87 retweets and 8,000 views(see image below).

However, the image is outdated and unrelated to the ongoing conflict in Amhara Region – the conflict that erupted in April 2023 between the Ethiopian government and Fano militants. MFC observed that the aforementioned Twitter account repeatedly spreads disinformation.

Three weeks ago, on May 2, the same image was shared by a Facebook account named Mereja Tv, which has over 1.2 million followers. The post claimed that the image was related to the current conflict in Amhara, which is untrue (see image below).

However, this image too is outdated and unrelated to the current conflict in Amhara.

A Google Reverse Image Search reveals the image was first shared on social media on October 30, 2021, by a social media account named Stalin Gebreselassie. This individual is known for expressing support for the TPLF/TDF – a political party and an armed group – during the war in Tigray region of Ethiopia. Currently, he is based in Washington DC, USA, and works at Zara Media Network, a media that he reportedly founded. 

Based on the result of the tool we used, MFC confirmed that the image shared by the X account claiming that “members of the 51st Regiment were destroyed in today’s battle and that the pictured individual(s) was (were) captured during an operation in Gondar” is false. 

Context

The conflict in Amhara Regional State began in April 2023 when the Ethiopian military raided the Amhara region to disarm regional special forces and Fano militias – who disregarded the government’s announcement of disarming and integrating them into its formal security forces. This sparked resistance with the Fano Militiamen, finally leading to clashes with the federal government’s military forces. The situation remains tense, which has been resulting in death of civilians, causing significant damage to properties, and displacing hundreds of thousands people. Thus, the post has been circulating in this context. 

The post Image of Captured Soldier Not Fit the Claim appeared first on MultiFactCheck.

]]>
እውን አቶ ታዲዮስ ታንቱ ከእስር ተፈትተዋል? https://multifactcheck.org/%e1%8a%a5%e1%8b%8d%e1%8a%95-%e1%8a%a0%e1%89%b6-%e1%89%b3%e1%8b%b2%e1%8b%ae%e1%88%b5-%e1%89%b3%e1%8a%95%e1%89%b1-%e1%8a%a8%e1%8a%a5%e1%88%b5%e1%88%ad-%e1%89%b0%e1%8d%88%e1%89%b5%e1%89%b0%e1%8b%8b/ Sat, 08 Jun 2024 17:04:53 +0000 https://multifactcheck.org/?p=8121 “አቶ ታዲዮስ ታንቱ ከእስር ተፈትተዋል” የሚሉ መረጃዎች በፌስቡክ እና በትዊተር ላይ እየተሰራጩ ይገኛሉ። ይሁን እንጂ መረጃዎቹ ሐሰት ናቸው።

The post እውን አቶ ታዲዮስ ታንቱ ከእስር ተፈትተዋል? appeared first on MultiFactCheck.

]]>
በናኦል ጌታቸው

የተጠቀሰው መረጃ፦ “አቶ ታዲዮስ ታንቱ ከእስር ተፈትተዋል” የሚሉ መረጃዎች በፌስቡክ እና በትዊተር ላይ እየተሰራጩ ይገኛሉ።

ብያኔ፦ መረጃዎቹ ሐሰት ናቸው።

“አቶ ታዲዮስ ታንቱ ከእስር ተፈትተዋል” የሚሉ መረጃዎች በፌስቡክ ( ለአብነት ይህንንይህንን ፣ ይህንንናይህንን መስፈንጠሪያዎች ተጠቅመው ይመልከቱ)  እና በትዊተር ላይ ( ለአብነትይህንንናይህንን መስፈንጠሪያዎች ተጠቅመው ይመልከቱ) በግንቦት 30/ 2016 አ.ም. ሲሰራጩ ውለዋል።

ይሁን እንጂ  በተለያዩ አካውንቶች የተሰራጨው መረጃ ሐሰት ነው።

መረጃዎቹ ሲሰራጩም ከአንድ ፎቶግራፍ ጋር መዘዋወራቸውን ለመመልከት ተችሏል። MFC ፎቶውን በGoogle Reverse Image ያጣራ ሲሆን ምስሉ ከሶስት አመት በፊት አቶ ታዲዮስ ከእስር መፈታታቸውን ተከትሎ በፌስቡክ ላይ የ“እንኳን አደረስዎ” መልእክት ሲያሰተላልፉ የተሰራጨ ምስል መሆኑን ለማወቅ ተችሏል (ለአብነት ይህንንይህንንይህንንይህንን መስፈንጠሪያዎች ተጠቅመው ይመልከቱ)። ይሁን እንጂ ፎቶው ለመጀመሪያ ጊዜ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በመታየቱን እንጂ በትክክል መቼ እንደተነሳ ለማወቅ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

በወቅቱ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በወንጀል ተጠርጥረው ከሚያዝያ 27 ቀን 2013 አንስቶ ለሰላሣ ቀናት በእስር ላይ ከቆዩ በኋላ በአራት ሺህ ብር ዋስትና ነበር የተለቀቁት

ከዚህም በተጨማሪ MFC  የአቶ ታዲዮስ ታንቱ ባለቤት የሆኑትን ወ/ሮ ጸጋ ሞገስን በስልክ ያነጋገረ ሲሆን መረጃው ሐሰተኛ መሆኑን አረጋግጠዋል። 

ከዚህም በተጨማሪ የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን በፌስቡክ ገጹ ላይ መግለጫ ያወጣ ሲሆን “አቶ ታዲዮስ ታንቱ በዛሬው ዕለት ከእስር ተፈቱ ተብሎ በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የተሠራጨው መረጃ ስህተት መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን” በማለት ገልጿል።

በመሆኑም ከላይ በተጠቀሱት መረጃዎች መሰረት MFC አቶ ታዲዮስ ታንቱ ከእስር ተፈትተዋል የሚለው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን አረጋግጧል። 

አውድ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በኢትዮጵያ የሚዲያና የፖለቲካ መድረክ የታወቁ ሰው ሲሆኑ ለረጅም ጊዜ አነጋጋሪ የታሪክ ሀሳቦችን በተለያዩ መድረኮችና ሚዲያዎች ላይ በመግለጽ ይታወቃሉ። በፍትሕ ጋዜጣ ፣ ፋክት መፅሔት ፣ ልዕልና ጋዜጣ ፣ አዲስ ታይምስ መፅሔትና እና በሌሎች የህትመት ሚዲያዎች ላይ የአርበኞችን ታሪክና ሌሎች ሀሳቦችን ሲፅፉ የቆዩ ሲሆን ከቅርብ አመታት ወዲህ ደግሞ በዩቲዩብ ሚዲያዎች በእንግድነት በመቅረብ አነጋጋሪ ቃለ መጠይቆችን ሲሰጡ ቆይተዋል። በዚህም ምክንያት በተለያዩ ጊዜያት ለእስር ሲዳረጉና ሲፈቱ ቆይተዋል። የአሁን እስርም በግንቦት 10/2014 የ “ጥላቻ ንግግር በማሰራጨትና የእርስ በእርስ ግጭት በመቀስቀስ” ወንጀል ተጠርጥረው ነው።

በ2012 አ.ም. በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኩል የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር አዋጅ መውጣቱ ይታወሳል። 

በ2012 አ.ም. በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኩል የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር አዋጅ መውጣቱ ይታወሳል። 

አዋጁ በተራ ቁጥር 4 ስር “ማንኛውም ሰው የጥላቻ ንግግርን በብሮድካስት፣ በህትመት ወይም በማህበራዊ ሚዲያዎች ወይም በሌላ ተመሳሳይ ዘዴዎች አማካኝነት በጽሁፍ፣ በምስል፣ በድምጽ ወይም በቪዲዮ ማሰራጨት የተከለከለ ነው፡፡” ይህን በማለት የጥላቻ ንግግር ስለመከልከሉ ያሰፈረ ሲሆን ፤ የጥላቻ ንግግር ያደረገ ማንኛውም ሰው እስከ ሁለት አመት በሚደርስ ቀላል እስራት ወይም ከብር 100 ሺ ያልበለጠ መቀጮ እንደሚቀጣ ፣ እንዲሁም በጥላቻ ንግግሩ ምክንያት ጥቃት የተፈጸመ እንደሆነ ቅጣቱ ከአንድ አመት እስከ አምስት አመት የሚደርስ ቀላል እስራት እንደሚሆንም አዋጁ አስቀምጧል።

The post እውን አቶ ታዲዮስ ታንቱ ከእስር ተፈትተዋል? appeared first on MultiFactCheck.

]]>
Circulated Video not Suggest Residents of Addis Ababa Taking Part in “Zemecha Wubante” https://multifactcheck.org/circualted-video-not-suggest-addis-ababeans-taking-part-in-zemecha-wubante/ Tue, 02 Apr 2024 17:20:12 +0000 https://multifactcheck.org/?p=7933 The shared video alleging that Addis Ababa residents are taking part in the so called "Zemecha Wubante" is a false claim because the video is outdated and unrelated to the current conflict in Amhara.

The post Circulated Video not Suggest Residents of Addis Ababa Taking Part in “Zemecha Wubante” appeared first on MultiFactCheck.

]]>
By Naol Getachew

Claim: An X account named Amhara Youth Association with significant followers shared a video alleging that Addis Ababa residents are taking part in the so-called “Zemecha Wubante” (roughly meaning Wubante’s Campaign/March).

Verdict: False, as the video is outdated and unrelated to the current conflict in Amhara.

Image 1: A screenshot taken from the appears to show youth and federal police marching together.

On March 22, 2024, an X account named Amhara Youth Association, with over 36,000 followers, tweeted a video claiming that residents of Addis Ababa were engaged in the so-called “Zemecha Wubante” (meaning Wubante’s Campaign). The tweet has garnered over 25,000 views and more than 110 retweets.

The video was accompanied by an Amharic caption translated as: “Wubante’s Campaign has begun in Addis Ababa! The youth of Pisa [one of the most vibrant areas in the capital] are awakening at last. Protests are erupting. We have confirmed a bomb attack on a bus transporting an official.”

Image 2: A screenshot of the tweet from the Amhara Youth Association

However, MultiFactCheck (MFC) investigated the claim utilizing the Fake news debunker by InVID & WeVerify and discovered that the video in the tweet is an old clip from a 2018 clash incident involving Oromo youths (Qeerroo) and Addis Ababa youths during welcoming event for leaders of the exiled Oromo Liberation Front (OLF). This occurrence transpired five years ago.

Image 2: Another screenshot showing the image was from 2018

The video was circulated on various social media platforms, including Facebook (Link ) and Youtube (Link ) on September 14, 2018. Thus, relating that incident to the current “Zemecha Wubante” in Addis Ababa is not based on fact. Consequently, MFC rated this claims as False.

Context 

The Amhara region is in a state of emergency due to the fighting that erupted last July between Fano militiamen and the Ethiopian securitz forces.

Amid this conflict, Wubante Abate, a prominent Fano leader was reportedly killed in action. 

Thus, there are unconfirmed information circulating on social media that the Fanos are on a revenge campaign inspired by their fallen leader. 

The post Circulated Video not Suggest Residents of Addis Ababa Taking Part in “Zemecha Wubante” appeared first on MultiFactCheck.

]]>
Perpetrators Abusing a Person with Knife and Gun was Claimed on OLF-OLA https://multifactcheck.org/perpetrators-abusing-a-person-with-knife-and-gun-was-claimed-on-olf-ola/ Wed, 06 Mar 2024 16:48:49 +0000 https://multifactcheck.org/?p=7792 Social media accounts claimed that the perpetrators of recently circulated video of armed soldiers threatening a victim with a knife and a gun were the fighters of the Oromo Liberation Army (OLA). After cross-checking the claims and the response from the OLA, the MultiFactCheck (MFC) rated the claims as Misleading

The post Perpetrators Abusing a Person with Knife and Gun was Claimed on OLF-OLA appeared first on MultiFactCheck.

]]>
By Alemu Teshome

_______________________________________________________

Claims: Social media accounts claimed that the perpetrators of recently circulated video of armed soldiers threatening a victim with a knife and a gun were the fighters of the Oromo Liberation Army (OLA)

Verdict: After cross-checking the claims and the response from the OLA, the MultiFactCheck (MFC) rated the claims as Misleading

____________________________________________________________

During the last days of February, social media users shared a video content on their X (formerly Twitter) and on Tiktok accounts claiming that the perpetrators who were  seen in the uniform of the Ethiopian National Defense Force (ENDF) and Federal Forces physically harassing and intimidating a young man with a knife and a gun were members of the Oromo Liberation Front-Oromo Liberation Army (OLF-OLA). 

Anteneh Shiferaw, who has close to 6000 followers on his X account, wrote: “This’s the Savagery and Barbaric act of Oromo Liberation Front [OLF]”. This specific tweet was viewed by more than 78,000 people, received hundreds of interactions, and reposted by thousands of people (see below screenshot). 

Image 1: Screenshot from Anteneh’s X account claiming the OLF-OLA harassing the young man.

This content became a potential source of mis/disinformation triggering hate speech with the allegations that the incident happened against an Amhara victim by the OLF-OLA soldiers. The content also bears slurs that have the potential of inciting or exacerbating conflicts between the Oromo and the Amhara people, the two populous ethnic groups in Ethiopia. 

Another X account holder with the name Antonio, who has more than 33,000 followers, for instance, wrote: “What has been happening in Wellega [a place in the Oromia Regional State] for years now came to the doorsteps of every Amhara.” This content was again viewed by close to 11,000 people.  

Image 2: Screenshot of Antonio’s X account claiming the victim was from an Amhara ethnic member.

Another twitter named Ras Tafari wrote that “the #Amhara people are fighting with a beast” not only today but starting “600 years ago”, which could give others the picture that the Oromo people have been ‘invaders, assimilators, and killers’. 

Image 3: Screenshot from X account holder disseminating false and demeaning content against Oromo with a video allegation.

However, the OLF-OLA issued a statement stating that the perpetrators of the physical abuse against the young man were the members of the ENDF and of the Federal Police operating in the Goro Dola district in the Guji Zone of Oromia Regional State. The statement elaborated that the victim was also found to be a young man named Ahmed Qasim Dube living in Saraansa village, which is located in the Zone. 

The OLF-OLA stated its non-engagement in the action by accusing the ENDF and the Federal Police for what it said was “inhumane treatment and barbaric act” committed by “uniformed Ethiopian security forces’. 

Such human rights violations and related atrocities in the conflict-troubled Ethiopia are not the first time. Beside these gross violations of human rights against civilians, social media users have been also manipulating such audiovisual content to fit into their narratives that exacerbate conflicts on the ground. In June 2023, for instance, similar content that happened in January 2022 in Benishangul Gumuz Regional State was shared on social media as if it happened in the Amhara Regional State against the Amhara civilians. 

In light of what was shared by X account holders and the statement issued by OLF-OLA as a response to the claimants, MFC rendered the claims as misleading.

The post Perpetrators Abusing a Person with Knife and Gun was Claimed on OLF-OLA appeared first on MultiFactCheck.

]]>
ሁለቱ ምስሎች በየካቲት 20/2016 በምስራቅ ወለጋ ጊዳ አያና ወረዳ ተፈፀመ የተባለውን ጥቃት አያሳዩም https://multifactcheck.org/%e1%88%81%e1%88%88%e1%89%b1-%e1%88%9d%e1%88%b5%e1%88%8e%e1%89%bd-%e1%89%a0%e1%8b%a8%e1%8a%ab%e1%89%b2%e1%89%b5-20-2016-%e1%89%a0%e1%88%9d%e1%88%b5%e1%88%ab%e1%89%85-%e1%8b%88%e1%88%88%e1%8c%8b/ Mon, 04 Mar 2024 17:35:49 +0000 https://multifactcheck.org/?p=7749 በመሆኑም MFC የተዘዋወሩትን ፎቶዎች በመመርመር ሁለቱ ምስሎች በየካቲት 20/2016 ዓም በምስራቅ ወለጋ ጊዳ አያና ወረዳ ከተፈፀመው ጥቃት ጋር የሚያያዙ አለመሆናቸውን በማረጋገጡ ፤ ሐሰት ሲል በይኗቸዋል።

The post ሁለቱ ምስሎች በየካቲት 20/2016 በምስራቅ ወለጋ ጊዳ አያና ወረዳ ተፈፀመ የተባለውን ጥቃት አያሳዩም appeared first on MultiFactCheck.

]]>
በናኦል ጌታቸው

________________________________________________________________________________

የተጠቀሰው መረጃ ፦ ሁለት ፎቶዎች የረቡዕ የካቲት 20/2016ቱ የምስራቅ ወለጋ ጊዳ አያና ወረዳ ጥቃት የሚያስረዱ ተደርገው በፌስቡክ ላይ ተሰራጭተዋል።

ብያኔ ሁለቱ ምስሎች በየካቲት 20/2016 ዓ.ም. በምስራቅ ወለጋ ጊዳ አያና ወረዳ ከተፈፀመው ጥቃት ጋር የሚያያዙ ባለመሆናቸውን ፤ ሐሰት ሲል MFC በይኗቸዋል።

_________________________________________________________________________________

በርካታ የፌስቡክ አካውንቶች “በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ በንፁሀን ላይ የደረሰ ጥቃትን” በማውገዝ ሀዘናቸውን የገለፁ ሲሆን ፤ በፅሁፋቸውም ሁለት ምስሎችን እያያያዙ በየካቲት 21/2016 ፖስት አድርገዋል (በስክሪንሾቱ በሚታየው መልኩ)። ለአብነትም Sagalee Wareegamtoota WangeelaaGemechisa HirpaDaandii ElemooJabaa KeenyaSiraaji EliyaasiHamatamaan Leenca ፣ በመሳሰሉት አካውንቶች የተለጠፉትን ፖስቶች መጥቀስ የሚቻል ሲሆን ፣ እያንዳንዳቸውም ከ 20 እስከ 87 የሚደርሱ ግብረ መለሶች አግኝተዋል።

ምስል 1 :- ይህ ምስል Sagalee Wareegamtoota Wangeelaa የተባለውና 6,900 ተከታዮች ያሉት አካውንት በ “ጊዳ አያናው” ጥቃት ማዘኑን የገለፀበት ሲሆን በፅሁፉ መጨረሻም “ማሳሰቢያ” በማለት ምስሎቹ የጊዳ አያና መሆናቸውን የሚገልፅበት ስክሪንሾት ነው

በአፋን ኦሮሞ ተፅፈው የተዘዋወሩት ፅሁፎች ፤ ክስተቱ መፈፀሙንና የሶስት ሰዎች ሕይወት “ፋኖ ናቸው” በተባሉ ታጣቂዎች መፈፀሙን ከስፍራው መረጃ ማግኘታቸውን የተለያዩ ዘገባዎች ወጥተዋል። ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ የአካባቢውን ነዋሪዎች ዋቢ አድርጎ እንደዘገበውም ጥቃቱ የተፈፀመው ረቡእ የካቲት 20/2016 ነው (ይህንን መስፈንጠሪያ ይመልከቱ)።

ይሁን እንጂ የተለያዩ የፌስቡክ አካውንቶቹ የተጠቀሰውን ጥቃት ለማስረዳት የተጠቀሟቸው ሁለቱ ምስሎች ግን የቆዩ በመሆናቸው ፎቶዎቹ ረቡዕ የካቲት 20/2016 ዓ.ም. ተፈፀመ ለተባለው ክስተት ማስረጃ ተደርገው መቅረባቸው አሳሳች ነው።

በምዕራቡ የኢትዮጵያ ክፍል በተለይም በምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ ለበርካታ አመታት የዘለቀ ግጭትና የሰላም መደፍረስ መኖሩ የሚታወቅ ነው። ግጭቶቹም አንዴ በመንግስት እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት መካከል ፤ ሌላ ጊዜ በፋኖ ኃይሎችና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት መካከል እና በሌሎች ኢ-መደበኛ ታጣቂዎች መካከል ሲደረግም ቆይቷል። በነዚህ ጥቃቶችም የበርካታ ንፁሐን ዜጎች ህይወት ማለፉንም በተለያዩ ጊዜያት የሚወጡ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ርፖርት ያመለክታል። 

በተመሳሳይም በዚሁ ሳምንት የካቲት 20/2016 በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ጊዳ አያና ወረዳ በተፈፀመ እና “የፋኖ ታጣቂዎች ፈፅመውታል” በተባለው ጥቃት የ3 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተዘግቧል። የፌስቡክ ፖስቶቹም በዚህ አውድ ውስጥ የተሰራጩ ናቸው። 

ይሁንና የጎግል ምስል ማፋለጊያ (Google Reverse Image Search) ውጤት እንደሚያሳየው ፤ ምስሎቹ ከሁለት ወራት በፊት ከህዳር 30/2016 በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲዘዋወር ነበር (እነዚህን ማስፈንጠሪያዎች ተጠቅመው ይመልከቷቸው)።

ምስሎቹም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በተሰራጨው መልኩ ‘የተከሰተን ግደያ’ የሚያሳይ ሳይሆን በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት ምክንያት ‘ሕፃፅ’ በተባለ የትግራይ አካባቢ በኤርትራ ሰራዊት ተፈፅሟል ያሉትን “የሰብአዊ መብት ጥሰት” ከሚዳስስ ፊልም ላይ የተወሰደ ቀረፃ መሆኑን ሕፃፅ የተሰኘው ፊልም ዳይሬክተር Resom Aredom በፌስቡክ ላይ አጋርቷል።

ምስል 2 :- ይህ ምስል የፊልሙ ፀሐፊና ዳይሬክተር እንደሆነ የሚናገረው ርእሶም አረዶም በማህበራዊ ሚዲያው ላይ በተሳሳተ መልኩ ስለተዘዋወሩት ሁለቱ ፎቶዎች ያጋራበት ስክሪንሾት ሲሆን ፣ የተፃፈው የትግርኛ ፅሁፍም በፎቶዎቹ ላይ የሚታዩት የፊልሙ ኣባላት መሆናቸውን ይገልፃል። 

እንደዚሁም የፊልሙ ፕሮዲዩሰር እንደሆነ የሚገልፀው TK Adver ከአንድ ወር በፊት ስለሚዘዋወረው ፎቶ በFeb 2 እንዲህ ብሎ አጋርቶ ነበር። “ይህ ምስል የተወሰደው በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ፊልም በምንሰራበት ወቅት ነው። አንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ይህንን ምስል ለፖለቲካዊ መልእክቶች እየተጠቀሙበት ነው።”

ምስል 3 :- ይህ ምስል “ሕፃፅ” የተሰኘው በትግርኛ ቋንቋ የተሰራው ፊልም ፖስተር መሆኑን የፊልሙ አባላት ካጋሩት መረጃዎች ለማወቅ ተችሏል።

ሌሎች ከቀረፃ ጀርባ ምስሎችንም ስንምለከት ተመሳሳይ ተዋናዮችና የፊልም ካሜራ የያዙ ባለሙያዎችን እንመለከታለን (ከታች ያለውን ስክሪንሾት ይመልከቱ)።

ሁለት አመት በዘለቀውና በፕሪቶሪያው ስምምነት ማብቂያ ያገኘው የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስትና የትግራይ ሀይሎች ጦርነት ብዙ ደም ያፋሰሰ መሆኑ የሚታወስ ነው። በተለይም ከኢትዮጵያ ጎን ተሰልፎ የትግራይን ሀይሎች ሲዋጋ የነበረው የኤርትራ ሰራዊት በትግራይ ክልል በንፁሀን ላይ የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈፅሟል ተብሎ በተለያዩ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ሪፖርቶች ሲወጡ ቆይተዋል። 

ከእነዚህ መካከልም አንደኛው በኤርትራ ሰራዊት በሕፃፅ ከተማ ተፈጽሟል የተባለው ጭፍጨፋ ነው። ይህም “ሕፃፅ” የተሰኘው ፊልም ይህንን ክስተት የሚዘግብ እንደሆነ ዳይሬክተር እንደሆነ የሚገልፀው ርእሶም ኣረዶም ባደረጋቸው ቃለ መጠይቆች ገልጿል።

በመሆኑም MFC የተዘዋወሩትን ፎቶዎች በመመርመር ሁለቱ ምስሎች በየካቲት 20/2016 ዓም በምስራቅ ወለጋ ጊዳ አያና ወረዳ ከተፈፀመው ጥቃት ጋር የሚያያዙ አለመሆናቸውን በማረጋገጡ ፤ ሐሰት ሲል በይኗቸዋል።

The post ሁለቱ ምስሎች በየካቲት 20/2016 በምስራቅ ወለጋ ጊዳ አያና ወረዳ ተፈፀመ የተባለውን ጥቃት አያሳዩም appeared first on MultiFactCheck.

]]>